Get Mystery Box with random crypto!

ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ ፎካል ፐርሰኖች በሪፖርት ቅጾች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡ ህ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ ፎካል ፐርሰኖች በሪፖርት ቅጾች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡ ህጻናት ጋብቻ እና በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃት ወንጀሎችን በመከላከልና ምላሽ በመስጠት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት እንደሚገባ የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) አሳሰቡ፡፡ምክትል ቢሮ ኃላፊው በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈጸሙ የኃይል ጥቃት ወንጀሎች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚያስከትሉ በመሆኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራሮችን በማጠናከር ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡በተመሳሳይም በፍልሰት ተጎጅ ለሆኑ ዜጎች የሚደረግ የህግ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ከዚሁ ጋር በተያያዘም የሚሰሩ ስራዎች መረጃዎችን በአግባቡ በመመዝገብ እና በመያዝ ሪፖርት ማድረግ ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያሌው አባተ (ዶ/ር) ይህን ያሉት ከክልል ፍትህ ቢሮ ለሚመለከታቸው ዳይሬክተሮች፣ዐቃብያነ ህጎች እንዲሁም ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ ፎካል ፐርሰኖች በሪፖርት ቅጾች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ በተሰጠበት ወቅት ነው፡፡ ተሳታፊዎችም በበኩላቸው መሻሻል ይገባቸዋል ያሏቸውን በማንሳት እና በመወያት መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