Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 7

2023-04-03 11:28:37 ካዳስተር ማለት ምን ማለት ነው?

ካዳስተር ማለት መሬት ይዞታን መሰረት ያደረገ የመሬት መረጃ ሥርዓት ሲሆን የሚደራጁት መረጃዎችም በዋናነት ሁለት ዓይነት ናቸው፡፡ ይኸውም የካርታ መረጃ (spatial data) የይዞታውን መገኛ ቦታ፣ ወሰኑን፣ ስፋቱንና ቅርፁን፣ አጎራባች ይዞታዎችን እና አዋሳኝ መንገዶችን የሚያሳይ ሲሆን ሌላኛው ገላጭ መረጃ (non-spatial data) በመባል የሚታወቀው የባለይዞታውን ማንነት (ስም፣ አድራሻ፣ ጾታ፣ የጋብቻ ሁኔታ፣ ወዘተ.)፣ በይዞታው ላይ ያለው መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት፣ የቦታው አገልግሎትና ደረጃ፣ ወዘተ… እንደ ካዳስተር ዓይነቱ ተዘርዝረው የሚያዙ መረጃዎችን ያካትታል፡፡ እነዚህ ሁለት የመረጃ ዓይነቶችም በልዩ የይዞታ መለያ ኮድ እንዲገናኙ ይደረጋል፡፡

ካዳስተር በሦስት ዓይነት ይከፈላል፡- አንደኛው ህጋዊ ካዳስተር ሲሆን ለእያንዳንዱ ህጋዊ ወሰን ለተለየለት ይዞታ፣ የይዞታ መብት፣ ክልከላና ኃላፊነት የሚያመለክት መረጃ ከይዞታው ካርታ ጋር አጣምሮ የያዘ ወቅታዊ የመሬት ይዞታ መረጃ ሥርዓት ሲሆን አስፈላጊነቱም ዬትኛው ይዞታ በማንና በምን አግባብ ተይዟል የሚለውን በማጣራት የባለይዞታውን የይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ ነው፡፡ ሁለተኛው ዓይነት ፊስካል ካዳስተር ሲሆን በይዞታው ላይ ስላረፈው ቋሚ ንብረት ዝርዝር መረጃ እና የመሬቱን ወቅታዊ ግምት ከይዞታው ካርታ ጋር የሚይዝ ሆኖ ለቦታና ለንብረት ግብር ክፍያ የሚያገለግል ሥርዓት ነው፡፡ ሦስተኛው ዓይነት ካዳስተር ሁለገብ/ሁሉን አቀፍ ካዳስተር/ የሚባለው በሁለቱ የካዳስተር ዓይነቶች የተገለፁትን መረጃዎች የሚይዝ ሆኖ በተጨማሪም የመሰረተ ልማት፣ የአካባቢ ጥበቃ እና ሌሎች መረጃዎችን እና ካርታን አካቶ የሚይዝ የመረጃ ሥርዓት ነው፡፡

የካዳስተር ሥርዓት በመገንባት ሂደት በርካታ ልምድ ያላቸውና ብዙ ርቀት የሄዱ አገሮች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በዚህ የግንባታ ሂደት እያንዳንዱ አገር ከራሱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር አጀማመሩና አካሄዱ የተለያየ ነው፡፡ አንዳንድ ሀገሮች ከፊስካል ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የሄዱ አሉ ለምሳሌ ፈረንሳይ፤ ሌሎች ደግሞ ከህጋዊ ካዳስተር ጀምረው ወደ ሁለገብ የካዳስተር ሥርዓት የተሸጋገሩበት ሁኔታም አለ ለምሳሌ ኔዘርላንድ፡፡ በእኛ አገር ደረጃም ከዚህ ቀደም በከተማ ደረጃ ሥርዓቱን ለመዘርጋት በርካታ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ የተሞከሩትም ሁለገብ ካዳስተርን በመዘርጋት ነበር ሆኖም ግን የሚፈለገውን ውጤት ሊያመጣና የሥርዓቱን ዘለቄታዊነት የሚያረጋግጥ ሊሆን አልቻለም፡፡

በመሆኑም በቅድሚያ ባለይዞታውን ተጠቃሚ የሚያደርገው ከተማ አስተዳደሮችም መሬታቸውን ቆጥረው ሊያውቁ የሚችሉበትን የህጋዊ ካዳስተር በመዘርጋት በመቀጠልም የፊስካል ካዳስተር ብሎም ወደ ሁለገብ ካዳስተር የሚያድግ ሥርዓት መዘርጋቱ ሥርዓቱን ቀጣይ ለማድረግ የሚያስችል በመሆኑ ተመርጧል፡፡

