Get Mystery Box with random crypto!

የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በአጠቃላይ ማሩ ቀመስ ደንቢያ ተብሎ በሚጠራው  ክፍል ' ሆን | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የምዕራብ ደንቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት በአጠቃላይ ማሩ ቀመስ ደንቢያ ተብሎ በሚጠራው  ክፍል " ሆን ተብሎ የሚፈጸም የግድያ ወንጀል መነሻ ምክንያት ; ያስከተለው ጉዳትና መፍትሔ" በሚል ከ3 ወር በላይ የወሰደ ጥናታዊ ጽሑፍ  የካቲት 4ቀን 2015 ዓ.ም በጯሂት ከተማ የሕዝብ መሰብሰቢያ አዳራሽ ያቀረበ ሲሆን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማንዴ ዘሜ የእለቱን የክብር እንግዶች እና የስብሰባውን ተሳታፊዎች እንኳን ደህና በጣችሁ በማለት የመድረኩን አስፈላጊነት እና ጥናቱ እንዲካሔድ መስተዳድሩ በጀት ከመመደብ እና ለጥናቱ አሰፈላጊውን ግብአትና ተሽከርካሪ ከማቅረብ ጀምሮ የነበረውን የላቀ አስተወፅኦ በመግለፅ በመጨረሻ ምንም እንኳ ጥናቱ በሒደት በሕዝብ ተሳትፎ እየተጠናከረ የሚመጣ ቢሆንም በደንቢያ እና በአካባቢው ስር እየሰደደ እና እየተስፋፋ የመጣውን ሆን ተብሎ የሚፈፀም የግድያ   ወንጀል የት ቀበሌ ይበዛል? መንስኤው ምንድነው? የሚለውን እና መፍትሔውን የሚያመላክት የጥናት ውጤት በመገኘቱ አስተዳደሩ ደስተኛ መሆኑን እና ይኸው ወንጀል ፈፅሞ እስኪጠፋ ድረስ አስተዳደሩ ከወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ጎን በመሆን ቀጣይ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደርግ መሆኑን በመግለፅ ለጥናት ቡድኑ አባላት የሕግ የበላይነትን ለማስፈን የእረፍት ጊዚያቸውን ጭምር ተጠቅመው ተሽከርካሪ  የማይገባበት የገጠር ቀበሌ ድረስ በግር ተጉዘው  ላከናወኑት የላቀ ተገባር ምስጋና በማቅረብ በተጨማሪም የውይይት መድረኩ ይሳካ ዘንድ በጀት በመመደብ አስተዋፅኦ ላደረገው አናፕካን ኢትዮጵያ የሰላም ግንባታ ፕሮጀክት በማመሰገን መድረኩ በይፋ መከፈቱን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አብሰረዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች፦
የወረዳዉ የካቢኔ አባላት፣የወረዳዉ የፍትህና የጸጥታ አካላት ፣ የሃይማኖት አባቶች ፣ አስታራቂ ሽማግሌዎች ፣ የሴቶችና የወጣቶች ተወካይ ፣ የዞኑ ፍትህ መምሪያ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የዞኑ የብልጽግና ፓርፒ ጽ/ቤት ኃላፊ ፣የዞኑ ሴቶች እና ህፃናት ማሕበራዊ ጉዳይ መምርያ ኃላፊ እና የሚመለከታቸው ክፍሎች የምስረቅ ደንቢያ የክልል ምክርቤት ተመራጭ ፣
የዞኑ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊና ሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት እንዲሆም የሟች እና የገዳይ ቤተሰቦች በተገኙበት 70 ገፅ የጥናት ጽሑፉ በጥት የቡድን አባላት በወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት የወንጀል የሥራ ሂደት ዐቃቤያነ ሕግ በሆኑት ወ/ሪት መንበረ አንድነትና አቶ ለማ እያዩ የጥናት ፁሑፉ ቀርቧል ።

በጥናቱ  መሠረት በወረዳዉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ሆን ተብሎ የሚፈጸም የሰዉ ግድያ ወንጀል እንዳለ እና እንደተስፋፋ  በጥናቱ መረጋገጡ ተመላክቷል።
በወረዳዉ ዉስጥ ካሉት ቀበሌዎች መካከል በ11 ቀበሌዎች የሚኖሩ የሃይማኖት አባቶችን ፣ የአገር ሽማግሌዎች፣ከሟችና ከገዳይ ቤተሰቦች ጋር በቡድን በዉይይት (FGD) እና ቃለ መጠይቅ በመጠቀም፦
1/ እንደ መነሻ ምክንያቶች በጥናት የተለዩት
ስርቆት (ከስርቆት በኋላ በገንዘብ ክፍፍል ወቅት አለመስማማት)
የመጠጥ ቤቶች መበራከትና የጊዜ ገደብ አለመኖር
ሕገወጥ እና ሕጋዊ የጦር መሳሪያ መብዛት
ደም መመለስና የማህበረሰቡ አመለካከት
የሕግ አስፈጻሚ አካላት በወንጀል ፈጻሚዉ ላይ አስተማሪ ዉሳኔ አለመስጠት
የመሬት ይገባኛል ጥያቄ
የሥራ አጥነት መስፋፋት
በሁለም ቀበሌ የፓሊስ ኦፊሰር አለመኖር

