Get Mystery Box with random crypto!

የ13ዓመት ህፃን አስገድዶ የደፈረዉ ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ። ተከሳሽ አቶ ፋሲል | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የ13ዓመት ህፃን አስገድዶ የደፈረዉ ግለሰብ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ።

ተከሳሽ አቶ ፋሲል ክፋለ እየሱስ እድሜ 42  አድራሻ ጎንደር  ከተማ ቀበሌ 17 ሲሆን ተከሳሽ ተቃራኒ ፆታ ከሆነችው 13 አመት  ያልሞላት ታዳጊ ህፃን ጋር የካቲት 4/ 06 /2015 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 3 :00 ስዓት  አካባቢ  በጣቁሳ ወረዳ  ጨዉድባ ቀበሌ ከግል ተበዳይ ወላጆች መኖሪያ ቤት ህፃኗን  አስገድዶ ክብረ ንፅህናዋ ላይ በደል ያደረሰባት በመሆኑ  በወረዳዉ በወንጀል  ምርመራ  የፖሊስ ክፋል   ማጣራት  ተደርጎ ለጣቁሳ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት  የወንጀል ዐቃቢ ህግ እንዲደርስ የተደረገ ሲሆን የወረዳዉ ዐቃቢ ህግም የሰነድና የሰዉ ማስረጃዎች  በማጠናከር  በ1996 ዓ.ም ተደንግጎ የወጣዉ  የኢ ፈደሪ  የወንጀል ህግ አንቀጽ 627 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የተመለከተውን  ተላልፎ  በመገኝቱ ዐቃቢ ህግ በኩል ለጣቁሳ ወረዳ ፋርድ ቤት ክስ አቅርቧል።

በዚህ መነሻ መሰረት በማድረግ የጣቁሳ ወረዳ ፋርድ ቤት  የወንጀል ዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥ ግራ ቀኙን ሲያከራክር ከቆየ  በኋላ ዐቃቢ ህግ እንደ ክስ አመሰራረቱ በሰዉና በሰነድ ማስረጃ  ተከሳሽ ላይ በሚገባ ያስረዳ በመሆኑ ፋርድ ቤቱ ተከሳሱን ተከላካይ ሲል ብይን ሰጥቷል ።

ይሁን እንጂ  ተከሳሽ የቀረበበትን ክስ መከላከል ባለመቻሉ በቀን 14/07/2015 ዓ/ም ፋርድ ቤቱ በዋለዉ ችሎት ጥፋተኛ ነዉ ሲል ዉሳኔ ተሰጥቷል ።

በጨረሻም  ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኝ ተከራካሪዎች ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ ና ማክበጃ ምክንያቶች ታሳቢ በማድረግ ፍርድ ቤቱ በቀን 15/072015 ዓ/ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሹን ያርማል ሌላዉን የማህበረሰብ ክፍል ያስተምራል ያለዉን የ14 አመት ፅኑ እስራት ተከሳሽ እንዲቀጣ ውሳኔ  አስተላልፏል ።
የጣቁሳ ወረዳ ዐቃቤ ህግ ጽ/ቤት