Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 9

2023-03-20 16:18:26
ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ ፎካል ፐርሰኖች በሪፖርት ቅጾች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡ ህጻናት ጋብቻ እና በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃት ወንጀሎችን በመከላከልና ምላሽ በመስጠት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) አሳሰቡ፡፡ምክትል ቢሮ ኃላፊው በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃት ወንጀሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያስከትሉ በመሆኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በተመሳሳይም በፍልሰት ተጎጅ ለሆኑ ዜጎች የሚደረግ የህግ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሚሰሩ ስራዎች መረጃዎችን በአግባቡ በመመዝገብ እና በመያዝ ሪፖርት ማድረግ ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያሌው አባተ (ዶ/ር) ይህን ያሉት ከክልል ፍትህ ቢሮ ለሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች፣ዐቃብያነ ህጎች እንዲሁም ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ ፎካል ፐርሰኖች በሪፖርት ቅጾች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው መሻሻል ይገባቸዋል ያሏቸውን በማንሳት እና በመወያት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡
475 viewsAlemshet Miheretie, edited  13:18
ओपन / कमेंट
2023-03-20 14:57:57 የደምበጫ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ከአጋር አካላት ጋር በተለይም ከደምበጫ ወረዳ ፍ/ቤት ከደምበጫ ዙ/ወ/ፓሊስ ጽ/ቤት እና ከደምበጫ/ከ/አሰ/ ፓሊስ ጽ/ቤት የሁሉንም የማናጅመንት አባላት ባካተተ መልኩ ውይይት ማድረግ የቻለ ሲሆንና ፦ የመወያያ አጀንዳዎችም፡ 1ኛ የችሎት አቀራርብን በተመለከተ 2ኛየሰባዊ መብት አየያዝን በተመለከተ 3ኛፓሊስ በወንጀል ጠርጥሪያችሏለሁ ብሎ በህግ ቁጥጥር ስር የሚያውላቸውን የተጠረጠሩበትን ወንጀል ከማሳወቅ አኳያ እና በ48 ስዓት ውስጥ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ከማድረግ አኳያ 4ኛ የተከሳሽ እና የምስክር አቀራርብን በተመለከተ አንስተን የተወያየን ሲሆን በውይይቱ የተነሱት ሀሳቦችም ፦ በደምበጫ ከተማ አስተዳድር ፓሊስ የተነሳው እና መፍትሔነው ብለው ያስቀመጡት የችሎት አቀራርብ ፓሊስን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ዙሪያነበር የሚያቀርብ አሁን በምን አግባብነው እኛን አቅርቡ የምትሉን የሰባዊ መብትን በተመለከተ ፍፁምነን ማለት ብንችልም በተቻለ መጠን የሰባዊ መብት አየያዝን ባከበረ መልኩ እየሰራንነው። የተከሳሽ ምስክር አቀራርብን በተመለከተ ከመቸውም በላይ እየሰራን ነው ወደፊትም ጠክረን እንሰራለን ብለዋል። የደም/ዙ/ወ/ ፓሊስ በበኩሉ ከዚህ ቀደምም ቢሆን የችሎት አቀራርብም ሆነ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ጣቢያ የራሳችሁ እዲኖራችሁ ተነጋግረናል ነገርግን በነበረው ሀገራዊ ሁኔታ እና ትሰሩ እንደሆነ ብለን ታገሰናችሏል ካሁን በሏላ አንችልም የሚል ሀሳብ ሰጠዋል። የሰባዊ መብት አየያዝ ብዙም ችግር የለብንም ወደፊትም ከዚህ የተሻለ እናደርገዋለን ብለዋል። የተከሳሽ ምስክር አቀራርብ ባለፈው ስድስት ወር አንድ መዝገብ ብቻነው የተዘጋብን ወደፊት ያንንም እናስከፍታለን ሌላም እደይዘጋብን ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል። በፍ/ቤት በኩል የተነሳው ፦ ችሎት አቀራርብን በተመለከተ በጣም እየተቸገርን ስለሆነ ሁለታችሁ ተነጋግራችሁ መፍትሔ አስቀምጡ ይህን የማታደርጉ ከሆነ የምንሰጠውን ትዕዛዝ ለማስከበር እንገደዳለን ብለዋል አልፎ አልፎ ቢሆንም ማረሚያቤት እድትወስዱ ትዛዝ ሰጠን ጣቢያ ታቆያላችሁ ይህም መታረም አለበት ብለዋል። ዐ/ህግ በበኩላቸው ከመቸውም በተሻለ ከአጋር አካላት ማለትም ከሁለቱም ፓሊስ እናፍ/ቤትጋር ስራን መሰረት ያደረገ መልካም ግንኝነት አለን ሆኖም ግን ጣቢያላይ ማቆየት ፣ በ48 ስዓት ውስጥ ፍ/ቤት ያለ ማቅረብ ፣ የልፎአልፎ ቢሆንም የሰባዊ መብት አየያዝ ችግር በሁለቱም በኩል በተለይ ከተማ ፓሊስላይ ጉላ ብሎ በሚታይ መልኩ መኖር እና የተከሳሽ ምስክር አቀራርብም ተደጋጋሚ ቀጠሮ እያስጠየቃችሁን ስለሆነ ጠንክራችሁ ብሰሩ የሚል ሀሳብ ሰጠዋል። በማጠቃለያ ሀሳብ ላይ የተስማማንባቸው ፦ ዙሪያ ፓሊስ እደተዚህ ቀደማችሁ በመቻቻል እና በመተጋገዝ እስከዚህ ዓመት መጨረሻ የችሎት አቀራርብንም ሆነ ጣቢያውን ተባበሯቸው ከተሞችም በተለይ ከባድ ወንጀል የሚጠረጠሩትን እና የጊዜ ቀጠሮ የሚያስፈልጋቸውን ዋስትናን በተመለከተ እናተ አቅርቡ በሌላ በኩል ለተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበትን ወንጀል አሳውቁ እንዲሁም የሰባዊ መብት አየያዝን በተመለከተ ከዚህ በተሻለ እንዲሆን ስለምንፈልግ እራሳችሁን በማየት አስተካክሉ ፡ ተከሳሽ ምስክር አቀራርብን በተመለከተ ጥሩነው ግን ስጋቶች ስለአሉ ጠከር ብላችሁ ስሩ በፍ/ቤት በኩል የዋስትና የሚያዘው /እንዲያሲዙ ሲፈቀድ በጣዝቅተኛ የተጠረጠረበትን ወንጀል ከግምት የማያስገባ ሆኖ ስለ አገኝነው በደንብ ብታዩት እንዲሁም አንዳንድ ውሳኔዎች ጥፋተኞችን ከጥፋታቸው ሊያርም የማይችል ለሌሎችም አስተማሪ የማይሆን እና በፍትህ ስራቱላይ አሜኔታ የሚያሳጣ ስለ ሆነ ወስዳችሁ በአግባቡ ብታዩት የሚል የማጠቃለያ ሀሳብ በመስጠት ውይይታችንን አጠናቀናል።
440 viewsAlemshet Miheretie, 11:57
ओपन / कमेंट
2023-03-20 12:21:07
የአብክመ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተወጣጡ ባለሙያዎች በቼክ ሊስት የተደገፈ ድጋፍና ክትትል ዛሬ መጋቢት 11 ቀን 2015ዓ.ም በአብክመ ፍትሕ ቢሮ ላይ አካሄዱ። ከቢሮው ማኔጅመንት አባላት ጋር አጠቃላይ ውይይት አድርገዋል።
450 viewsAlemshet Miheretie, edited  09:21
ओपन / कमेंट
2023-03-19 12:44:16 በሕግ አምላክ ምዕራፍ 1 ክፍል 2



