Get Mystery Box with random crypto!

የፍ/ሰላም ከተማ ወ/ፍ/ቤት እና የፍ/ሰላም ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት  መጋቢት 18/2015 ዓ.ም ውይይ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የፍ/ሰላም ከተማ ወ/ፍ/ቤት እና የፍ/ሰላም ከተማ ፍትህ ጽ/ቤት  መጋቢት 18/2015 ዓ.ም ውይይት አደረጉ። በውይይቱም ፦
ፍትህን ለማስፈን እና የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ፍርድ ቤት እና ፍትህ ጽ/ቤት እንዴት  ተባብረን በመስራት የማህበረሰቡን ችግሮች መፍታት የሚቻለው?  የሚለውን የመነሻ ሀሳብ በማድረግ ሰፋ ያሉ ሀሳቦች በዐ/ህጎች እና በዳኞች የተነሱ ሲሆን በተለይም ህገ ወጥ የመሬት ወረራን መከላከልን በተመለከተ፣ የእግድ ትዕዛዝ አሰጣጥን በተመለከተ፣ የማስረጃ አቀራረብን በተመለከተ ፣ የቀጠሮ አሰጣጥን፣  ከመሬት ጋር የተያያዙ  ክሶች (ሁከት ይወገድልኝ) የዕርቅ ውል ማፅደቅን በተመለከተ እና ሌሎችም ሀሳቦች ሰፋ ባለመልኩ በሁለቱም በኩል ተነስተው  ምላሽ ተሰጦባቸዋል::
 በማጠቃለያውም የፍ/ቤቱ ሰብሳቢ ዳኛ እና የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊው በውይይቱ በተነሱት ሀሳቦች ላይ ምላሽ ሰጥተው በቀጣይም ችግሮችን በመለየት እና የጋራ ውይይቶችን በማድረግ የመፍትሄ ሀሳቦችን በማስቀመጥ ማህበረሰቡን ፍትሀዊ የሆነ አገልግሎት በመስጠት ተባብረን እና ተጋግዘን በመስራት ችግሮች መፍታት ያለባቸው መሆኑን በመግባባት ውይይቱ ተጠናቋል::