Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት  ፍትሕ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ ይዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዩጵያ ጋር በመተ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት  ፍትሕ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ ይዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዩጵያ ጋር በመተባበር  ለተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ  ደረጃ ኃላፊዎች የአመራር  ክህሎት እና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ትኩረት ያደረገ ሥልጠና ከየካቲት 24 እስከ 25 ቀን 2015 ዓ.ም በጎንደር ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ተከበሩ አቶ ገረመው ገብረጻድቅ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለፁት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ከዩኤስኤአይዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዩጵያ በጀትና የቴክኒክ ድጋፍ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ፣የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ እና የማንዋል ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው ይሄን መሠረት በማድረግ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማንዋል በመፈተሸ ወደ ስራ በማስገባት አዳዲስ አመራሮችን ሰይመን ወደ ስራ ተገብቷል፡፡አደረጃጀትና አሰራሩ ከክልል እስከ ወረዳ የሚያካትት በመሆኑ የተሰጠው ስልጠና ፣ተዘረጉት አሰራሮች፣የተዘጋጀው ማንዋል እና የተፈጠረው አደረጃጀት እና የሰየምናቸው ኃላፊዎች የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አላማ ለማሳካት መነቃቃት የፈጠረ እንደሆነና ወደ ስራ ተገብቶ ለውጦችንም እያን ነው ብለዋል፡፡
ይሄ በቂ ነው ለማለት ስለማያስችል አብዛኛው የፍትሕ ሴክተር አመራር ወደ አመራርነት የሚመጣው ከባለሙያነት ተነስቶ ስለሆነ ዘመናዊ የሆነ የአመራር ብቃት ማሳደጊያ ስልጠና አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት በዘመናዊ የአመራር ክህሎት እና ስትራቴጂያዊ አስተዳደር ላይ ትኩረት አድርጎ በስልጠናው ላይ የአመራር አይነቶችን በመውሰድ ተቋማችን ላይ ተግባራዊ በማድረግ ተቋማችንን መምራት ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ሰፊ ህዝብ  የሚያስተዳድር ክልል  ነው፡፡በክልሉ ውስጥ የሕግ የበላይነት እንዲሰፍን፣ በየትኛውም ደረጃ በማንኛውም አይነት የሚገለጽ  ሕገ-ወጥ ተግባራት መልክ በማስያዝ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ማዕከላዊ ተቋም  መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት፡፡ይሄንን ለመወጣት ሁላችንም የድርሻችንን የአመራር ሚና መወጣት አለብን ብለዋል፡፡
ዛሬ እና በቀጣይ ዙር ስልጠናውን የምትወስዱ የተቋማችን አመራሮች አመራርነት ሚናችሁ እናንተ ላይ ወደቀ በመሆኑ የአመራር ክህሎትና ስትራቴጂዊ አስተዳደር  ላይ መግባባት በመፍጠር  ከላይ ሆኖ ራስን እየተመለከቱ ፣የሕዝብን ስሜት እያዳመጡ ጥረት፣ትጋት በማሳየት በሥነ-ምግባራችን የተመሰገን መሪ ልንሆን ይገባል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም  የምን ጊዜም ተባባሪያችን የሆነው የዩ ኤስ ኤ ይዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዩጵያ  የበላይ ኃላፊዎች ሚስተር ዴቪድ እና አቶ ማንደፍሮት በላይ ፕሮጀክቱ ከእኛ ጋር የሚሰራውን ስራ አጠናቆ ቢወጣም ይህ ስልጠና ቀደም ብለን የጠየቅን በመሆኑ አስፈላጊነቱን በመረዳት በጀቱን ስለፈቀዱልን በቢሮው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