በዚህ ሂደት የካርታው መረጃ አንድ ጊዜ የሚዘጋጅ ሲሆን ለውጥን ተከትሎ ወቅታዊ ማድረግ የሚያስፈልግ ሆኖ ሁሉም የካዳስተር ዓይነት መሰረት የሚያደርገው በህጋዊ ካዳስተር የተዘጋጀውን የካዳስተር ካርታ ነው:: ሌሎች መረጃዎች ተደማሪ እየተደረጉ ወደ ሁለገብ ካዳስተር ሥርዓት የሚያድግ ይሆናል፡፡
417 viewsAlemshet Miheretie, 08:28
ओपन / कमेंट
2023-04-01 10:32:39
547 viewsAlemshet Miheretie, 07:32
ओपन / कमेंट
2023-04-01 10:32:39
521 viewsAlemshet Miheretie, 07:32
ओपन / कमेंट
2023-04-01 10:32:38 በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አማካኝነት ውጤታማ የሆነውና ግድያን ለማስቆም እተሰጠ የሚገኘው የንቃተ ህግ ግንዛቤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

ተቋሙ እስካሁን ጠቃሚ ጥናት በመንደፍ በወረዳው ጯሂት ከተማን ጨምሮ ስምራ፣ ጀንዳ፣ መስቀለ ክርስቶስ፣ ተዘባ፣ ጉራንዲ፣ ማንጌ፣ ቸንከላ፣ ዳህና ዋዋ እና ሌሎች ቀበሌዎች ላይ በአካባቢው እየተከሰተ ስላለው ግድያ ግንዛቤ ሰጥቷል።

በዛሬው ዕለት በዳህና ዋዋ ቀበሌ ተገኝተው ለነዋሪዎች ግንዛቤ የፈጠሩት የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲያቆን ደርባባው ድንቄ በወረዳው ግድያን ለማስቆም ጥናት በማጥናት ወደ ስራ መግባታቸውን አስረድተዋል።

ጥናቱ የእርስ በርስ ግድያን በማስቆም ደም የተጋቡትን ገና ከጅምሮ ወደ እርቅ እያመጣ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ስካር፣ ስርቆት፣ አላስፈላጊ ግጭት፣ እርኩስ ቅናት፣የቆየ ደም ምለሳ እና ሌሎች የግድያ መንስኤ መሆናቸዉን አስረድተዋል።

በመሆኑም ያሉት የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊው ዲያቆን ደርባባው ድንቄ ሰው መግደል በመሬት በህግ፤ በሰማይ ደግሞ ሀጢያት መሆኑን እና የሚያስጠይቅ እንደሆነ ገልፀዋል።

ይህን ለማስቀረት እና በወረዳው ማህበረሰብ ግድያን በእርቅ ለመሻር ሰላም ለመፍጠርም ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ስራ መግባታቸውን ኃላፊው አስረድተዋል።

በሌላ በኩል በንቃተ ህጉ ግንዛቤ ፈጠራ የተገኙት ሊቀ ጠበብት መንግስቱ ተገኘ ሰው መግደል ሰይጣናዊ ተግባር መሆኑን ገልፀው ግድያ ለማስቀረትም ለወረዳው ህዝብ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሆኑን አስረድተዋል።

ሊቀ ጠበብቱ ለቤተሰቦቻችን በቀል ማውረስ የለብነም ያሉ ሲሆን ግድያን በእርቅ ለማስቆም እየሰራን ነው ብለዋል።

እንደ አጠቃላይ የንቃተ ህግ የግንዛቤ ስራው የሚቀጥል መሆኑ እና እርስ በእርስ የተጋደሉ ወገኖቻችን በማስታረቅ ሰላም በመፍጠር በተሰጠን የተፈጥሮ ጠጋ ደምቢያን የምናለማ መሆኑን ነው በመድረኩ የተመላከተው።

በጌትነት ተችሎ
መጋቢት 21/2015 ዓ/ም
491 viewsAlemshet Miheretie, 07:32
ओपन / कमेंट
2023-03-31 21:47:07 የወሎ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የንቃተ ሕግ ግንዛቤ ሥራ



509 viewsAlemshet Miheretie, 18:47
ओपन / कमेंट
2023-03-31 11:27:15
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ከዮንሴፍና ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በሚገኙ ሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀም የኃይል ጥቃትን ለመከላከልና ለመስጠት በተቋቋመ የአንድ የአንድ ማዕከል ኘሮቶኮል፣የፓሊስ ጣቢያ እና ማረሚያ ቤት ጉብኝት ማንዋል በሚመለከት ጉዳዮ ከሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት ግንዛቤ ለማስጨበጥ ዛሬ መጋቢት 22 ቀን 2015ዓ.ም የውይይት መድረክ እያካሄደ ነው።
618 viewsAlemshet Miheretie, edited  08:27
ओपन / कमेंट
2023-03-29 21:34:42
#በአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ላይ በደን አዋጅ የተከለከለ ተግባር የፈፀ ተከሳሽ በእስራት እና በገንዘብ ተቀጣ
******
ከሳሽ፦ዐ/ህግተከሳሽ፦አብዱ ተበጀ አድራሻ ቋራ ወረዳ መሀዲድ ቀበሌ ተከሳሽ የኢፌድሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1)(ሀ)እና 1ኛ.የደን ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 አንቀፅ 25(4)(ረ)እና አንቀፅ 26(1)ን እና 2ኛ.የደን ልማት ጥበቃ እና አጠቃቀም አዋጅ ቁጥር 1065/2010 አንቀፅ 25(4)(ሀ) እና አንቀፅ 26(8)ን በመተላለፍ በፈፀማቸዉ ሁለት ወንጀሎች ተከሷል።

