2023-03-09 18:21:38
የርስበርስ ግድያን የሚፀየፍ ማህበረሰብ ለመገንባት የሃይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች ሚናቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ በዛሬው እለት ማለትም በ29/6/2015 ዓ/ም የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ በተገኙበት በምስራቅ ና ምዕራብ ደንቢያ፣ጎንደር ዙርያ ወረዳ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ የመጣውን የርስበርስ በርስ ግድያ ለማስቆም ያለመ የምክክር መድረክ በምእራብ ደንቢያ ወረዳ በጯሂት ከተማ ተካሂዷል።
በሦስቱ ወረዳዎች ከግድያ መስፋፋት ጋር ተያይዞ በመንስኤዎቻቸው፣ ባስከተለው ጉዳት እና በመፍትሔዎቻቸው ዙሪያ ጥናት የተካሔደ ሲሆን፦ በተካሄደው ጥናትም የስራ ሃላፊዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፍትህ እና የፀጥታ አካላት በተገኙበት የጥቁር ደም መባቃቀልን ማስቆም የሚያስችል ጥናት በምእራብ ደንቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/በት አቅራቢነት ምክክር አካሂደዋል።
በጥናቱ ለርስበርስ ግድያ መስፋፋት ዋናው ምክንያት የጦር መሳሪያ መብዛት ና የአያያዝ ችግር ፣ መሬት፣ የሀሰት ምስክር፣ ደም ምለሳ፣ የስራ አጥነት ፣የገጠር አረቂ ቤቶች መስፋፋት፣ሕገወጥ የጥይት ተኩስ፣ ስርቆት ና ወንጀል ፈፃሚዎች ላይ አስተማሪ ቅጣት አለመስጠት ከተጠቀሱት ዋና ዋና ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው ።
በዚህም የተነሳ በነዋሪዎች ላይ መፈናቀል ይደርሳል፣መሬት ሳይዘራ ይቀራል ብዙዎቹ ለረሀብ እና እንግልት ይጋለጣሉ፣ ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ይደርስባቸዋል ፣ የንብረት ዘረፋና ልጆች ከትምህርት ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ያደርጋል።
ይህን የርስ በርስ ግድያ ችግር ለማስቆም በመፍትሔነት የተጠቀሱት ደም አድርቅ የሀገር ሽማግሌዎችን ማቋቋም፣ አገር በቀል የሰላም እና የልማት ሲቪክ ማህበራትን ማቋቋም ሕገወጥ የጥይት ተኩስን ማስቆም ፣የጦር መሳርያ አያያዝን እና ሕጋዊነቱን መቆጣጠር፣የፍትህ አካላት ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር ፣አስተማሪ ውሳኔዎችን ማሰጠት፣ የሀይማኖት አባቶች ተከታዮቻቸውን ሃይማኖታዊ አስተምህሮዎችን ሊወጡ እንደሚገባ በምክክር መድረኩ ተገልጿል።
የህገወጥ የጦር መሳሪያ አያያዝ መበራከት የሚታዩ የአፈፃፀም ችግሮችን ቁጥጥር እና ክትትል በማድረግ የፀጥታ አካላት ሕገወጥ የጥይት ተኩስን ከማስቆም ይልቅ አልፍ አልፍ የወንጀለኛ ተባባሪ መሆን በሚመለከት መንግስት ሃላፊነቱን ወስዶ በግልፅ የሚታዩ ችግሮችን ለመቅረፍ ከሕዝብ ጋር በመተባበር ሊሰራ እንደሚገባ ነው በመድረኩ የተገለፀው።
በአጠቃላይ የሚከሰቱ ፈተናዎችን ለመቋቋም በጋራ ውስጣዊ አንድነት ማጠናከር ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ ተቀምጧል በማለት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ያደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
194 viewsAlemshet Miheretie, edited 15:21