Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ  ፍትሕ ቢሮ  ከአማራ ክልል ጠበቆች ማሕበር  ጋር  በመተባበር ከባሕር ዳር እና በአካባቢ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የአብክመ  ፍትሕ ቢሮ  ከአማራ ክልል ጠበቆች ማሕበር  ጋር  በመተባበር ከባሕር ዳር እና በአካባቢው ከሚገኙ ከጠበቆች እና ከሚመለከታቸው አጋር አካለት ጋር  ዛሬ መጋቢት 2 ቀን 2015ዓ.ም የምክክር መድረክ በባሕርዳር ከተማ አካሄደ፡፡
በክልላችን የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥና የፍትሕ ሥርዓቱን መሠረታዊ ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ጠበቆች፣ከፍትሕ ተቋማት ጋር  የጋራ ምክክር መድረክ  ማዘገጀት ለተገልጋዮች ፤ለመንግስት እና ለራሳቸው ለጠበቆች  አስፈላጊ በመሆኑ፣  በፍትሕ ተቋማት  የሚስተዋሉ ጉድለቶች እና በጠበቆች የሚስተዋሉ የሰነ-ምግባር ችግሮችን በመቀራረብ  ወይይት ተደርጎባቸው ጠበቆች ምልካም ስነ-ምግባር  ተላበሰው  በመስራት ለሕግ የበላይነት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጾ እንዲያበረክቱ በማሰብ እና በአጥፊ ጠበቆች ላይ  ተጠያቂነቱ እንዲኖር፣ በክልሉ ውስጥ በየደረጃው ባሉ ፍትሕ ተቋማት የሚሰጡዋቸው ውሳኔዎች  ፈጣን ፣ ፍትሃዊ እና ተገማች ሁነው ለህብረተሰቡ የተሸለ አገልግሎት  እዲሰጥ ያመች ዘንድ፤  ለፍትህ ስርአቱ አጋዥ ከሆኑት ጠበቆች ጋር በመወያየት በክልሉ ውስጥ የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ፣  የፍትሕ ሥርዓቱን መሠረታዊ ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ  ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር በማሰብ  የተዘጋጀ  የምክክር መድረክ ነው፡፡