Get Mystery Box with random crypto!

የችሎት ዘገባ ተከሳሹ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የችሎት ዘገባ

ተከሳሹ የማይገባውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 12:00 ሰአት አካባቢ በእንሳሮ ወረዳ ገዙዋሻ ዳሎታ ቀበሌ ልዪ ቦታው ገለታእናት እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ የግል ተበዳይ አቶ ሸዋረገድ እምይ እና አቶ ፍቃዱ ተሾመ የሆኑ አንድ ነጭ በሬ ግምቱ 55000(ሀምሳ አምስት ሺህ ብር) የሚያወጣ በሬ እና አንድ ዳልቻ ቦራ በሬ ግምቱ 40000(አርባ ሺህ ብር) የሚያወጡ በሬዎች ከበረት የጠፉ በመሆኑ በፍለጋ ላይ እያሉ ተከሳሹ በሬዎቹን እየነዳ በመምጣት ላይ እያለ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከለሊቱ 7:30 በመርሀቤቴ ወረዳ ጌብዘሞይ ቀበሌ በቀበሌው የጸጥታ ሀይሎች የተያዘ በመሆኑ እና የሰረቀውም ንብረት ከሁለት የተለያዩ ገለሰቦች ላይ በመሆኑ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ 669(3)(ለ) ስር የተመለከተውን በመተላለፉ ሁለት ክስ ቀርቦበት ችሎቱም በሁለቱም ክሶች ተከላከል ብሎት ያቀረባቸው የመከላከያ ምስክሮች የዐ/ህግን ማስረጃዎች ማስተባበል ያልቻለ በመሆኑ በተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ ጥፋተኛ ተብሎአል።
ዐ/ህግም ተከሳሹ ከዚህ በፊት ሪከርድ ያለበት መሆኑን በማክበጃነት ያቀረበ ሲሆን ተከሳሽም የማቅለያ ሀሳቦችን አቅርቦ ፍ/ቤቱ የሁለቱንም ቅጣት ደምሮ ተከሳሹን ያርማል እንዲሁም ሕብረተሰቡን ያስተምራል ያለውን ተከሳሹን በ 12 ዓመት ጽኑ እስራት ቀጥቶታል።