Get Mystery Box with random crypto!

የደምበጫ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ከአጋር አካላት ጋር በተለይም ከደምበጫ ወረዳ ፍ/ቤት ከደምበጫ ዙ/ወ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የደምበጫ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ከአጋር አካላት ጋር በተለይም ከደምበጫ ወረዳ ፍ/ቤት ከደምበጫ ዙ/ወ/ፓሊስ ጽ/ቤት እና ከደምበጫ/ከ/አሰ/ ፓሊስ ጽ/ቤት የሁሉንም የማናጅመንት አባላት ባካተተ መልኩ ውይይት ማድረግ የቻለ ሲሆንና ፦ የመወያያ አጀንዳዎችም፡ 1ኛ የችሎት አቀራርብን በተመለከተ 2ኛየሰባዊ መብት አየያዝን በተመለከተ 3ኛፓሊስ በወንጀል ጠርጥሪያችሏለሁ ብሎ በህግ ቁጥጥር ስር የሚያውላቸውን የተጠረጠሩበትን ወንጀል ከማሳወቅ አኳያ እና በ48 ስዓት ውስጥ ፍ/ቤት እንዲቀርቡ ከማድረግ አኳያ 4ኛ የተከሳሽ እና የምስክር አቀራርብን በተመለከተ አንስተን የተወያየን ሲሆን በውይይቱ የተነሱት ሀሳቦችም ፦ በደምበጫ ከተማ አስተዳድር ፓሊስ የተነሳው እና መፍትሔነው ብለው ያስቀመጡት የችሎት አቀራርብ ፓሊስን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ዙሪያነበር የሚያቀርብ አሁን በምን አግባብነው እኛን አቅርቡ የምትሉን የሰባዊ መብትን በተመለከተ ፍፁምነን ማለት ብንችልም በተቻለ መጠን የሰባዊ መብት አየያዝን ባከበረ መልኩ እየሰራንነው። የተከሳሽ ምስክር አቀራርብን በተመለከተ ከመቸውም በላይ እየሰራን ነው ወደፊትም ጠክረን እንሰራለን ብለዋል። የደም/ዙ/ወ/ ፓሊስ በበኩሉ ከዚህ ቀደምም ቢሆን የችሎት አቀራርብም ሆነ የተጠርጣሪዎች ማቆያ ጣቢያ የራሳችሁ እዲኖራችሁ ተነጋግረናል ነገርግን በነበረው ሀገራዊ ሁኔታ እና ትሰሩ እንደሆነ ብለን ታገሰናችሏል ካሁን በሏላ አንችልም የሚል ሀሳብ ሰጠዋል። የሰባዊ መብት አየያዝ ብዙም ችግር የለብንም ወደፊትም ከዚህ የተሻለ እናደርገዋለን ብለዋል። የተከሳሽ ምስክር አቀራርብ ባለፈው ስድስት ወር አንድ መዝገብ ብቻነው የተዘጋብን ወደፊት ያንንም እናስከፍታለን ሌላም እደይዘጋብን ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል። በፍ/ቤት በኩል የተነሳው ፦ ችሎት አቀራርብን በተመለከተ በጣም እየተቸገርን ስለሆነ ሁለታችሁ ተነጋግራችሁ መፍትሔ አስቀምጡ ይህን የማታደርጉ ከሆነ የምንሰጠውን ትዕዛዝ ለማስከበር እንገደዳለን ብለዋል አልፎ አልፎ ቢሆንም ማረሚያቤት እድትወስዱ ትዛዝ ሰጠን ጣቢያ ታቆያላችሁ ይህም መታረም አለበት ብለዋል። ዐ/ህግ በበኩላቸው ከመቸውም በተሻለ ከአጋር አካላት ማለትም ከሁለቱም ፓሊስ እናፍ/ቤትጋር ስራን መሰረት ያደረገ መልካም ግንኝነት አለን ሆኖም ግን ጣቢያላይ ማቆየት ፣ በ48 ስዓት ውስጥ ፍ/ቤት ያለ ማቅረብ ፣ የልፎአልፎ ቢሆንም የሰባዊ መብት አየያዝ ችግር በሁለቱም በኩል በተለይ ከተማ ፓሊስላይ ጉላ ብሎ በሚታይ መልኩ መኖር እና የተከሳሽ ምስክር አቀራርብም ተደጋጋሚ ቀጠሮ እያስጠየቃችሁን ስለሆነ ጠንክራችሁ ብሰሩ የሚል ሀሳብ ሰጠዋል። በማጠቃለያ ሀሳብ ላይ የተስማማንባቸው ፦ ዙሪያ ፓሊስ እደተዚህ ቀደማችሁ በመቻቻል እና በመተጋገዝ እስከዚህ ዓመት መጨረሻ የችሎት አቀራርብንም ሆነ ጣቢያውን ተባበሯቸው ከተሞችም በተለይ ከባድ ወንጀል የሚጠረጠሩትን እና የጊዜ ቀጠሮ የሚያስፈልጋቸውን ዋስትናን በተመለከተ እናተ አቅርቡ በሌላ በኩል ለተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበትን ወንጀል አሳውቁ እንዲሁም የሰባዊ መብት አየያዝን በተመለከተ ከዚህ በተሻለ እንዲሆን ስለምንፈልግ እራሳችሁን በማየት አስተካክሉ ፡ ተከሳሽ ምስክር አቀራርብን በተመለከተ ጥሩነው ግን ስጋቶች ስለአሉ ጠከር ብላችሁ ስሩ በፍ/ቤት በኩል የዋስትና የሚያዘው /እንዲያሲዙ ሲፈቀድ በጣዝቅተኛ የተጠረጠረበትን ወንጀል ከግምት የማያስገባ ሆኖ ስለ አገኝነው በደንብ ብታዩት እንዲሁም አንዳንድ ውሳኔዎች ጥፋተኞችን ከጥፋታቸው ሊያርም የማይችል ለሌሎችም አስተማሪ የማይሆን እና በፍትህ ስራቱላይ አሜኔታ የሚያሳጣ ስለ ሆነ ወስዳችሁ በአግባቡ ብታዩት የሚል የማጠቃለያ ሀሳብ በመስጠት ውይይታችንን አጠናቀናል።