Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 13

2023-02-17 21:41:51 የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የፍታብሔርና ሕግ ጉዳይ ዘርፍ በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎች የመረጃ ለውውጥ እና የስድስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ በዘርፉ ስር ከታቀፉ ዳይሬክተሮች፣ዐቃቤያነ ሕግ፣የአስተዳደር ሠራተኞች ጋር አካሄደ፡፡

(የካቲት 10 ቀን 2015ዓ.ም)የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የፍታብሔር እና የሕግ ጉዳዩች ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር አያሌው አባተ በውይይቱ እንደገለፁት መረጃ መለዋወጥ፣በዳይሬክተሮች የተከናወኑ ስራዎች ምን ላይ እንዳለ ማወቅ፣ቅንጅታዊ አሰራራር ምን ይመስላል፣እስከታችኛው መዋቅር ያለ ግንኙነት፣በትኩረት መስኮች ላይ መነጋገር፣የድጋፍና ክትትል ስራችን ምን ይመስላል፣ በባለሙያው የሚነሱ ጉዳዩች መልካም ተሞክሮዎችን እና ችግሮችን መመልከት እንደሆነ ገልፀው፡፡
የዘርፉ ዕቅድ ለብቻው ተዘጋጅቶ አስከታች ወርዷል፣የቢሮውን አደረጃጀት በመስራት የቡድን መሪዎችን በመመደብ የተሻለ ስራ ተሰርቷል፡፡አጋር አካላት ቅንጂታዊ ስራ እንዲሳለጥ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ከ300 በላይ ሴት ዐቃቤያነ ሕግ ስልጠና እንዲያገኙ ተደርጓል፡፡ከጠበቆች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡ከዩንቨርስቲዎች ጋር የመግባቢያ ሰነድ የማዘጋጀት ስራ ተሰርቷል ፣መፈራረም ብቻ ይቀራል በቅርብ ይከናወናል፡፡ከዩንቨርስቲዎች ጋር በትብብር የአካባቢዎችን ዋና ዋና ችግር መሰረት አድርጎ ስራ ይሰራል፡፡ከአባይ ባንክ ጋር የብድር ስምምነት ለመፈፀም ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ከ2005 ዓ.ም ያሉ ሕጎችን ማጠቃለል፣የድለላ ሥራ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎችን ግብር ለማስከፈል መመሪያ ማውጣት፣በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል፣የኦዲት ግብረ ሃይል ሃብት ማስመለስ፣ጥናትና ፕሮጀክቶች እየተሰራ ነው፣የሕገ-መንግስት አጣሪ ጉባኤ፣የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎችን ቀረብ ብሎ በሕግ ጉዳይ መደገፍ፣በኮሚቴ  የተሰጡንን ስራዎች በተሻለ መፈፀም ተችሏል ብለዋል፡፡
የፍታብሔርና ሕግ ጉዳይ ዘርፍ ስር የታቀፉ ዳይሬክተሮች በስድስት ወራት የተከናወኑ ስራዎች በጥንካሬ ፣በድክመት እና ቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ዘርዘር አድርገው አቅርበው በቀጣይ ትኩረት በሚደረግባቸው ጉዳዩች ላይ ዝርዝር ውይይት ተደርጓል፡፡የሰነዶች፣የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና ጠበቆች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት በፌዴራል ደረጃ በሶስት ተቋማት የሚከናወን ተግባር እዚህ በአንድ ዳይሬክቶሬት የታጨቀ በመሆኑ ተግባሩ ሰፋ ብሎ መሰራት አለበት፣የሰው ኃይል ከስራው ፍሰት ጋር በተጣጠመ መንገድ ቢሰራ፣የረጅም ጊዜ ስልጠና በተመለከተ ከዩንቨርስቲዎች ጋር ተቀራርቦ መረጃ መለዋወጥ ይገባል፡፡በጀት ተፈላልጎ የተጠቃለሉ ህጎች ቅጽ 4 ቢታተም፣አዋጆች እንዲፀድቁ እንዲተገበር ማድረግ ይገባል፡፡
