Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 65

2022-05-16 18:57:55
የሀዘን መግለጫ

በምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ የመተማ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት የፍትሐብሄር የስራ ሒደት አስተባባሪ እና ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ ኢዮኤል መንገሻ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ ግንቦት 08 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ኢዮኤል መንገሻ በዐቃቤ ሕግ ሙያቸው በቋራ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን ህብረት ስራ ማህበር የሕግ ባለሙያነት እና አሁን በህይወት አሰከተለዩበት ድረስ የመተማ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት የፍትሐብሄር የስራ ሒደት አስተባባሪ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ፣ምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ፣የመተማ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ዐቃቤያነ ሕግና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ ለቤተሰቦቹ ፣ ለጓደኞቹ ፣ ለስራ ባልደረቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛሉ።
231 viewsAlemshet, edited  15:57
ओपन / कमेंट
2022-05-16 08:58:15 በሀሰተኛ ሰነድ/መታወቂያ/መገልገል ወንጀል የተከሰሰው በ2 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በብር 40,000 እንዲቀጣ ተወሰነ
ተከሳሽ ዋሲሁን እረብሶ ወዳጆ ለራሱ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በጎንደር ከተማ አስተዳደር  በሽሮ ሜዳ ቀበሌ በመታወቂያ ቁጥር 03/መ. ቁ 27400 በቀን 30.4.2013 ዓ.ም እንደተሰጠው  በማስመሰል በሀሰት የተዘጋጀ ሀሰተኛ የነዋሪነት የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ ታህሳስ 7.04.2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8:30 ሰአት ሲሆን በጎንደር ከተማ አስተዳደር ሽሮ ሜዳ ቀበሌ በሐሰት የተዘጋጀውን መታወቂያ ለማሳደስ ሲል በቀጥታ የተያዘ በመሆኑ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምርያ 3ኛ ፓሊስ ጣቢያ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ምርመራ አጣርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሒደት በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ የተላከለትን መዝገብ መርምሮ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23/3/የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ በ28.8.2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት  ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ2 አመት ከ6 ወር እስራት እና በብር 40,000 እንዲቀጣ ተወስኗል በማለት መረጃውን ያደረሰን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ነው።
284 viewsAlemshet, 05:58
ओपन / कमेंट
2022-05-16 05:57:51 በአሚኮ ቴሌቪዥን "ፍትሕ" ኘሮግራማችን "የሚዲያ አጠቃቀም እና ሕግ ላይ" የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አያሌው አባተ የሰጡት ማብራሪያ ሙሉውን ይከታተሉ። 

290 viewsAlemshet, 02:57
ओपन / कमेंट
2022-05-16 05:56:40 አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል ባካሄደው ወረራ ያደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ጉዳት የጥናት ውጤት

284 viewsAlemshet, 02:56
ओपन / कमेंट
2022-05-15 15:19:38 በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል የተከሰሰው ተከሳሽ ላይ በፅኑ እስራት እና የገንዘብ ቅጣት ተወሰነ ተከሳሽ ሞገስ ሙላት ለራሱ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የላይ አርማጭሆ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ በቁጥር የሰ/ሃ/459/09 በቀን 15/02/2009 ለትክል ድንጋይ መሪ ማዘጋጃ ቤት ሲቪል መኃንዲስ ባወጣው ማስታወቂያ ተወዳዳሪዎች ለትምህርት ደረጃው መነሻ የብቃት ማረጋገጫ COC ማቅረብ እንዳለባቸው ማስታወቂያው ስለሚገልፅ ተከሳሽም በዚህ ማስታወቂያ ከሳንጃ ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጅ ደረጃ lV በኢንሳይት ቢውልዲንግ ኮንስትራክሽን ማኔጅመንት የተሰጠ ማስረጃ በመያዝ ለዚህም የትምህርት ዝግጅት የብቃት ማረጋገጫ እንዳለፈ በማስመሰል በፌዴራል ትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቶ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሙያ ብቃት ምዘናና ብቃት ማረጋገጫ ኤጀንሲ በመለያ ቁጥር CONBBC 2014 _ 2017 _03_ 154548 በሐሰት በማዘጋጀት በወጣው ማስታወቂያ ተመዝግቦ በማለፍ እና ስራ ላይ ሆኖ እየተገለገለ ብር 59,930.00 የማይገባውን ክፍያ /ጥቅም በማግኘቱ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፓሊስ መምርያ የሙስና ወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል በተከሳሹ ላይ ምርመራ አጣርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምርያ የሙስና ጉዳይ ወንጀል የስራ ሒደት በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን ምርምሮ በሰውና እና በሰነድ ማስረጃ ወንጀሉ ሰለመፈፀሙ አረጋግጦ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23/3/ የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ በማቅረብ ጉዳዮ በክርክር ቆይቶ በ28.8.2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ3 አመት ፅኑ እስራት እና በብር 60,000 እንዲቀጣ ተወስኗል በማለት መረጃውን ያደረሰን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ነው።
345 viewsAlemshet, edited  12:19
ओपन / कमेंट
2022-05-15 11:44:19 በ"ፍትሕ"የቴሌቪዥን ፕሮግራማችን "የቋሚ ንብረት ምዝገባ እና ስመ-ንብረት ዝወውር" በተመለከተ ሕጉ ምን ይላል? በአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የሰነዶች የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና የጠበቆች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ዮሐንስ ተገኘ ማብራሪያ በቅርብ ቀን በአሚኮ ቴሌቪዥን ይቀርባል።ይጠብቁን?
345 viewsAlemshet, edited  08:44
ओपन / कमेंट
2022-05-14 14:36:00
በህጻናት ጋብቻና በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ የፍትሕ፣የፀጥታ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ሚና በሚል በእንጅባራ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ውይይቱ የክልል የሚመለከታቸውን ዐቃብያነ ሕግ እና በምስራቅ አማራ በዩኒሴፍ ለታቀፉ ወረዳዎች የተውጣጡ ዐቃብያነ ሕግንና የፖሊስ አባላትን ያሳተፈ ነው።

የአማራ ክልል ፍትሐ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዝጋለ ገበየሁ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር አድርገው የመወያያ ፅሁፎች በዳይሬክተሮች ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ነው።
389 viewsAlemshet, edited  11:36
ओपन / कमेंट
2022-05-14 04:13:25
በአሚኮ ቴሌቪዥን "ፍትሕ" ኘሮግራማችን "የሚዲያ አጠቃቀም እና ሕግ ላይ" የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አያሌው አባተ ማብራሪያ ግንቦት 7 ቀን 2014ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ይቀርባል። ተመልክተው አድምጠው አስተያየት ይስጡን?
390 viewsAlemshet, edited  01:13
ओपन / कमेंट
2022-05-14 03:54:39
በአማራ የክልል ፍትሕ ቢሮ የፍታብሔር ዐቃቤ ሕግ በሆኑት አቶ አረጋ የእኔአለም በፍትሕ ኘሮግራማችን "በነፃ የሕግ አገልግሎት ላይ" ግንቦት 7 ቀን 2014ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጀምሮ በመደበኛው አማራ ሬዲዮ እና በኤፍ ኤም ጣቢያዎች ማብራሪያ ይቀርባል።አዳምጠው አስተያየት ይስጡን?
381 viewsAlemshet, edited  00:54
ओपन / कमेंट
2022-05-11 06:15:08 https://www.facebook.com/103843377867774/posts/531252335126874/?sfnsn=mo
309 viewsAlemshet, 03:15
ओपन / कमेंट