Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 8

2023-03-28 13:44:35 የሰብል ምርት ግምትን አላግባብ በመቀነሰ ከሰብል ምርት ታክሰ ሊገኝ የሚችለውን 8.9 ሚሊዮን ብር መንግስት እንዲያጣ ያደረገ የግብርና ጽ/ቤት ሓላፊ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል  በፅኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጣ
~~~~

ተከሳሸ በህሩ አህመድ የመተማ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ በነበሩበት 2011 ዓም ከሰብል ምርት ታክሰ ለመሰብሰብ በወረዳው የሚገኙ የእርሻ ኢንቨስተሮች 2010 ዓም ለ2011 ዓም ያመረቱት ምርት በሰብል ገማች ኮሚቴ ተገምግሞ የፀደቀ ሲሆን ተከሳሹ ያልተገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ተገምግም የፀደቀውን የሰብል ግምት አላግባብ የቀነሰ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።

ተከሳሹም የመንግስትን ስራ በማያመች አኳሗን በመምራት የሰብል ምርት ግምገማውን በመቀነሱ መንግስት ሊያገኝ ይችል የነበረውን 8.9 ሚሊዮን ብር እንዲያጣ ያደረገ በመሆኑ የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤህ ህግ ከመተማ ወረዳ ፖሊሰ ጽ/ቤት ተጣርቶ የመጣለትን መዝገብ በመመርመር ለምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ተከራክሯል።

ዐቃቤ ህግም የሙስና ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 13(3) በመጥቀሰ የመንግሰትን ስራ በማያመች አኳሃን በመምራት የሙስና ወንጀል ከሶ ሲከራከር የቆየ ሲሆን የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ዛሬ በቀን 14/07/2015 ዓም በዋለው ችሎት የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል

ፍ/ቤቱም የዐቃቤ ህግንና የተከሳሹን የቅጣት አስተያየት ካዳመጠ በሗላ ዛሬ ከሰዓት በነበረው ችሎት #የ6አመት ከ6ወር ፅኑ እስራትና #የሶስት ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ ፍርድ ሰጥቷል።

መረጃው የምዕ/ጎ/ዞ/ፍ /መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሒደት ነው
14/07/2015 ዓም
313 viewsAlemshet Miheretie, 10:44
ओपन / कमेंट
2023-03-28 13:42:51 በከባድ እምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የተከሰሱት ግለሰቦች ተቀጡ፡፡
1ኛ. ተከሳሽ ሳ/ን ኢብራሄም ሀሰን 2ኛ. ተከሳሽ ኮ/ል አሰፋ ሞገስ 3ኛ ተከሳሻ ረ/ኢ ተሻለ አመዴ 4ኛ ተከሳሽ ሞሳየ ጀምበሩ እርስ በእርሳቸዉ በመመሰጣጠር በቀን 14/11/2014 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 11፡00 ስዓት ጃናሞራ ወረዳ ባህር አምባ ቀበሌ ልዩ ቦታዉ 32ኛ ሻለቃ ኦረድናስ ክፍል ከጦር መሳሪያ እና ግምጃ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ለክፍለ ጦሩ መሳሪያና ጥይት ላስረክብ ነዉ በማለት የሻለቃዉ አስተዳደርና ሎጅስቴክ ሃላፊ የሆነዉን 3ኛ ተከሳሽ እንዲያስረክበዉ ከጠየቀ በኋላ እስቶር ዉስጥ እንዲያድር በማመቻቸት ከተረከበዉ 1 ኤስ-ኬስ እና 15 ሰደፍ ክላሽ መሳሪያ ዉጭ 3832 የክላሽ ጥይት በመጨመር በቀን 15/11/2014 ዓ/ም ጠዋት በማዳበሪያ እና በወታደራዊ ሻንጣ የተቋጠሩትን የጦር መሳሪያ በሌሎች የልዩ ሃይል እገዛ ከጃናሞራ ወረዳ ወደ መንገድ በማቅረብና በመኪና ጭኖ ወደ ደባርቅ ከተማ በማምጣት በዩኒክላንድ ሆቴል አልጋ በመያዝ 1 እግር ታጣፊ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይት