2022-05-18 11:11:52
በሰው መጥለፍ/ማገት/ መግደል ወንጀል የተከሰሰው በ25 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ
ተከሳሽ አበበ ዳኘው ታህሳስ 24.4.2013 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 3:00 ሰአት ሲሆን ጭልጋ ወረዳ አይከል ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ቀጠና 3 ሞላ አጃው ይላቅ የተባለ የ15 አመት ህፃን ልጅ በኃይል በጦር መሳርያ ጠልፎ ወደ ቤዛሆ መቀነት ቀበሌ ከወሰደ በኋላ በስልክ ወደ ሟች ታጋች ህፃን ቤተሰብ በመደወል ብር 100,000 ክፈሉ ካልከፈላችሁ ግን ህፃኑን እገድለዋለሁ በማለት ካነጋገራቸው በኋላ እንዲሰጠው የጠየቀው ብር አልተላከልኝም በሚል ህፃን ሞላ አጃው ይላቅን ገድሎ ገደል ውስጥ ጥሎት ጥር 2 ቀን 2013 ዓ.ም ተገኝቷል። የጭልጋ ወረዳ አይከል ከተማ አስተዳደር ፓሊስ ጽ/ቤት በሰው ማገት እና ሰው መግደል ወንጀል ምርመራ አጣርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ መዝገቡን መርምሮ የኢ ፌ ዲ ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 590/2/ሠ / እና 539/1/ሀ/ በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ መስርቶ በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ በ1/9/2014 ዓ/ም በዋለው የወንጀል ችሎት ጥፋተኛ ተብሎ በ25 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ተወስናል በማለት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ መረጃውን አድርሶናል።
220 viewsAlemshet, edited 08:11