የፍታብሔር እና የሕግ ጉዳዩች ዘርፍ ወስጡ የፍታብሔር ጉዳዩች፣የሕግ ምክር፣ማርቀቅና ማጠቃለል ፣የሰብዓዊ መብት ጉዳዩች፣ሰነዶች፣የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶችና ጠበቆች ጉዳይ ዳይሬክቶሬትን አካቶ  ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡
427 viewsAlemshet Miheretie, edited  18:41
ओपन / कमेंट
2023-02-17 21:41:13
350 viewsAlemshet Miheretie, 18:41
ओपन / कमेंट
2023-02-17 10:31:18
የአብክመ ፍትህ ቢሮ ለአመራሩ፣ ለዐቃብያነ ሕግ እና ለአስተዳደር ሰራተኞች ከአባይ ባንክ ብድር ማግኘት እንዲችሉ በጠየቀው መሠረት ከአባይ ባንክ ባለሙያዎች ጋር ውይይት አደረገ፡፡

(የካቲት 9 ቀን 2015ዓ.ም) የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገረመው ገብረጻድቅ በውይይት መድረኩ እንደገለፁት ዐቃብያነ ሕግና የአስተዳደር ሠራተኞች ብድር እንዴት ማግኘት እንደሚቻሉ የክፍያው ሁኔታና ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዬች እንዲያስረዱ በአባይ ባንክ የብድር አገልግሎት ባለሙያ የሆኑትን አቶ ሰለሞንን አበጀው ጋብዘዋል፡፡
አቶ ሰለሞን አበጀው የብድር አይነቶችን፣ የአመላለስ ሁኔታዎችንና ተያያዥነት ያላቸውን ጉዳዬች ግልጽ በሆነ መልኩ አስረድተው የብድር አገልግሎቱን ለማስጀመር ከስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
በዚህም መሠረት ከዐቃብያነ ሕግና ከአስተዳደር ሠራተኞች መካከል ብድር ፈላጊዎችን አባይ ባንክ በሚወጣው መስፈርት መሰረት መልምለው ወደ ባንኩ የሚልኩ 5 አባላት ያሉት ኮሚቴዎችን በመምረጥ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡
494 viewsAlemshet Miheretie, 07:31
ओपन / कमेंट
2023-02-17 08:54:58 በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ በመምህር አካለ ወልዲ 2ኛ ደርጃ ትምህርት ቤት በ08/06/2015 ዓ ም ከጠዎቱ 1:30ጀምሮ እስከ2:10 ለ40ደቂቃ ለተማርዎች  ለመምህራኖች የንቃተ ህግ ትምህርት ተሰጥቷል።
376 viewsAlemshet Miheretie, edited  05:54
ओपन / कमेंट
2023-02-17 08:54:20
362 viewsAlemshet Miheretie, 05:54
ओपन / कमेंट
2023-02-17 07:09:03 በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሞትን ባስከተለ ከባድ የወንብድና ወንጀል የተከሰሰው  እንዳልክ ግዛው አለማየሁ በ21 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ፦
  ተከሳሽ ለጊዜው ካልተያዙት ግብረ አበሮቹ ፋሲል ወንዴ እና ሻንበል ታገለ ጋር በመሆን ለራሳቸው  ተገቢ ያልሆነ ሕገወጥ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ/ም በግምት ከምሸቱ 11:30 ሲሆን ታች አርማጭሆ ወረዳ ጭልቋና ቀበሌ ቦች ተብሎ ከሚጠራው ልዩ ቦታ ማች አቶ ማሙየ የሽዋስ ፍየል በመጠበቅ ላይ እንዳለ ሶስቱም ተከሳሽዎች በያዙት ክላሽ ወደማች አነጣጥረው በርካታ ጥይት በመተኮስ ከተተኮሱት ጥይቶች መካከል በአንድ ጥይት ተመቶ ሒወቱ ያለፈ ሲሆን ማች ይዞት የነበረውን የናብራ ቁጥር 563670 አንድ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይት ጋር ይዘው በመሔዳቸው የታች አርማጭሆ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት በተከሳሾች ላይ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ አስደግፍ በተከሳሾች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ሀ/671/2/ የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ በ6/6/2015 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ባቀረበው የመከላከያ ምስክር የዐቃቤ ሕግን ክስ እና ማስረጃ ማስተባበል ባለሠቻሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ፍ/ቤቱ በ21 አመት ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
385 viewsAlemshet Miheretie, 04:09
ओपन / कमेंट
2023-02-16 21:56:26
136 viewsAlemshet Miheretie, 18:56
ओपन / कमेंट
2023-02-16 21:55:42 በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሞትን ባስከተለ ከባድ የወንብድና ወንጀል የተከሰሰው  እንዳልክ ግዛው አለማየሁ በ21 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ፦
  ተከሳሽ ለጊዜው ካልተያዙት ግብረ አበሮቹ ፋሲል ወንዴ እና ሻንበል ታገለ ጋር በመሆን ለራሳቸው  ተገቢ ያልሆነ ሕገወጥ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ/ም በግምት ከምሸቱ 11:30 ሲሆን ታች አርማጭሆ ወረዳ ጭልቋና ቀበሌ ቦች ተብሎ ከሚጠራው ልዩ ቦታ ማች አቶ ማሙየ የሽዋስ ፍየል በመጠበቅ ላይ እንዳለ ሶስቱም ተከሳሽዎች በያዙት ክላሽ ወደማች አነጣጥረው በርካታ ጥይት በመተኮስ ከተተኮሱት ጥይቶች መካከል በአንድ ጥይት ተመቶ ሒወቱ ያለፈ ሲሆን ማች ይዞት የነበረውን የናብራ ቁጥር 563670 አንድ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይት ጋር ይዘው በመሔዳቸው የታች አርማጭሆ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት በተከሳሾች ላይ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ አስደግፍ በተከሳሾች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ሀ/671/2/ የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ በ6/6/2015 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ባቀረበው የመከላከያ ምስክር የዐቃቤ ሕግን ክስ እና ማስረጃ ማስተባበል ባለሠቻሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ፍ/ቤቱ በ21 አመት ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።
146 viewsAlemshet Miheretie, 18:55
ओपन / कमेंट
2023-02-16 20:59:30 በሰሜን ሸዋ ዞን የግሼ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤትበቀን 07/06/15 በወረዳዉ ለሚገኙ11 ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች የአ/ብ/መ/ማህ/ፍቤቶች አዋጅ ቁጥር 246/09 ላይ ማንዋል በማዘጋጀት ማንዋሉን ኮፒ በማድረግ ለሁሉም ቀበሌዎች፡ ስልጠና ተሰጥቷል።
178 viewsAlemshet Miheretie, edited  17:59
ओपन / कमेंट
