Get Mystery Box with random crypto!

ከሰ/ሸዋ እና ከኦሮሞ ብሔ/አስ/ዞን ፍትህ መምሪያና ጽ/ ቤቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዐቃብያነ ህግ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

ከሰ/ሸዋ እና ከኦሮሞ ብሔ/አስ/ዞን ፍትህ መምሪያና ጽ/ ቤቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ዐቃብያነ ህግ ስልጠና ተሰጠ።
ድህነትን ለመቅረፍ በሙሉ አቅም ወደ ልማት መግባት ያስፈልጋል። ወደ ልማት ለመግባት ደግሞ ዘላቂ የሆነ ሰላም ሊረጋገጥ ይገባል።
በመሆኑም ዘላቂ ሰላም በማምጣት ወደ ልማት ለመግባት እና ድህነትን ለመቅረፍ ይቻል ዘንድ ዩ ኤን ዲ ፒ /United Nations Development Programe/ ከአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በትብብር ስራዎችን ለመስራት የቴክኒክና የበጀት ድጋፍ በማድረግ ወደ ስራ መገባቱን የአማራ ክልል ፍትህ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዷ/ር አያሌው አባተ ገልጸዋል።
ዷ/ር አያሌው አባተ አክለውም ማህበረሰብ አቀፍ የግጭት አወጋገድ ዘዴዎችን በመተግበር ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማምጣትበሚቻልበት ሁኔታ ላይ እንደሚሰራ እና ከዚህ በፊት ግጭት ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች የመልሶ መገንባት ስራዎችን መንግስታዊ ተቋማት ያከናውኑ ዘንድ ቸቋማዊ አቅማቸውን ማሳደግ፣ የማህበረሰብ የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከር ማድረግ፣ ለጉዳት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጉዳት እንዳይደርስባቸው ቅድመ መከላከል ማድረግ ፤ጉዳት የደረሰባቸውን ድጋፍና ክብካቤ በማድረግ ጉዳያቸውን ወደ ህግ በመውሰድ ፍትህ እንዲያገኙ   የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በዚህ የውይይት መድረክ የዩ ኤን አይ ዲ ፕ ፕሮፋይል፣ዓላማው፣የሚጠበቅ ውጤት፣የበጀት ድልድል ቀመር፣ሰለ አፈጻጸምና ሪፖርት፣ክትትልናቁጥጥር እንዲሁም የአሰራር ስርዓት ምንነትና አተገባበር በሚሉ ነጥቦች ላይ ገለጻና ውይይት ተደርጓባቸዋል።