Get Mystery Box with random crypto!

በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሞትን ባስከተለ ከባድ የወንብድና ወንጀል የተከሰሰው  እን | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ሞትን ባስከተለ ከባድ የወንብድና ወንጀል የተከሰሰው  እንዳልክ ግዛው አለማየሁ በ21 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ፦
  ተከሳሽ ለጊዜው ካልተያዙት ግብረ አበሮቹ ፋሲል ወንዴ እና ሻንበል ታገለ ጋር በመሆን ለራሳቸው  ተገቢ ያልሆነ ሕገወጥ ብልፅግና ለማግኘት በማሰብ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ/ም በግምት ከምሸቱ 11:30 ሲሆን ታች አርማጭሆ ወረዳ ጭልቋና ቀበሌ ቦች ተብሎ ከሚጠራው ልዩ ቦታ ማች አቶ ማሙየ የሽዋስ ፍየል በመጠበቅ ላይ እንዳለ ሶስቱም ተከሳሽዎች በያዙት ክላሽ ወደማች አነጣጥረው በርካታ ጥይት በመተኮስ ከተተኮሱት ጥይቶች መካከል በአንድ ጥይት ተመቶ ሒወቱ ያለፈ ሲሆን ማች ይዞት የነበረውን የናብራ ቁጥር 563670 አንድ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይት ጋር ይዘው በመሔዳቸው የታች አርማጭሆ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት በተከሳሾች ላይ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ አስደግፍ በተከሳሾች ላይ ምርመራ አጣርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ በ1996 ዓ/ም ተደንግጎ የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ሀ/671/2/ የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማእከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ በ6/6/2015 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ባቀረበው የመከላከያ ምስክር የዐቃቤ ሕግን ክስ እና ማስረጃ ማስተባበል ባለሠቻሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ፍ/ቤቱ በ21 አመት ፅኑ አስራት እንዲቀጣ ወስኗል።