Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 12

2023-02-24 15:08:34
የአብክመ ፍትሕ ቢሮ፣ከምድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች፣ከዞን ፍትሕ መምሪያዎች፣ ከሪጂዮ ፓሊታን ከተማ ፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ጋር በ2015 በጀት ዓመት 6 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሠላም ከተማ ዛሬ የካቲት 17 ቀን 2015ዓ.ም በመገምገም ላይ ይገኛል።
302 viewsAlemshet Miheretie, edited  12:08
ओपन / कमेंट
2023-02-24 15:08:28
298 viewsAlemshet Miheretie, 12:08
ओपन / कमेंट
2023-02-23 14:56:08 የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ዲያቆን ጌታቸው ላይ የ1 ዓመት ከ8 ወር የእስራት ቅጣት ተወሰነበት ።

በምስራቅ ጎጃም ዞን በግንደወይን ከተማ አስተዳደር የ12 አመት ህፃን ልጅ ላይ የጋብቻ ስነስረዓት በፈፀመ የ28 አመት ወጣት ላይ የ1ዓመት ከ8ወር የእስራት ቅጣት የተወሰነበት መሆኑን ፋስት መረጃ ከጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

ተከሳሽ ዲያቆን ጌታቸው አለልኝ አግባብ ባለው የቤተሰብ ህግ ከተፈቀደው ውጭ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ልጅ ለማግባት በማሰብ ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም በግምት ከሌሊቱ 11፡0ዐ ሲሆን በግ / ወይን ከተማ አስተዳደር ዐ1ቀበሌ ልዩ ቦታው አርሴማ ቤተክርስቲያን ውስጥ የግል ተበዳይ የ12 ዓመት ህፃንን በተክሊል ጋብቻ ወይም በሀማኖት ስርዓት ያገባት በመሆኑ ተከሳሽ በፈፀመው ለአካለ መጠን ያልደረሰችን ልጅ ማግባት ወንጀል ዓ/ህግ የሰውና ጋብቻው ሲፈፀም የሚያሳይ የፎቶ ማስረጃ በማያያዝ ክስ መስርቶ ተከሳሽም የዓ/ህግ ክስ በችሎት ተሰጥቶት የዓ /ህግ ክስ በችሎት ተነቦለት ክሱን እንዲረዳው ከተደረገ በኋላ ወንጀሉን መፈፀሙን አምኖ ነገር ግን ህፃናትን ማግባት በቤተክርስቲያ ህግ የተፈቀደ ነው ወንጀል አይደለም በማለት ተከራክሮ ፍ/ቤቱም የህግ ምስክሮችን ሰምቶ በወ/መ/ስ/ስ/ህ/ ቁ113/2 / መሠረት ፍ/ቤቱ ወደ ወንጀል ህግ አንቀጽ 648 /ሀ/በመቀየር እንዲከላከል ቢጠይቀውም ተከሳሽ ግን የመከላከያ ምስክር አቅርቦ የአቃቢ ህግን ማስረጃዎች ባለማስተባበሉ በቀን 13/6/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን እና ሌላውን የህብረተሰብ ክፍል ያስተምራል ተብሎ የታሰበውን የአንድ ዓመት ከስምንት ወር ቅጣት ውሳኔ ተላልፎበታል ፡፡
448 viewsAlemshet Miheretie, 11:56
ओपन / कमेंट
2023-02-22 20:16:59
186 viewsAlemshet Miheretie, 17:16
ओपन / कमेंट
2023-02-22 20:15:46 የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የአማራ ክልል ትብብር ጥምረት የተከናወኑ ተግባራት የሚገመግም መድረክ ተካሄደ።
(የካቲት 14 ቀን 2015ዓ.ም) መድረኩን በንግግር የከፈቱት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ የተከበሩ አቶ ገረመው ገብረጻድቅ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት በክልሉ ውስጥ ያለውን በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል መከላከልና ምላሽ መስጠት በተመለከተ ባለፉት ጥቂት አመታት የተለያዮ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ይሄን ወንጀል ለመከላከል የወጣውን አዋጅ መሠረት በማድረግ የተቋቋሙ ስድስት የስራ ቡድኖች ሕግ መከላከሉ፣ መልሶ ማቋቋሙ፣የማህበረሰብ ውይይት ፣የስልጠና የምርምር፣ የዲያስፖራ ጉዳዬች ቡድኖች ባለፋት ስድስት ወራት ስራዎችን ሲያከናውኑ ቆይተዋል ብለዋል፡፡
ይሄንን ደግሞ በበላይነት የሚያስተባብረው በአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሚመራ ተጠሪነቱ ለአማራ ክልል ኘሬዚዳንት የሆነ ምክር ቤት እንዲኖር በአዋጁ የተቋቋመውን ወደ ተግባር ለማስገባት በሂደት ያለ መሆኑን አውስተው ከርሱ በመለስ ያሉ ተግባራት እየተከናወኑ በአገር ደረጃ ላለው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስተሩ ለሚመሩት አገራዊ የትብብር ጥምረት ጭምር የተሰሩ ስራዎችን ሪፖርት እያቀረበ እየተገመገመ ነው፡፡ አያይዘውም በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀል በክልላችን ላይ በኢኮኖሚም በማህበራዊም የሚኖረው ተፅዕኖ እንዳለ ሆኖ ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች የሚያስከትል ግዙፍ ወንጀል ነው ብለዋል፡፡
