Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች የአመራር ክህሎት እና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ትኩረት አድርጎ በሁለት ዙር ከየካቲት 24-25 /2015ዓ.ም እና መጋቢት 1-2/2015ዓ.ም በጎንደር እና በባህር ዳር ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ፡፡
ይህ ስልጠና በስኬት እንዲጠናቀቅ ጊዜያቸውን መስዋዕት አድርገው በተከታታይ ስልጠናውን ለሰጡት አማካሪ፣አሰልጠኝ፣ተመራማሪ ዶክተር ተመስገን ዳኜ እንዲሁም የአማራ ክልል የፍትሕ ቢሮ የፍትሕ ስርዓት የተሻለ አፈፃፀም እንዲኖረው የቴክኒክ እና በጀት ድጋፍ ላደረጉልን በዩ ኤስ ኤ አይ ዲ የፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ኃላፊ ሚስተር ዴቪድ ዲ ጃይልስ፣ምክትል ኃላፊ አቶ ማንደፍሮት በላይ በአብክመ ፍትሕ ቢሮ ስም የቢሮው ምክትል ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አያሌው አባተ እጂ ዕውቅና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል፡፡