Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 10

2023-03-16 20:56:55 በቋራ ወረዳ ሰዎችን በማገት 200,000 ብር  የተቀበለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ ።
ተከሳሸ ይታየው ጎራው ከልተያዘው ግብረ አበሩ እና በፀጥታ አካላት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሁለት ግለሰቦች ጋር በመሆን በቋራ ወረዳ በርሜል ፀበል ተጠምቀው ሲመለሱ የነበሩትን ግለሰቦች በማገት 200000(ሁለት መቶ ሺ ብር) የተቀበለ በመሆኑ በቋራ ወረዳ ፍ/ቤት የወረዳው ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶ ተከራክራል። ዐቃቤ ህንም ተከሳሸ ከግል ተበዳዮች የተቀበለውን 200,000 ብር እንደከፍል ከወንጀል  ክሰ ጋር አቅርቦ እንደተከራከረ የቋራ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አበጀ ገልፀውልናል።

      የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው  ተከሳሽ በ1996ዓ.ም ተደንግጎ የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣58(1)፣560(1)ለ እና 2(ሐ)ን በመተላለፍ የጦር መሳሪያ ከያዙ ግብረ አበሮች ጋር በመሆን የማይገባዉን ጥቅም ለማግኘት በማሠብ የካቲት 9ቀን 2015 ዓ/ም በግምት ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ቋራ ወረዳ ከበርሚል ፀበል ተጠምቀዉ ወደ ገለጉ ቀበለ በመመለሥ ላይ የነበሩትን የግል ተበዳዮች  2 (ሁለት) ግለሰቦች በማገት ከእያንዳንዳቸዉ ከአቶ ኢሳያስ ፍቃዱ 110,000 (አንድ መቶ አስር ሺ) ብር ከ አቶ ላይችሉ ብርሃኑ 90,000(ዘጠና ሺ) ብር በጠቅላላው  200,000(ሁለት መቶ ሺ) ብር በማሥከፈል የለቀቋቸዉ በመሆኑ በሰዉ መጥለፍ (ማገት) ወንጀል ተከሷል።
ተከሳሽም በዐ/ህግ በኩል የቀረበበትን ክስ  መፈፀሙን ያመነ በመሆኑ ጥፋተኛ ተብላል።

ፍ/ቤቱም ተከሳሹ የቀረበበትን ክሥ መቃወም ያልቻለና ጥፋተኛነቱን ያመነ በመሆኑ ተከሣሽን ያርማል መሠል ድርጊት ፈጻሚዎችን ያሥተምራል ብሎ ያመነበትን በቀን 27/6/2015 ዓ/ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት በተሠጠዉ ፍቅድ ሥልጣን በ6 (ስድስት )  አመት ፅኑ እሥራት እንዲሁም የግል ተበዳዮች ለማስለቀቅ የተከፈለውን ገንዘብ ለግል ተበዳዮች በወንጀል ህግ 101 መሰረት እንዲመለስ  በማለት ዉሣኔ ሠጥቷል።

ከላይ የክሰ ሒደት እንደተመለከትነው ተከሳሾች በእገታ ወንጀል ያገኙትን ጥቅም በወንጀል ክሱ ጋ አጣምሮ ከሰ ገንዘቡን ማስመለሰ ያልተመደና የተሻለ አሰራር በመሆኑ ሁሉም በዞኑ የሚገኙ ፍትህ ፅ/ቤት በወንጀል የተገኘ ንብረትን አጣርት በማስመለሰ ወንጀለኞች ያልተገባ ጥቅም ማምከን ይገባል።
ፖሊስም የወንጀል ምርመራ ሲያጣራ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን በማፈላለግ ከተጠርጣሪዎች የተገኘን ንብረትን በፍሬድ ቤት በማሳገድ የመዝገቡ አካል አድርጎ ለዐቃቤ ህግ እንዲልክ እንገልፃለን።

መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ  ነው

መጋቢት 07 ቀን 2015ዓም
396 viewsAlemshet Miheretie, 17:56
ओपन / कमेंट
2023-03-16 20:48:26
360 viewsAlemshet Miheretie, 17:48
ओपन / कमेंट
2023-03-16 20:48:26
379 viewsAlemshet Miheretie, 17:48
ओपन / कमेंट
2023-03-16 20:48:25 የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ከአጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የበጀት ድጋፍ ከወርልድ ቪዥን በመጠየቅና በማስፈቀድ ለ44 የቀበሌ ስራ አስኪያጅ ለሃይማኖት አባቶች ለወረዳው ወሳኝ ኩነት ኮሚቴና ለ1 ቀበሌ ጤና ኤክስቴንሽን በድምሩ ለ54 ተሳታፊዎች ከ06/07/2015 ዓ/ም እስከ 07/07/2015 ዓ/ም ድረስ ለ2 ቀን ያህል በ4ቱም ከወሳኝ ኩነት ምዝገባና ሰርፍ ትኬት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ስልጠና እና ስልጠናዊ ግምገማ በማድረግ በቀጣይ አሁን ካለንበት ዝቅተኛ አፈፃፀም መውጣትና የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ እንደሚገባን ከተሳፊዎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሷል::
386 viewsAlemshet Miheretie, 17:48
ओपन / कमेंट
2023-03-16 11:57:29 የችሎት ዘገባ

ተከሳሹ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 12:00 ሰአት አካባቢ በእንሳሮ ወረዳ ገዙዋሻ ዳሎታ ቀበሌ ልዪ ቦታው ገለታእናት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ የግል ተበዳይ አቶ ሸዋረገድ እምይ እና አቶ ፍቃዱ ተሾመ የሆኑ አንድ ነጭ በሬ ግምቱ 55000(ሀምሳ አምስት ሺህ ብር) የሚያወጣ በሬ እና አንድ ዳልቻ ቦራ በሬ ግምቱ 40000(አርባ ሺህ ብር) የሚያወጡ በሬዎች ከበረት የጠፉ በመሆኑ በፍለጋ ላይ እያሉ ተከሳሹ በሬዎቹን እየነዳ በመምጣት ላይ እያለ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከለሊቱ 7:30 በመርሀቤቴ ወረዳ ጌብዘሞይ ቀበሌ በቀበሌው የጸጥታ ሀይሎች የተያዘ በመሆኑ እና የሰረቀውም ንብረት ከሁለት የተለያዩ ገለሰቦች ላይ በመሆኑ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ 669(3)(ለ) ስር የተመለከተውን በመተላለፉ ሁለት ክስ ቀርቦበት ችሎቱም በሁለቱም ክሶች ተከላከል ብሎት ያቀረባቸው የመከላከያ ምስክሮች የዐ/ህግን ማስረጃዎች ማስተባበል ያልቻለ በመሆኑ በተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ ጥፋተኛ ተብሎአል።
ዐ/ህግም ተከሳሹ ከዚህ በፊት ሪከርድ ያለበት መሆኑን በማክበጃነት ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽም የማቅለያ ሀሳቦችን አቅርቦ ፍ/ቤቱ የሁለቱንም ቅጣት ደምሮ ተከሳሹን ያርማል እንዲሁም ሕብረተሰቡን ያስተምራል ያለውን ተከሳሹን በ 12 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጥቶታል።
502 viewsAlemshet Miheretie, 08:57
ओपन / कमेंट
2023-03-11 23:07:05
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የአመራር ክህሎት እና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ትኩረት አድርጎ በሁለት ዙር ከየካቲት 24-25 /2015ዓ.ም እና መጋቢት 1-2/2015ዓ.ም በጎንደር እና በባህር ዳር ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
ይህ ስልጠና በስኬት እንዲጠናቀቅ ጊዜያቸውን መስዋዕት አድርገው በተከታታይ ስልጠናውን ለሰጡት አማካሪ፣አሰልጠኝ፣ተመራማሪ ዶክተር ተመስገን ዳኜ እንዲሁም የአማራ ክልል የፍትሕ ቢሮ የፍትሕ ስርዓት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው የቴክኒክ እና በጀት ድጋፍ ላደረጉልን በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ኃላፊ ሚስተር ዴቪድ ዲ ጃይልስ፣ምክትል ኃላፊ አቶ ማንደፍሮት በላይ በአብክመ ፍትሕ ቢሮ ስም የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አያሌው አባተ እጂ ዕውቅና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡
218 viewsAlemshet Miheretie, edited  20:07
ओपन / कमेंट
2023-03-11 21:29:00
የአብክመ  ፍትሕ ቢሮ  ከአማራ ክልል ጠበቆች ማሕበር  ጋር  በመተባበር ከባሕር ዳር እና በአካባቢው ከሚገኙ ከጠበቆች እና ከሚመለከታቸው አጋር አካለት ጋር  ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2015ዓ.ም የምክክር መድረክ በባሕርዳር ከተማ አካሄደ፡፡
በክልላችን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የፍትሕ ሥርዓቱን መሠረታዊ ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ጠበቆች፣ከፍትሕ ተቋማት ጋር  የጋራ ምክክር መድረክ  ማዘገጀት ለተገልጋዮች ፤ለመንግስት እና ለራሳቸው ለጠበቆች  አስፈላጊ በመሆኑ፣  በፍትሕ ተቋማት  የሚስተዋሉ ጉድለቶች እና በጠበቆች የሚስተዋሉ የሰነ-ምግባር ችግሮችን በመቀራረብ  ወይይት ተደርጎባቸው ጠበቆች ምልካም ስነ-ምግባር  ተላበሰው  በመስራት ለሕግ የበላይነት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያበረክቱ በማሰብ እና በአጥፊ ጠበቆች ላይ  ተጠያቂነቱ እንዲኖር፣ በክልሉ ውስጥ በየደረጃው ባሉ ፍትሕ ተቋማት የሚሰጡዋቸው ውሳኔዎች  ፈጣን ፣ ፍትሃዊ እና ተገማች ሁነው ለህብረተሰቡ የተሸለ አገልግሎት  እዲሰጥ ያመች ዘንድ፤  ለፍትህ ስርአቱ አጋዥ ከሆኑት ጠበቆች ጋር በመወያየት በክልሉ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣  የፍትሕ ሥርዓቱን መሠረታዊ ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ  ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በማሰብ  የተዘጋጀ  የምክክር መድረክ ነው፡፡
281 viewsAlemshet Miheretie, edited  18:29
ओपन / कमेंट
2023-03-10 21:25:55 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትህ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትህ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የአመራር ክህሎት እና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

