Get Mystery Box with random crypto!

በከባድ እምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የተከሰሱት ግለሰቦች ተቀጡ፡፡ 1ኛ. ተከሳሽ ሳ/ን ኢብራሄም | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በከባድ እምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል የተከሰሱት ግለሰቦች ተቀጡ፡፡
1ኛ. ተከሳሽ ሳ/ን ኢብራሄም ሀሰን 2ኛ. ተከሳሽ ኮ/ል አሰፋ ሞገስ 3ኛ ተከሳሻ ረ/ኢ ተሻለ አመዴ 4ኛ ተከሳሽ ሞሳየ ጀምበሩ እርስ በእርሳቸዉ በመመሰጣጠር በቀን 14/11/2014 ዓ/ም ከቀኑ በግምት 11፡00 ስዓት ጃናሞራ ወረዳ ባህር አምባ ቀበሌ ልዩ ቦታዉ 32ኛ ሻለቃ ኦረድናስ ክፍል ከጦር መሳሪያ እና ግምጃ ቤት 1ኛ ተከሳሽ ለክፍለ ጦሩ መሳሪያና ጥይት ላስረክብ ነዉ በማለት የሻለቃዉ አስተዳደርና ሎጅስቴክ ሃላፊ የሆነዉን 3ኛ ተከሳሽ እንዲያስረክበዉ ከጠየቀ በኋላ እስቶር ዉስጥ እንዲያድር በማመቻቸት ከተረከበዉ 1 ኤስ-ኬስ እና 15 ሰደፍ ክላሽ መሳሪያ ዉጭ 3832 የክላሽ ጥይት በመጨመር በቀን 15/11/2014 ዓ/ም ጠዋት በማዳበሪያ እና በወታደራዊ ሻንጣ የተቋጠሩትን የጦር መሳሪያ በሌሎች የልዩ ሃይል እገዛ ከጃናሞራ ወረዳ ወደ መንገድ በማቅረብና በመኪና ጭኖ ወደ ደባርቅ ከተማ በማምጣት በዩኒክላንድ ሆቴል አልጋ በመያዝ 1 እግር ታጣፊ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይት ጋር፣2 እግር ታጣፊ ክላሽ ከመሰል 30 ጥይት ጋር፣በ2 ሻንጣ 2754 የክላሽ ጥይት፣በሚሌተሪዉ 30 የክላሽ ጥይት፣እና 7 የክላሽ ካዝና ይዞ የተገኘ፣ 2ኛ ተከሳሽ ደግሞ ከላይ የተገለፁትን መሳሪያዎች አብሮ የወሰደና 2 እግር ክላሽ መሳሪያ ከመሰል 30 ጥይት ጋር ይዞ ከዚያ ሆቴል መዉጫ ላይ ይዞ የተገኘ፣3ኛ ተከሳሽ ደግሞ እስቶር ዉስጥ እንዲያድር በማድረግ ያሥወሰደ እና የተመሳጠረ እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ያመጡትን የጦር መሳሪያ በመቀበልና በመተባበር 2 እግር ታጣፊ ክላሽ ከ30 ጥይት ጋር፣928 የክላሽ ጥይት እና 6 ካዝና በመያዝ የወንጀሉ ሙሉ ተካፋይ የሆነ በመሆኑ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/፣የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 31/2/ን በመተላለፍ በፈፀሙት በዋና ወንጀል አድራጊነት በከባድ እምነት ማጉደል የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ስለሆነም የደባርቅ ከተማ ፖሊስ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀል ምርመራ ክፍል አጣርቶ የላከውን መዝገብ የሰሜን ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ክስ መስርቶበት የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲያከራከር ከቆየ በኋላ ተከሳሾች በመከላከያ ምስክሮች ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸዉ ፍርድ ቤቱ መጋቢት 11/2015 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሾቹን ያስተምራል፤ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ያለዉን 1ኛ ተከሳሽን 5 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራትና የ2000 ብር እንዲሁም 2ኛ፣3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾችን በእያንዳንዳቸዉ 6 ዓመት ፅኑ እስራትና የ3000 ብር ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