በአማራ ክልል ይሄን ወንጀል ለመከላከልና ምላሽ ለመስተት በቅንጅት ምላሽ መስጠት ካልተቻለ የፀጥታም፣የደህንነት ስጋት እየሆነ ነው የመጣው፡፡በስድስት ወራት የተከናወኑ ተግባራትን መነሻ በማድረግ ለቀጣይ እንዴት ባለ መንገድ ተቀናጅተን እንሰራለን በሚል ተወያይተን በየድርሻችን ባደገ ሁኔታ ወደ ተግባር መግባት አለብን ብለዋል፡፡
ስለዚህ በክልላችን በሁሉም ዞኖች ላይ የዚህ ተግባር ምልክቶች ቢኖሩም፣ክልሉ መነሻ ፣የሌሎች ክልሎች፣የጎረቤት አገራት ጭምር ማቋረጫ መሸጋገሪያ እየሆነ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡በዚህ ልክ ከፍ አድርገን እየገመገምን እንዴት እንፍታው በማለት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
በክልላችን በሁሉም ዞኖች ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡ስለዚህ ይሄንን ለመከላከል ዋና ዋና አካባቢዎችን ለይተን ርብርብ ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ በተለይ በምስራቁ ቀጠና ፣በምዕራብ ቀጠና ምዕራብ ጎንደርና ማዕከላዊ ጎንደር በ25 ወረዳዎች ላይ በ86 ቀበሌዎች ላይ በቀበሌ ጭምር ችግር ያለባቸው ተለይተዋል፡፡
የመከላከሉ ተግባሩን እየሰፋ በየቀበሌው በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር ከማሻገር ነፃ የሆነ ቀበሌ መፍጠር በሚል መሪ መልዕክት ይዘን በንቅናቄ ችግሩን ለመፍታት የተጀማመሩ ስራዎች አሉ ብለዋል፡፡
በመጨረሻ አቶ ገረመው መድረኩ ለማዘጋጀት አስተዋፅኦ ያደረገውን አለማቀፍ የፍልሰተኞች ድርጅት (አይ.ኦ.ኤም) የቴክኒክና የገንዘብ ድጋፍ በተቋሙ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የአብክመ ፍትሕ ቢሮ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀሐይነህ አጥናፍ የአማራ ክልል የትብብር ጥምረት የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበው ከባለድርሻ ተቋማት ተለያዩ ሀሳቦች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል።
የአማራ ክልል ም/ቤት የሕግና ፍትሕ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ወርቅነህ እንደግ በበኩላቸው በክልልና ከክልል በታች ባሉ አካላት በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት እንዴት ነው ልንሰራ የሚገባ የሚለውን በአንድ ማዕቀፍ ማየት፣በሌላ በኩል ክልሉ ደግሞ ከፌዴራል እና ከአጐራባች ክልሎች ጋር ምንድነው ሊሰራ የሚገባው ብሎ ለይቶ ማውጣትና ተቀናጅቶ መስራት ይገባል ብለዋል፡፡
181 viewsAlemshet Miheretie, 17:15
ओपन / कमेंट
2023-02-22 09:29:15
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የዐቃቤያነ ሕግ አስተዳደር ጉባኤ የካቲት 14 ቀን 2015ዓ.ም ባካሄደው ጉባኤ መመሪያ ቁጥር 21/2015 የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፍትሕ ቢሮ የተሻሻለው የዐቃቤያነ ሕግ የደረጃ እድገት አሰጣጥ መመሪያ ቀርቦለት ከተወያየ በኋላ የተሰጡ አስተያየቶችን በማካተት መመሪያው እንዲፀድቅ ወስኗል። ጉባኤው ውይይቱን ዛሬ የካቲት 15 ቀን 2015ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን የተለያዮ ጉዳዮችን መርምሮ ውሳኔዎችን ያስተላልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
345 viewsAlemshet Miheretie, edited  06:29
ओपन / कमेंट
2023-02-22 05:53:38 በሕገወጥ መንገድ ሰውን ድበር የማሻገር ወንጀል የተከሰሱት 1ኛ/ ናትናኤል አደራጀው 2ኛ/ ማእረግ አድማሱ በ5 አመት ፅኑ እስራት እና በብር= 5000 እንዲቀጡ ተወሰነ፦
