Get Mystery Box with random crypto!

በከባድ የሰው ግድያ እና ሰው መጥለፍ ወንጀል ተከሰው በከፍተኛ ፍ/ቤቱ ነፃ በተባሉ ተከሳሾች ላይ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በከባድ የሰው ግድያ እና ሰው መጥለፍ ወንጀል ተከሰው በከፍተኛ ፍ/ቤቱ ነፃ በተባሉ ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ህግ ይግባኝ ጠየቀ፤


ተከሳሾች ፦
1) አደራጀው ገብሬ
2) ባንቲሁን አለሙ
3) ከፋለ ደምሴ
4) ምስጋናው አበራ
5) መታደል ደምሴ
6) ስሜነህ አለሙ
7) ከፋለ ቢራራ
8) አበበ ከፋለ
9) ጌትነት አስፋው
መካከል ባለው የከባድ ሰው ግድያ እና ሰው መጥለፍ ወንጀል የመተማ ወረዳ ማጠቢያ ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት የወንጀል ምርመራውን አጣርቶ ለምዕራብ ጎንደር ዞን ዐቃቤ ህግ መምሪያ መዝገቡ ተመርምሮ እንዲወሰንለት ልኳል።

ተካሳሾችም ጥር 09 ቀን 2014 በግምት ከጠዋቱ 3:00 ሲሆን መተማ ወረዳ ቱመት መንዶካ ቀበሌ እንዲቢሎ ተብሎ ከሚጠራው ልዩ ቦታ ሟች ቄስ አያሌው አይናለምን በማገት 400,000 ብር ከተቀበሉ በሗላ መረጃ ለማጥፋት የግል ተበዳይን አይኑን በማውጣት ጫቃ ላይ ጥለውት የሔዱ ሲሎን የግል ተበዳይ በጎንደር ዩኒቨርስቱ ሪፈራል ሆስፒታል ሲታከም ቆይቶ በደረሰበት ጉዳት የሞተ በመሆኑ የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያው በተከሳሾች ላይ በከባድ ሰው ግድያና ጠለፋ ወንጀል በምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክሰ መስርቶ ተከራክራል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማ በሗላ በቀን 07/07/2015 ዓም በዋለው ችሎት ተከሳሾችን ከተከሰሱባቸው ክሶች ነፃ ናቸው በማለት ፍርድ ሰጥቷል።

የዞን ዐቃቤ ህግም ከፍተኛ ፍ/ቤቱ ዐቃቤ ህግ ያቀረበውን ማስረጃ በአግባቡ ሳይመዝን እና ተከሳሾችም የቀረበባቸውን ክሶች በአግባቡ ሳይከላከሉ ነፃ ብሏቸዋል የሚል እምነት ስላለው እና በፍ/ቤቱ ውሳኔ ላይ ቅር ሰለተሰኘ ለአብክመ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ለማቅረብ የይግባኝ ግልባጭ ተገልብጦ እንዲሰጠው በቀን 07/07/2015 ዓም ለፍ/ቤቱ አመልክቷል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ
08/07/2015 ዓም