ጋር፣2 እግር ታጣፊ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይት ጋር፣በ2 ሻንጣ 2754 የክላሽ ጥይት፣በሚሌተሪዉ 30 የክላሽ ጥይት፣እና 7 የክላሽ ካዝና ይዞ የተገኘ፣ 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ከላይ የተገለፁትን መሳሪያዎች አብሮ የወሰደና 2 እግር ክላሽ መሳሪያ ከመሰል 30 ጥይት ጋር ይዞ ከዚያ ሆቴል መዉጫ ላይ ይዞ የተገኘ፣3ኛ ተከሳሽ ደግሞ እስቶር ዉስጥ እንዲያድር በማድረግ ያሥወሰደ እና የተመሳጠረ እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ያመጡትን የጦር መሳሪያ በመቀበልና በመተባበር 2 እግር ታጣፊ ክላሽ ከ30 ጥይት ጋር፣928 የክላሽ ጥይት እና 6 ካዝና በመያዝ የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ የሆነ በመሆኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/፣የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 31/2/ን በመተላለፍ በፈፀሙት በዋና ወንጀል አድራጊነት በከባድ እምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ስለሆነም የደባርቅ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀል ምርመራ ክፍል አጣርቶ የላከውን መዝገብ የሰሜን ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ክስ መስርቶበት የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲያከራከር ከቆየ በኋላ ተከሳሾች በመከላከያ ምስክሮች ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸዉ ፍርድ ቤቱ መጋቢት 11/2015 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሾቹን ያስተምራል፤ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ያለዉን 1ኛ ተከሳሽን 5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራትና የ2000 ብር እንዲሁም 2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾችን በእያንዳንዳቸዉ 6 ዓመት ፅኑ እስራትና የ3000 ብር ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡
326 viewsAlemshet Miheretie, 10:42
ओपन / कमेंट
2023-03-28 13:42:22 የ13ዓመት ህፃን አስገድዶ የደፈረዉ ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

ተከሳሽ አቶ ፋሲል ክፋለ እየሱስ እድሜ 42  አድራሻ ጎንደር  ከተማ ቀበሌ 17 ሲሆን ተከሳሽ ተቃራኒ ፆታ ከሆነችው 13 አመት  ያልሞላት ታዳጊ ህፃን ጋር የካቲት 4/ 06 /2015 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 3 :00 ስዓት  አካባቢ  በጣቁሳ ወረዳ  ጨዉድባ ቀበሌ ከግል ተበዳይ ወላጆች መኖሪያ ቤት ህፃኗን  አስገድዶ ክብረ ንፅህናዋ ላይ በደል ያደረሰባት በመሆኑ  በወረዳዉ በወንጀል  ምርመራ  የፖሊስ ክፋል   ማጣራት  ተደርጎ ለጣቁሳ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት  የወንጀል ዐቃቢ ህግ እንዲደርስ የተደረገ ሲሆን የወረዳዉ ዐቃቢ ህግም የሰነድና የሰዉ ማስረጃዎች  በማጠናከር  በ1996 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣዉ  የኢ ፈደሪ  የወንጀል ህግ አንቀጽ 627 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የተመለከተውን  ተላልፎ  በመገኝቱ ዐቃቢ ህግ በኩል ለጣቁሳ ወረዳ ፋርድ ቤት ክስ አቅርቧል።

