Get Mystery Box with random crypto!

በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አማካኝነት ውጤታማ የሆነውና ግድያን ለማስቆም እተሰጠ የሚገኘ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በምዕራብ ደምቢያ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት አማካኝነት ውጤታማ የሆነውና ግድያን ለማስቆም እተሰጠ የሚገኘው የንቃተ ህግ ግንዛቤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው።

ተቋሙ እስካሁን ጠቃሚ ጥናት በመንደፍ በወረዳው ጯሂት ከተማን ጨምሮ ስምራ፣ ጀንዳ፣ መስቀለ ክርስቶስ፣ ተዘባ፣ ጉራንዲ፣ ማንጌ፣ ቸንከላ፣ ዳህና ዋዋ እና ሌሎች ቀበሌዎች ላይ በአካባቢው እየተከሰተ ስላለው ግድያ ግንዛቤ ሰጥቷል።

በዛሬው ዕለት በዳህና ዋዋ ቀበሌ ተገኝተው ለነዋሪዎች ግንዛቤ የፈጠሩት የወረዳው ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ዲያቆን ደርባባው ድንቄ በወረዳው ግድያን ለማስቆም ጥናት በማጥናት ወደ ስራ መግባታቸውን አስረድተዋል።

ጥናቱ የእርስ በርስ ግድያን በማስቆም ደም የተጋቡትን ገና ከጅምሮ ወደ እርቅ እያመጣ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው ስካር፣ ስርቆት፣ አላስፈላጊ ግጭት፣ እርኩስ ቅናት፣የቆየ ደም ምለሳ እና ሌሎች የግድያ መንስኤ መሆናቸዉን አስረድተዋል።

በመሆኑም ያሉት የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊው ዲያቆን ደርባባው ድንቄ ሰው መግደል በመሬት በህግ፤ በሰማይ ደግሞ ሀጢያት መሆኑን እና የሚያስጠይቅ እንደሆነ ገልፀዋል።

ይህን ለማስቀረት እና በወረዳው ማህበረሰብ ግድያን በእርቅ ለመሻር ሰላም ለመፍጠርም ኮሚቴ በማቋቋም ወደ ስራ መግባታቸውን ኃላፊው አስረድተዋል።

በሌላ በኩል በንቃተ ህጉ ግንዛቤ ፈጠራ የተገኙት ሊቀ ጠበብት መንግስቱ ተገኘ ሰው መግደል ሰይጣናዊ ተግባር መሆኑን ገልፀው ግድያ ለማስቀረትም ለወረዳው ህዝብ ግንዛቤ እየፈጠሩ መሆኑን አስረድተዋል።

ሊቀ ጠበብቱ ለቤተሰቦቻችን በቀል ማውረስ የለብነም ያሉ ሲሆን ግድያን በእርቅ ለማስቆም እየሰራን ነው ብለዋል።

እንደ አጠቃላይ የንቃተ ህግ የግንዛቤ ስራው የሚቀጥል መሆኑ እና እርስ በእርስ የተጋደሉ ወገኖቻችን በማስታረቅ ሰላም በመፍጠር በተሰጠን የተፈጥሮ ጠጋ ደምቢያን የምናለማ መሆኑን ነው በመድረኩ የተመላከተው።

በጌትነት ተችሎ
መጋቢት 21/2015 ዓ/ም