2023-02-16 17:30:17 የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በአጠቃላይ ማሩ ቀመስ ደንቢያ ተብሎ በሚጠራው  ክፍል " ሆን ተብሎ የሚፈጸም የግድያ ወንጀል መነሻ ምክንያት ; ያስከተለው ጉዳትና መፍትሔ" በሚል ከ3 ወር በላይ የወሰደ ጥናታዊ ጽሑፍ  የካቲት 4ቀን 2015 ዓ.ም በጯሂት ከተማ የሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያቀረበ ሲሆን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማንዴ ዘሜ የእለቱን የክብር እንግዶች እና የስብሰባውን ተሳታፊዎች እንኳን ደህና በጣችሁ በማለት የመድረኩን አስፈላጊነት እና ጥናቱ እንዲካሔድ መስተዳድሩ በጀት ከመመደብ እና ለጥናቱ አሰፈላጊውን ግብአትና ተሽከርካሪ ከማቅረብ ጀምሮ የነበረውን የላቀ አስተወፅኦ በመግለፅ በመጨረሻ ምንም እንኳ ጥናቱ በሒደት በሕዝብ ተሳትፎ እየተጠናከረ የሚመጣ ቢሆንም በደንቢያ እና በአካባቢው ስር እየሰደደ እና እየተስፋፋ የመጣውን ሆን ተብሎ የሚፈፀም የግድያ   ወንጀል የት ቀበሌ ይበዛል? መንስኤው ምንድነው? የሚለውን እና መፍትሔውን የሚያመላክት የጥናት ውጤት በመገኘቱ አስተዳደሩ ደስተኛ መሆኑን እና ይኸው ወንጀል ፈፅሞ እስኪጠፋ ድረስ አስተዳደሩ ከወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ጎን በመሆን ቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን በመግለፅ ለጥናት ቡድኑ አባላት የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የእረፍት ጊዚያቸውን ጭምር ተጠቅመው ተሽከርካሪ  የማይገባበት የገጠር ቀበሌ ድረስ በግር ተጉዘው  ላከናወኑት የላቀ ተገባር ምስጋና በማቅረብ በተጨማሪም የውይይት መድረኩ ይሳካ ዘንድ በጀት በመመደብ አስተዋፅኦ ላደረገው አናፕካን ኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ፕሮጀክት በማመሰገን መድረኩ በይፋ መከፈቱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አብሰረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች፦
የወረዳዉ የካቢኔ አባላት፣የወረዳዉ የፍትህና የጸጥታ አካላት ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ አስታራቂ ሽማግሌዎች ፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካይ ፣ የዞኑ ፍትህ መምሪያ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የዞኑ የብልጽግና ፓርፒ ጽ/ቤት ኃላፊ ፣የዞኑ ሴቶች እና ህፃናት ማሕበራዊ ጉዳይ መምርያ ኃላፊ እና የሚመለከታቸው ክፍሎች የምስረቅ ደንቢያ የክልል ምክርቤት ተመራጭ ፣
የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት እንዲሆም የሟች እና የገዳይ ቤተሰቦች በተገኙበት 70 ገፅ የጥናት ጽሑፉ በጥት የቡድን አባላት በወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት የወንጀል የሥራ ሂደት ዐቃቤያነ ሕግ በሆኑት ወ/ሪት መንበረ አንድነትና አቶ ለማ እያዩ የጥናት ፁሑፉ ቀርቧል ።

በጥናቱ  መሠረት በወረዳዉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሆን ተብሎ የሚፈጸም የሰዉ ግድያ ወንጀል እንዳለ እና እንደተስፋፋ  በጥናቱ መረጋገጡ ተመላክቷል።
በወረዳዉ ዉስጥ ካሉት ቀበሌዎች መካከል በ11 ቀበሌዎች የሚኖሩ የሃይማኖት አባቶችን ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ከሟችና ከገዳይ ቤተሰቦች ጋር በቡድን በዉይይት (FGD) እና ቃለ መጠይቅ በመጠቀም፦
1/ እንደ መነሻ ምክንያቶች በጥናት የተለዩት
ስርቆት (ከስርቆት በኋላ በገንዘብ ክፍፍል ወቅት አለመስማማት)
የመጠጥ ቤቶች መበራከትና የጊዜ ገደብ አለመኖር
ሕገወጥ እና ሕጋዊ የጦር መሳሪያ መብዛት
ደም መመለስና የማህበረሰቡ አመለካከት
የሕግ አስፈጻሚ አካላት በወንጀል ፈጻሚዉ ላይ አስተማሪ ዉሳኔ አለመስጠት
የመሬት ይገባኛል ጥያቄ