በዚህ መነሻ መሰረት በማድረግ የጣቁሳ ወረዳ ፋርድ ቤት  የወንጀል ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ከቆየ  በኋላ ዐቃቢ ህግ እንደ ክስ አመሰራረቱ በሰዉና በሰነድ ማስረጃ  ተከሳሽ ላይ በሚገባ ያስረዳ በመሆኑ ፋርድ ቤቱ ተከሳሱን ተከላካይ ሲል ብይን ሰጥቷል ።

ይሁን እንጂ  ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ በቀን 14/07/2015 ዓ/ም ፋርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ጥፋተኛ ነዉ ሲል ዉሳኔ ተሰጥቷል ።

በጨረሻም  ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ተከራካሪዎች ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ና ማክበጃ ምክንያቶች ታሳቢ በማድረግ ፍርድ ቤቱ በቀን 15/072015 ዓ/ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ያርማል ሌላዉን የማህበረሰብ ክፍል ያስተምራል ያለዉን የ14 አመት ፅኑ እስራት ተከሳሽ እንዲቀጣ ውሳኔ  አስተላልፏል ።
የጣቁሳ ወረዳ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት
277 viewsAlemshet Miheretie, 10:42
ओपन / कमेंट
2023-03-27 21:04:21 ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር ወንጀል ላይ ትኩረት ያደረገ ውይይት ከባለድርሻ አካላት ተካሄደ። የአሚኮ የቴሌቪዥን የመጀመሪያውን ዜና ይከታተሉ።
https://www.youtube.com/live/PVDQYaZxaek?feature=share
409 viewsAlemshet Miheretie, 18:04
ओपन / कमेंट
2023-03-27 15:24:49
የአብክመ ፍትሕ ቢሮ በዮንሴፍ በጀትና ቴክኒክ ድጋፍ በኦን ላይን አማካኝነት በሴቶችና ሕፃናት የሚፈፀሙ የኃይል ጥቃት ወንጀሎች በተደራጀ አግባብ ለመከላከልና ምላሽ ለማሰጠት ከባህርዳርና ከጎንደር ከተማ ለተወጣጡ ባለድርሻ አካላት ከመጋቢት 14-16/2015ዓ.ም ለሶስት ቀናት በደብረታቦር ከተማ ስልጠና ተሰጠ።
456 viewsAlemshet Miheretie, edited  12:24
ओपन / कमेंट
2023-03-27 00:11:56 በሕግ አምላክ ምዕራፍ 1 ክፍል 3


507 viewsAlemshet Miheretie, 21:11
ओपन / कमेंट
2023-03-26 23:19:13 በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ዜጎችን ከእንግልት ለመታደግ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት መፍጠር  እንደሚያስፈልግ ተጠቆመ።

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 17/2015 ዓ.ም   ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ስደት ለመከላከል በፓዴት አስተባባሪነት የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በባሕር ዳር ከተማ ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ሥራ እና ስልጠና ቢሮ ምክትል ኀላፊ አቶ አወቀ ዘመነ፤ በሕገ ወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡ ዜጎችን ከእንግልት ለመታደግ ሕጋዊ የሥራ ስምሪት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

አቶ አወቀ በሕገ ወጥ መልኩ ሰዎችን የሚያዘዋውሩ ደላላዎች መበራከታቸው ወጣቶች በሀገራቸው ሠርተው የመለወጥ እድላቸውን እንዳይመለከቱ እና ለሕገወጥ ስደት እንዲጋለጡ እያደረገ ነው ብለዋል። አቶ አወቀ ወጣቶች ከሕገ ወጥ ስደት ይልቅ በየአካባቢያቸው ያሉ የሥራ እድሎችን መመልከት አለባቸው ብለዋል።