    ተከሳሾች ማንነታቸው ከማይታወቁ ሶማሊያ ክልል ከሚገኙ ደላላዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር  የግል ተበዳይ ዘካርያ አብዱ በሕገወጥ መንገድ ድንበር ለማሻገር  በማሰብ የግል ተበዳይን ከሶማሌ ክልል ወደ አዲስ አበባ ከአዲስ አበባ  ወደ ጎንደር በማስመጣት ሰኔ 5 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 11:ዐዐ ተከሳሾች ጎንደር ማራክ ክፍለ ከተማ ማራኪ ደሴት ማዞርያ አካባቢ ከመኪና ተቀብለው ወደ አዘጋጁት ደርም በመውሰድ እና ከዶርሙ ውስጥ አሰገብተው በመቆለፍ ለ4 ቀን ምግብ እየሰጡ ካቆ ዩት በኋላ ወደሱዳን እንድንልክህ ቅድምያ ብር=20,000 ክፈል በማለት 20,000 ብር ከተቀበሉ በኋላ በድጋሚ ብር=50,000 ካልከፈልክ ወደ ሱዳን አንልክህም መልሰን ወደ ሱማሊያ እንልክህ አለን ብለው ስለነገሩት የገል ተቀዳይ ተቆልፍ የተቀመጠበትን ደርም ቁልፍ  ሰብሮ በመውጣት ለሕግ ተቋም በማመልከቱ የጎንደር ከተማ 6ኛ ፓሊስ ጠብያ ምርመራ አጣርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ  አዋጅ ቁጥር 1178/2012 አንቀፅ 8/1/ እና የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ሀ/ የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ  በ10/6/2015 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽዎች በዐቃቤ ሕግ የረበባቸውን ክስ እና ማስረጃ ማስተባበል/መከላከል/ ባለመቻለቸው ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው  ፍ/ቤቱ  ለእያንዳዳቸው የሚታሰብ በ5 አመት ፅኑ እስራት እና በብር=5,000 እንዲቀጡ  ወስኗል።
369 viewsAlemshet Miheretie, 02:53
ओपन / कमेंट
2023-02-21 11:38:44
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በሰው መነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ምላሽ ለመስጠት የአማራ ክልል ትብብር ጥምረት የተከናወኑ ተግባራት የግምገማ መድረክ የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም እያካሄደ ነው። መድረኩ በተከበሩ አቶ ገረመው ገብረጻድቅ የመክፈቻ ንግግር የተጀመረ ሲሆን። የአብክመ ፍትሕ ቢሮ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀሐይነህ አጥናፍ የአማራ ክልል የትብብር ጥምረት የ2015 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈፃፀም ሪፓርት አቅርበው ከባለድርሻ ተቋማት ጋር ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።                                               
448 viewsAlemshet Miheretie, edited  08:38
ओपन / कमेंट
2023-02-20 19:50:05
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ በክልሉ የመንግስት ሴክተር ተቋማት እና የልማት ድርጅቶች የሕግ ክፍል ዳይሬክተሮች፣ ባለሙያዎች፣ አጋር አካላት በተገኙበት በሕግ አገልግሎት አሰጣጥ፣ በሥነ-ምግባር ዙሪያ እና የፍትሕ ፎረም ምስረታ ትኩረት ያደረገ የጋራ የምክክር መድረክ የካቲት 13 ቀን 2015ዓ.ም በባህርዳር ከተማ አካሄደ።
496 viewsAlemshet Miheretie, edited  16:50
ओपन / कमेंट
2023-02-19 10:43:04 በሰው መጥለፍ ወንጀል የተከሰሰው  ሙሉሸት ደሳለኝ በ10 ዓመት ፅኑ እስራትና በ3000 ብር ተቀጣ
ተከሳሹ የማይገባውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ ነሃሴ 17 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 8:00 ሰዓት ሲሆን በሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ቡሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው አዲጉፋ እየተባለ ከሚጠራው ቦታ ተከሳሽ ሽጉጥ የጦር መሳሪያ በመያዝ የግል ተበዳይ ጎዳዳው ጋሻው የተባለውን አግቶ በመውሰድ ለ5 ተከታታይ ቀናት ካቆየ በሇላ ነሃሴ 21 ቀን 2014 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 10:00 ሰዓት ሲሆን ሶሮቃ ንዑስ ወረዳ ቡሬ ቀበሌ ልዩ ቦታው አዲ ባሪያ ከተባለው ቦታ ላይ ከእንጨት ጋር አስሮ ጥሎት በመሄድ ከግል ተበዳይ ቤተሰቦች 40,000 ብር በመቀበሉ በኢፌዲሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 586 እና 590(1)(ሀ) እና (ሐ) የተመለከተውን በመተላለፍ የሰው መጥለፍ ወንጀል ፈፅሟል በሚል በሶሮቃ ወረዳፍ/ቤት ክስ መስርተን ስንከራከር ከቆን በሇላ ዐ/ህግ እንደ ክስ አመሰራረቱ ያስረዳን በመሆኑና ተከሳሹ የዐ/ህግን ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በቀን 30/05/2015 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሹ በተከሰሰበት የህግ ድንጋጌ መሰረት የጥፋተኝነት ውሳኔ ከተሰጠ በሇላ ጥፋተኛውንና ሌላውን የህ/ሰብ ክፍል ያስተምራል በማለት ጥፋተኛው በ10 ዓመት ፅኑ እስራትና በ3000 ብር መቀጮ እንዲቀጣ ተወስኗል::
203 viewsAlemshet Miheretie, 07:43
ओपन / कमेंट