የስልጠናው ዋና ዓላማ የተሻሻለ የህግ ሥርዓት እንዲኖር ማስቻል እና የፍትሕ ተቋማት በሙያ ተመስርተው እና ሕግን መሰረት አድርገው እንዲሰሩ ለማድረግ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል።

በስልጠና መድረኩ ላይ የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዝግአለ ገበየሁን ጨምሮ የዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ምክትል ኃላፊ አቶ ማንደፍሮ በላይ፣ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የምድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪዎች፣ የዞን ፍትሕ መምሪያ ኃላፊዎች፣የሪጂኦ ፖሊታን ፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣የሂደት መሪዎች፣ዐቃቤያነ ሕግ በስልጠናው ታድመዋል።

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዝግአለ ገበየሁ የስልጠናውን ዋና ዓላማ አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው በንግግራቸው ወቅት ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትህ ተግባራት በኢትዮጵያ ባለፉት አራት ዓመታት ውስጥ በሀገራችን የፍትህ ሥርዓቱን ለማዘመን ከሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በፌዴራል ፍትህ ሚንስቴር እና ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች እንዲሁም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የፍትህ ተቋማት ውስጥ በቴክኖሎጂ የታገዙ ሰነዶችን በማዘጋጀት፣ ልዩ ልዩ ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ፣ ሥልጠናዎችን በመስጠት እና የፋይናንስ ድጋፍ ጭምር በማድረግ ለፍትህ ስርዓቱ መዘመን ትልቅ አስተዋፅዖ ማበርከቱን ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በተቋቋመው የአስፈፃሚ አካላት መመሪያ 280/2014 ዓ.ም መሰረት ቢሮው የአደረጃጀትና የአሰራር ማኑዋል ክለሳ ማካሄዱን ገልፀዋል። በዚህ ክለሳ መሰረትም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ በርካታ የፍትህ አመራሮችን አወዳድሮ መመደብ መቻሉን ጨመረው ገልፀዋል።