2/ ያስከተለዉ ጉዳት፦
የገዳይ ቤተሰቦች መፈናቀል ሐብት መውደም ከአካባቢው ለቆ መሰደድ ፣
መሬት ሳይዘራ ለብዙ ዓመት መኖር
የሕጻናት ከትምህርት ገብታ መፈናቀል
የአካባቢዉ ነዋሪዎች እርስ በእርስ አለመተማመን
በመንግሥት ላይ እምነት ማጣት

3/ የቀረቡ የመፍትሔ ሐሳቦች፦
ከወረዳ እስከ ቀበሌ እዉቅና የተሰጣቸዉን ደም አድራቂ ሽማግሌዎች ማቋቋም
የቀበሌው ነዋሪዎች ወንጀል ፈጻሚዎችን ለሚመለከተዉ የመንግሥት አካል አሳልፎ መስጠት
የሃይማኖት አባቶች መንፈሳዊ ግዴታቸዉን እንዲወጡ ማድረግ
የሕግ አስፈጻሚ አካላትን ከአድሎአዊ አሰራር ነጻ ሆነው ቀጠሮ ሳይራዘም አስተማሪ ውሳኔ መስጠት
በየገጠሩ የሚገኙ መጠጥ  ቤቶችን ሰዓት መገደብ
በሕገወጥ የጦር መሳሪያ ላይ መንግሥት ጥብቅ ቁጥጥር ማድረግ አለበት
ግድያ እንዲፈጸም በሚያነሳሱ ግለሰቦች ላይ መንግሥት እርምጃ ቢወስድ
  ከዚህ በላይ በጥናት አቅራቢዎቹ የቀረበውን ገለፃ ተጨማሪ ሐሳብ አስተያየት ጥያቀ ከተሳታፊው ለማሰባሰብ እና ጥናቱን የበለጠ ለማስፋት በአወያዮቹ አማካኝነት ለተሰብሳቢዎቹ እድሉ የተሰጠ ሲሆን መድረኩን የመሩት
1ኛ/ የማእከላዊ ጎንደር ዞን የብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፈንታሁን ስጦታው
2ኛ/ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ከተማ እና መሠረተ ልማት መምርያ ኃላፊ እና የምስራቅ ደንቢያ ወረዳ የክልል ምክርቤት ቤት አባል የሆኑት አቶ አንዱዓለም ሙሉ
3ኛ/ የማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ ኃላፊ አቶ ማሬ ብሬ
መድረኩን ሦስቱ አመራሮች የመሩት ሲሆን ከተሳታፊው ለቀረቡ በርካታ ጥያቄዎችና እና አስተያየት በጥናት ቡድን አባላት እና በመድረኩ መሪዎች ማብራርያ እና ምላሽ ተሰጥቷል ቀጣይ የጥናት ፁሑፋ በየደረጃው ለሚገኙ አመራሮች ፣ ሕዝብ፣የመንግስት ሰራተኛ እና በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ለኃይማኖተ አባቶች እናየሲቪክ ማህበር ፣ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንዲወያዩ ተደርጎ በሌሎች ወረዳዎችም ተመሳሳይ ወንጀል የሚፈፀምባቸው ወረዳዎች ከዚህ ጥናት ተሞክሮ በመውሰድ እንዲገባ ትኩረት ተሰጥቶ ወደተግባር የሚገባ ሲሆን ደንቢያን በሚለከት ግን በአጭር ጊዜ ወንጀሉን በማስቆም ወረዳ የተሟላ ሰለም በዘላቂነት እንዲሰፍን እና በኢንቨስትመንት ተመራጭ እንዲሆን የአፈፃፀም መመርያ እና የደርጊት መረሐ ገብር ወጥቶለት በዞን አመራር እየተመራ ወደተግባር እንቅስቃሴ የሚገባ መሆኑንእና ወንጀል ከመፈፀሙ በፊት በወንጀል መከላከል ተግባር የዞኑ ከር አመራር ከፍትህ አስተዳደሩ ጋር በመሆን እና አስፈላጊውን ደጋፍ እያደረገ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ አብሮ የሚሰራ መሆኑን የማእከላዊ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርፒ ጽ/ቤት ኃላፊ እና የአማራ ብልፅግና ፓርቲ ቅርጫፍ ጽ/ቤት   የማእከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ፈንታሁን ስጦታው የውይይቱን ማጠቃለያ እና የጣይ አቅጣጫ በመስጠት የእለቱ የውይይት መድረክ ተጠናቋል።