Get Mystery Box with random crypto!

የሰብል ምርት ግምትን አላግባብ በመቀነሰ ከሰብል ምርት ታክሰ ሊገኝ የሚችለውን 8.9 ሚሊዮን ብር | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የሰብል ምርት ግምትን አላግባብ በመቀነሰ ከሰብል ምርት ታክሰ ሊገኝ የሚችለውን 8.9 ሚሊዮን ብር መንግስት እንዲያጣ ያደረገ የግብርና ጽ/ቤት ሓላፊ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል  በፅኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጣ
~~~~

ተከሳሸ በህሩ አህመድ የመተማ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ሃላፊ በነበሩበት 2011 ዓም ከሰብል ምርት ታክሰ ለመሰብሰብ በወረዳው የሚገኙ የእርሻ ኢንቨስተሮች 2010 ዓም ለ2011 ዓም ያመረቱት ምርት በሰብል ገማች ኮሚቴ ተገምግሞ የፀደቀ ሲሆን ተከሳሹ ያልተገባ ጥቅም ለራሱ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ ተገምግም የፀደቀውን የሰብል ግምት አላግባብ የቀነሰ መሆኑ በማስረጃ ተረጋግጧል።

ተከሳሹም የመንግስትን ስራ በማያመች አኳሗን በመምራት የሰብል ምርት ግምገማውን በመቀነሱ መንግስት ሊያገኝ ይችል የነበረውን 8.9 ሚሊዮን ብር እንዲያጣ ያደረገ በመሆኑ የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤህ ህግ ከመተማ ወረዳ ፖሊሰ ጽ/ቤት ተጣርቶ የመጣለትን መዝገብ በመመርመር ለምዕራብ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ተከራክሯል።

ዐቃቤ ህግም የሙስና ወንጀል ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 13(3) በመጥቀሰ የመንግሰትን ስራ በማያመች አኳሃን በመምራት የሙስና ወንጀል ከሶ ሲከራከር የቆየ ሲሆን የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤት ተከሳሽ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ ዛሬ በቀን 14/07/2015 ዓም በዋለው ችሎት የጥፋተኝነት ፍርድ ሰጥቷል

ፍ/ቤቱም የዐቃቤ ህግንና የተከሳሹን የቅጣት አስተያየት ካዳመጠ በሗላ ዛሬ ከሰዓት በነበረው ችሎት #የ6አመት ከ6ወር ፅኑ እስራትና #የሶስት ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ ፍርድ ሰጥቷል።

መረጃው የምዕ/ጎ/ዞ/ፍ /መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሒደት ነው
14/07/2015 ዓም