Get Mystery Box with random crypto!

በቋራ ወረዳ ሰዎችን በማገት 200,000 ብር  የተቀበለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ ። ተከሳሸ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በቋራ ወረዳ ሰዎችን በማገት 200,000 ብር  የተቀበለው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ ።
ተከሳሸ ይታየው ጎራው ከልተያዘው ግብረ አበሩ እና በፀጥታ አካላት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሁለት ግለሰቦች ጋር በመሆን በቋራ ወረዳ በርሜል ፀበል ተጠምቀው ሲመለሱ የነበሩትን ግለሰቦች በማገት 200000(ሁለት መቶ ሺ ብር) የተቀበለ በመሆኑ በቋራ ወረዳ ፍ/ቤት የወረዳው ዐቃቤ ህግ ክስ መስርቶ ተከራክራል። ዐቃቤ ህንም ተከሳሸ ከግል ተበዳዮች የተቀበለውን 200,000 ብር እንደከፍል ከወንጀል  ክሰ ጋር አቅርቦ እንደተከራከረ የቋራ ወረዳ ፍትህ ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ሀብታሙ አበጀ ገልፀውልናል።

      የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው  ተከሳሽ በ1996ዓ.ም ተደንግጎ የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀፅ 32(1) (ሀ)፣58(1)፣560(1)ለ እና 2(ሐ)ን በመተላለፍ የጦር መሳሪያ ከያዙ ግብረ አበሮች ጋር በመሆን የማይገባዉን ጥቅም ለማግኘት በማሠብ የካቲት 9ቀን 2015 ዓ/ም በግምት ከለሊቱ 10:00 ሰዓት ቋራ ወረዳ ከበርሚል ፀበል ተጠምቀዉ ወደ ገለጉ ቀበለ በመመለሥ ላይ የነበሩትን የግል ተበዳዮች  2 (ሁለት) ግለሰቦች በማገት ከእያንዳንዳቸዉ ከአቶ ኢሳያስ ፍቃዱ 110,000 (አንድ መቶ አስር ሺ) ብር ከ አቶ ላይችሉ ብርሃኑ 90,000(ዘጠና ሺ) ብር በጠቅላላው  200,000(ሁለት መቶ ሺ) ብር በማሥከፈል የለቀቋቸዉ በመሆኑ በሰዉ መጥለፍ (ማገት) ወንጀል ተከሷል።
ተከሳሽም በዐ/ህግ በኩል የቀረበበትን ክስ  መፈፀሙን ያመነ በመሆኑ ጥፋተኛ ተብላል።

ፍ/ቤቱም ተከሳሹ የቀረበበትን ክሥ መቃወም ያልቻለና ጥፋተኛነቱን ያመነ በመሆኑ ተከሣሽን ያርማል መሠል ድርጊት ፈጻሚዎችን ያሥተምራል ብሎ ያመነበትን በቀን 27/6/2015 ዓ/ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት በተሠጠዉ ፍቅድ ሥልጣን በ6 (ስድስት )  አመት ፅኑ እሥራት እንዲሁም የግል ተበዳዮች ለማስለቀቅ የተከፈለውን ገንዘብ ለግል ተበዳዮች በወንጀል ህግ 101 መሰረት እንዲመለስ  በማለት ዉሣኔ ሠጥቷል።

ከላይ የክሰ ሒደት እንደተመለከትነው ተከሳሾች በእገታ ወንጀል ያገኙትን ጥቅም በወንጀል ክሱ ጋ አጣምሮ ከሰ ገንዘቡን ማስመለሰ ያልተመደና የተሻለ አሰራር በመሆኑ ሁሉም በዞኑ የሚገኙ ፍትህ ፅ/ቤት በወንጀል የተገኘ ንብረትን አጣርት በማስመለሰ ወንጀለኞች ያልተገባ ጥቅም ማምከን ይገባል።
ፖሊስም የወንጀል ምርመራ ሲያጣራ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን በማፈላለግ ከተጠርጣሪዎች የተገኘን ንብረትን በፍሬድ ቤት በማሳገድ የመዝገቡ አካል አድርጎ ለዐቃቤ ህግ እንዲልክ እንገልፃለን።

መረጃው የምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ  ነው

መጋቢት 07 ቀን 2015ዓም