ሕጋዊ እና ቀልጣፋ የኾነ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት  አለመኖሩም አንዱ የሕገወጥ ስደት ምክንያት ስለመኾኑ አመላክተዋል። ወጣቶች በቂ ሙያ ይዘው በሕጋዊ መልኩ የውጭ ሀገር የሥራ  ስምሪት እንዲያገኙ ለማስቻል የክልሉ ሥራ እና ስልጠና ቢሮ በትኩረት እየተንቀሳቀሰ ስለመኾኑም አቶ አወቀ ገልጸዋል። በክልሉ 23 ሽህ 238 ወጣቶች በ80 ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ሥልጠና እየወሰዱ እንደሚገኙም አመላክተዋል። ከስልጠና በኋላም ሕጋዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የሀገር ውጭ የሥራ ስምሪት ትስስር እንደሚፈጠርላቸውም ገልጸዋል።

የፓዴት ደቡብ ወሎ ዞን ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ ወልዴ ጋሻው፤ ፓዴት ወጣቶች በሀገራቸው ሠርተው እንዲለወጡ ግንዛቤ የመፍጠር ሥራ እያከናወነ ነው ብለዋል። ከስደት የተመለሱ ወጣቶች ተመልሰው እንዲቋቋሙም ድጋፍ እንደሚደረግ አመላክተዋል።

አቶ ወልዴ ወጣቶች ሕገ ወጥ ስደትን መጠየፍ አለባቸው ብለዋል። ይልቁንም በሀገራቸው ከትንሽ ነገር ተነስተው በመሥራት የመለወጥ ልምድን ማዳበር አለባቸው ነው ያሉት።

ጥብቅ ትስስር ፈጥረው የሰዎችን ዝውውር የገንዘብ ምንጭ ያደረጉ ደላላዎችን ተጠያቂ የሚያደርግ ጠንካራ አሠራር አለመኖሩ አምራች የኾኑ የክልሉ ወጣቶች በስደት ምክንያት ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሚገኝም አቶ ወልዴ ገልጸዋል። 

የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ኀላፊ አያሌው አባተ (ዶ.ር) ሕገወጥ የሰዎችን ዝውውር ዓለም አቀፍ ወንጀል መኾኑን ገልጸዋል። ይህንን ወንጀል ለመከላከል በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት የቅንጅት አሠራር ያስፈልገዋል ብለዋል። እንደ አማራ ክልል ሕገ ወጥ የሰዎችን ዝውውር መከላከል ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት አለበት ብለዋል። ወንጀሉ ተከስቶ ሲገኝም በተቀናጀ መልኩ የእርምት እርምጃ እንደሚወሰድም  ገልጸዋል።

ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የወንጀሉ ተጎጅዎች ጭምር ፈቃደኛ ኾነው ስለሚፈጸም ለመከላከል የውስብስብነት ባህሪ ያለው ነው ብለዋል። ይሕንን ወንጀል በቅንጅት በመከላከል ዜጎችን ከሕገ ወጥ ስደት ለማዳን ለወጣቶች ሰፊ ግንዛቤ መፈጠር አለበትም ብለዋል። ሕዝቡ ወንጀለኞችን አሳልፍ የመስጠት ትብብር በማድረግ ዜጎችን ከዚህ አስከፊ ስደት የመከላከል ኀላፊነቱን እንዲወጣ ዶክተር አያሌው አሳስበዋል።

አሚኮ
509 viewsAlemshet Miheretie, 20:19
ओपन / कमेंट
2023-03-26 23:18:24
463 viewsAlemshet Miheretie, 20:18
ओपन / कमेंट
2023-03-25 22:14:02
በደብረ ማርቆስ ሪጅዮፖሊታን ከተማ ውስጥ ለሚገኙ 304 ለሚሆኑ የሚሊሻ አባላት የወንጀል ህግ እና ህገ መንግስትን እንዲሁም የጦር መሳሪያ ቁጥጥር እና አስተዳደርን /አዋጅ ቁጥር 1177/2012 / አስመልክቶ በደብረ ማርቆስ ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት አማካኝነት ከሚሊሻ መምሪያ ጋር በመተባበር ስልጠና ተሰጠ
570 viewsAlemshet Miheretie, 19:14
ओपन / कमेंट
2023-03-23 22:17:58
የአዊ ብሔ/አስ/ዞን ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኮሚቴው ተከፋፍሎ ድጋፍ ክትትል ያረገላቸው ወረዳዎች የመጣውን ለውጥ እና የጥር ወር ምዝገባ አፈጻጸጸም በቀን 12/07/15 የገመገመ ሲሆን ቀጣይ በትኩረት መፈጸም የሚገባቸው ጉዳዩች ላይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ውይይቱ ተጠናቋል ፡፡
119 viewsAlemshet Miheretie, 19:17
ओपन / कमेंट