ተከሳሽ ሌሎች ካልተያዙ ግብረ አበሮች ጋር በመሆን መጋቢት 7/2015 ዓ/ም በግምት ከጥዋቱ 3:00 ሳአት ቋራ ወረዳ መሀዲድ ቀበሌ ከአልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ዉስጥ ልዩ ቦታዉ ስሁል እየተባለ ከሚጠራዉ በህገወጥ መንገድ በመግባት ከፓርኩ ዉስጥ በግምት 20 ኪሎ ግራም ማር እና 82 የወንበላ ዛፍ የቆረጠ በመሆኑ በፈፀመዉ በደን አዋጅ የተከለከለ ተግባር በሁለት ወንጀሎች ተከሷል።

ተከሳሽም ድርጊቱን መፈፀሙን ያመነ እና የቀረበበትን ክስ ያልተቃወመ በመሆኑ ጥፋተኛ ተብሏን።

ፍ/ቤቱም ዐ/ህግ ያቀረበዉን ክስ በመመርመር እና ተከሳሽም ድርጊቱን መፈፀሙን ያመነ በመሆኑ 4(አራት) የቅጣት ማቅለያዎችን እና 1(አንድ) የቅጣት ማክበጃን በመያዝ በቀን 19/07/12015ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽን ያርማል መሰል ድርጊት ፈፃሚዎችን ያስተምራል ብሎ ያመነበትን በተሰጠዉ ፍቅድ ስልጣን በ5 (አምስት)አመት ፅኑ እስራት እና በ1,500 (አንድ ሺ አምስት መቶ)ብር ይቀጣ ሲል ዉሳኔ ሰጥቷል።

/ቋራ ወረዳ ፍ/ቤት/
250 viewsAlemshet Miheretie, 18:34
ओपन / कमेंट
2023-03-29 21:17:04
256 viewsAlemshet Miheretie, 18:17
ओपन / कमेंट
2023-03-29 21:17:03 የባንጃ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በመከላከልና ተፈፅሞ ሲገኝ ምላሽ በመስጠት ረገድ ላደረገው ከፍተኛ አሰተዋፆኦ PLAN INTERNATIONAL ከተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት የምስገና ምስክር ወረቀት እና ከፍተኛ ሽልማት ተበርክቶልናል::
252 viewsAlemshet Miheretie, 18:17
ओपन / कमेंट
2023-03-29 14:00:10 የፍ/ሰላም ከተማ ወ/ፍ/ቤት እና የፍ/ሰላም ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት  መጋቢት 18/2015 ዓ.ም ውይይት አደረጉ። በውይይቱም ፦
ፍትህን ለማስፈን እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ፍርድ ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት እንዴት  ተባብረን በመስራት የማህበረሰቡን ችግሮች መፍታት የሚቻለው?  የሚለውን የመነሻ ሀሳብ በማድረግ ሰፋ ያሉ ሀሳቦች በዐ/ህጎች እና በዳኞች የተነሱ ሲሆን በተለይም ህገ ወጥ የመሬት ወረራን መከላከልን በተመለከተ፣ የእግድ ትዕዛዝ አሰጣጥን በተመለከተ፣ የማስረጃ አቀራረብን በተመለከተ ፣ የቀጠሮ አሰጣጥን፣  ከመሬት ጋር የተያያዙ  ክሶች (ሁከት ይወገድልኝ) የዕርቅ ውል ማፅደቅን በተመለከተ እና ሌሎችም ሀሳቦች ሰፋ ባለመልኩ በሁለቱም በኩል ተነስተው  ምላሽ ተሰጦባቸዋል::
 በማጠቃለያውም የፍ/ቤቱ ሰብሳቢ ዳኛ እና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊው በውይይቱ በተነሱት ሀሳቦች ላይ ምላሽ ሰጥተው በቀጣይም ችግሮችን በመለየት እና የጋራ ውይይቶችን በማድረግ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ ማህበረሰቡን ፍትሀዊ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ተባብረን እና ተጋግዘን በመስራት ችግሮች መፍታት ያለባቸው መሆኑን በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል::
348 viewsAlemshet Miheretie, 11:00
ओपन / कमेंट