546 viewsAlemshet Miheretie, edited  09:44
ओपन / कमेंट
2023-03-17 16:44:50
494 viewsAlemshet Miheretie, 13:44
ओपन / कमेंट
2023-03-17 16:18:00
374 viewsAlemshet Miheretie, 13:18
ओपन / कमेंट
2023-03-17 15:26:49 በከባድ የሰው ግድያ እና ሰው መጥለፍ ወንጀል ተከሰው በከፍተኛ ፍ/ቤቱ ነፃ በተባሉ ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ጠየቀ፤


ተከሳሾች ፦
1) አደራጀው ገብሬ
2) ባንቲሁን አለሙ
3) ከፋለ ደምሴ
4) ምስጋናው አበራ
5) መታደል ደምሴ
6) ስሜነህ አለሙ
7) ከፋለ ቢራራ
8) አበበ ከፋለ
9) ጌትነት አስፋው
መካከል ባለው የከባድ ሰው ግድያ እና ሰው መጥለፍ ወንጀል የመተማ ወረዳ ማጠቢያ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራውን አጣርቶ ለምዕራብ ጎንደር ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ መዝገቡ ተመርምሮ እንዲወሰንለት ልኳል።

ተካሳሾችም ጥር 09 ቀን 2014 በግምት ከጠዋቱ 3:00 ሲሆን መተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ እንዲቢሎ ተብሎ ከሚጠራው ልዩ ቦታ ሟች ቄስ አያሌው አይናለምን በማገት 400,000 ብር ከተቀበሉ በሗላ መረጃ ለማጥፋት የግል ተበዳይን አይኑን በማውጣት ጫቃ ላይ ጥለውት የሔዱ ሲሎን የግል ተበዳይ በጎንደር ዩኒቨርስቱ ሪፈራል ሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ በደረሰበት ጉዳት የሞተ በመሆኑ የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያው በተከሳሾች ላይ በከባድ ሰው ግድያና ጠለፋ ወንጀል በምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሰ መስርቶ ተከራክራል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በሗላ በቀን 07/07/2015 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ከተከሰሱባቸው ክሶች ነፃ ናቸው በማለት ፍርድ ሰጥቷል።

የዞን ዐቃቤ ህግም ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ በአግባቡ ሳይመዝን እና ተከሳሾችም የቀረበባቸውን ክሶች በአግባቡ ሳይከላከሉ ነፃ ብሏቸዋል የሚል እምነት ስላለው እና በፍ/ቤቱ ውሳኔ ላይ ቅር ሰለተሰኘ ለአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ለማቅረብ የይግባኝ ግልባጭ ተገልብጦ እንዲሰጠው በቀን 07/07/2015 ዓም ለፍ/ቤቱ አመልክቷል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ
08/07/2015 ዓም
365 viewsAlemshet Miheretie, 12:26
ओपन / कमेंट
2023-03-16 21:50:50
435 viewsAlemshet Miheretie, 18:50
ओपन / कमेंट
2023-03-16 21:50:50
423 viewsAlemshet Miheretie, 18:50
ओपन / कमेंट
2023-03-16 21:50:50 የሰብአዊ መብት ቡድን በትግል ፋሬ ት/ቤት በቀን 5/07/2015 በሰብአዊ መብት ምንነትና ባህሪያት እንዲሁም ስለወንጀል ምንነትና ስለወንጀል ተጠያቂነት በሰፊው ለተማሪዎችና ለመምህራን የንቃተ ትምህርት ተሰጥቷል
374 viewsAlemshet Miheretie, 18:50
ओपन / कमेंट