በመሆኑም የአዲሱን አመራር ክህሎት ለማዳበር እና የአመራር ክፍተቶችን ለመሙላት ተከታታይ ሥልጠናዎች ሲሰጡ መቆየታቸውን ገልፀው የዛሬው ሥልጠናም በዕውቀት እና ክህሎት የዳበረ አመራር በመፍጠር በአገልግሎቱ ህዝብን ማርካት የሚችል ብቁ መሪ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን አክለው ተናግረዋል።

የዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትህ ተግባራት በኢትዮጵያ ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ማንደፍሮ በላይ በበኩላቸው በ2010 ዓ.ም የመንግስት ለውጥ ከተደረገ በኋላ በፍትሕ ተግባራት ዙሪያ በርካታ ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን ገልፀዋል።

ምክትል ኃላፊው አያይዘውም ፕሮጀክቱ የሀገሪቱን የሕግ ተቋማት ለማጠናከር፣ የትምህርት ካሪኩለም እና ጥራት፣ የህግ ሪፎርም የቴክኒክ ሥራ እና ማህበረሰብ ተኮር ተግባራት ላይ በርካታ ሥራዎችን በመስራት የመንግስትን ወጭ በመሸፈን ትልቅ እገዛ ሲያደርግ መቆየቱን ገልፀዋል።

መመሪያዎችን እና አዋጆችን በተመለከተ ቴክኒካዊ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አንስተው የሲቪል እና የሚዲያ ተቋማትን ጭምር ለማጠናከር ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን አብራርተዋል።

የዛሬው ሥልጠና የዚህ አካል መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞቹ ስለ ሥራ አመራር ፅንሰ ሃሳብ፣ ስለ አመራርነት ጥበብ፣ ስለ አመራር ማይንድ ሴት፣ ስለ ለውጥ ተኮር የአመራር ዘዴ እና የረጅም ጊዜ ዕቅድ መምራት ጥበብ ስልጠና እንደሚሰጣቸውም ተናግረዋል። በቀጣይ ፕሮጀክቱ በቆይታው ያመጣው ውጤት በገለልተኛ አካል እንደሚገመገም እና አስተያዬት እንደሚሰጥበትም ጨምረው ተናግረዋል።

አመራሮች በየጊዜው በቴክኒክ እና በክህሎት እራሳቸውን ማዳበር ስለሚገባቸው እንዲሁም አንድ አመራር ወደ መሪነት ከመምጣቱ በፊት ብቁ ሆኖ መገኘት ስላለበት በፌዴራል እና በክልሎች ደረጃ በቂ እና ቋሚ የአመራር ማሰልጠኛ ተቋም መኖር እንደሚገባውም አስተያዬት ሰጥተዋል።
APP
426 viewsAlemshet Miheretie, 18:25
ओपन / कमेंट
2023-03-10 21:13:48
375 viewsAlemshet Miheretie, 18:13
ओपन / कमेंट
2023-03-09 20:12:19
እኔም የእህቴ ጠባቂ ነኝ በሚል መሪ ቃል"በአለም አቀፍ ደረጃ ለ112ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ47ኛ ጊዜ በሚከበረው መድረክ ለሴቶች ህፃናት የፍትህ ተቋም በሚሰጠው አገልግሎት ወ/ሮ ካሳየ እንግዳ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
167 viewsAlemshet Miheretie, edited  17:12
ओपन / कमेंट