የሥራ አጥነት መስፋፋት
በሁለም ቀበሌ የፓሊስ ኦፊሰር አለመኖር

2/ ያስከተለዉ ጉዳት፦
የገዳይ ቤተሰቦች መፈናቀል ሐብት መውደም ከአካባቢው ለቆ መሰደድ ፣
መሬት ሳይዘራ ለብዙ ዓመት መኖር
የሕጻናት ከትምህርት ገብታ መፈናቀል
የአካባቢዉ ነዋሪዎች እርስ በእርስ አለመተማመን
በመንግሥት ላይ እምነት ማጣት

3/ የቀረቡ የመፍትሔ ሐሳቦች፦
ከወረዳ እስከ ቀበሌ እዉቅና የተሰጣቸዉን ደም አድራቂ ሽማግሌዎች ማቋቋም
የቀበሌው ነዋሪዎች ወንጀል ፈጻሚዎችን ለሚመለከተዉ የመንግሥት አካል አሳልፎ መስጠት
የሃይማኖት አባቶች መንፈሳዊ ግዴታቸዉን እንዲወጡ ማድረግ
የሕግ አስፈጻሚ አካላትን ከአድሎአዊ አሰራር ነጻ ሆነው ቀጠሮ ሳይራዘም አስተማሪ ውሳኔ መስጠት
በየገጠሩ የሚገኙ መጠጥ  ቤቶችን ሰዓት መገደብ
በሕገወጥ የጦር መሳሪያ ላይ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አለበት
ግድያ እንዲፈጸም በሚያነሳሱ ግለሰቦች ላይ መንግሥት እርምጃ ቢወስድ
  ከዚህ በላይ በጥናት አቅራቢዎቹ የቀረበውን ገለፃ ተጨማሪ ሐሳብ አስተያየት ጥያቀ ከተሳታፊው ለማሰባሰብ እና ጥናቱን የበለጠ ለማስፋት በአወያዮቹ አማካኝነት ለተሰብሳቢዎቹ እድሉ የተሰጠ ሲሆን መድረኩን የመሩት
1ኛ/ የማእከላዊ ጎንደር ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ስጦታው
2ኛ/ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሠረተ ልማት መምርያ ኃላፊ እና የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ የክልል ምክርቤት ቤት አባል የሆኑት አቶ አንዱዓለም ሙሉ
3ኛ/ የማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ ኃላፊ አቶ ማሬ ብሬ
መድረኩን ሦስቱ አመራሮች የመሩት ሲሆን ከተሳታፊው ለቀረቡ በርካታ ጥያቄዎችና እና አስተያየት በጥናት ቡድን አባላት እና በመድረኩ መሪዎች ማብራርያ እና ምላሽ ተሰጥቷል ቀጣይ የጥናት ፁሑፋ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች ፣ ሕዝብ፣የመንግስት ሰራተኛ እና በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ለኃይማኖተ አባቶች እናየሲቪክ ማህበር ፣ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲወያዩ ተደርጎ በሌሎች ወረዳዎችም ተመሳሳይ ወንጀል የሚፈፀምባቸው ወረዳዎች ከዚህ ጥናት ተሞክሮ በመውሰድ እንዲገባ ትኩረት ተሰጥቶ ወደተግባር የሚገባ ሲሆን ደንቢያን በሚለከት ግን በአጭር ጊዜ ወንጀሉን በማስቆም ወረዳ የተሟላ ሰለም በዘላቂነት እንዲሰፍን እና በኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዲሆን የአፈፃፀም መመርያ እና የደርጊት መረሐ ገብር ወጥቶለት በዞን አመራር እየተመራ ወደተግባር እንቅስቃሴ የሚገባ መሆኑንእና ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት በወንጀል መከላከል ተግባር የዞኑ ከር አመራር ከፍትህ አስተዳደሩ ጋር በመሆን እና አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ አብሮ የሚሰራ መሆኑን የማእከላዊ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርፒ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት   የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ፈንታሁን ስጦታው የውይይቱን ማጠቃለያ እና የጣይ አቅጣጫ በመስጠት የእለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።
258 viewsAlemshet Miheretie, 14:30
ओपन / कमेंट