2022-05-31 07:56:14
ከሰሜን ሸዋ እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ፍትሕ መምሪያና ጽ/ ቤቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዐቃብያነ ሕግ ስልጠና ተሰጠ።
ድህነትን ለመቅረፍ በሙሉ አቅም ወደ ልማት መግባት ያስፈልጋል። ወደ ልማት ለመግባት ደግሞ ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊረጋገጥ ይገባል።
በመሆኑም ዘላቂ ሰላም በማምጣት ወደ ልማት ለመግባት እና ድህነትን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ዩ ኤን ዲ ፒ /United Nations Development Programe/ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር ስራዎችን ለመስራት የቴክኒክና የበጀት ድጋፍ በማድረግ ወደ ስራ መግባቱን የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አያሌው አባተ ገልጸዋል።
ዶ/ር አያሌው አባተ አክለውም ማህበረሰብ አቀፍ የግጭት አወጋገድ ዘዴዎችን በመተግበር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚሰራ እና ከዚህ በፊት ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች የመልሶ መገንባት ስራዎችን መንግስታዊ ተቋማት ያከናውኑ ዘንድ ተቋማዊ አቅማቸውን ማሳደግ፣ የማህበረሰብ የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረግ፣ ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ቅድመ መከላከል ማድረግ ፤ጉዳት የደረሰባቸውን ድጋፍና ክብካቤ በማድረግ ጉዳያቸውን ወደ ሕግ በመውሰድ ፍትሕ እንዲያገኙ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በዚህ የውይይት መድረክ የዩ ኤን አይ ዲ ፕ ፕሮፋይል፣ዓላማው፣የሚጠበቅ ውጤት፣የበጀት ድልድል ቀመር፣ሰለ አፈጻጸምና ሪፖርት፣ክትትልናቁጥጥር እንዲሁም የአሰራር ስርዓት ምንነትና አተገባበር በሚሉ ነጥቦች ላይ ገለጻና ውይይት ተደርጓባቸዋል።
399 viewsAlemshet, edited 04:56