Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 58

2022-06-15 04:52:24
በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ከUNDP በተገኘ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ "ነፃ የሕግ ድጋፍ አገልግሎት የሴቶችን መብት ለማረጋገጥ" በሚል መሪ ቃል በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች፣የሴቶችና ህፃናት ኃላፊና ባለሙያ እንዲሁም የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት በተገኙበት ስልጠና ሰጠ

(ሰኔ 7 ቀን2014ዓ.ም) በስልጠናና የአጋር አካላት ውይይቱ ላይም የወረዳው ም/አስተዳዳሪ ወ/ሮ ሐዋ መሐመድ የተገኙ ሲሆን የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ፕሮግራሙን በይፋ አስጀምረዋል።

በተጨማሪም በስልጠናው ላይ ከተለያዩ ቀበሌዎች የተወጣጡ ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ እና ጉዳያቸው እልባት ያላገኙላቸው ሴቶችና ቤተሰቦች የተገኙ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ሰፊ ውይይት ከተካሄደ በኃላ የመፍትሔ አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል።

በመጨረሻም በሴቶችና ህፃናት፣ በፖሊስ እና በፍትሕ ጽ/ቤቶች መካከል ሊኖር የሚገባውን የመረጃ ልውውጥ ፎርማቶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸው በመረጃ ቅብብል ፎርማቶቹ መሰረት ተግባራትን ልንከውን እንደሚገባ ከስምምነት ላይ ተደርሷል።
332 viewsAlemshet, edited  01:52
ओपन / कमेंट
2022-06-13 21:10:20

228 viewsAlemshet, 18:10
ओपन / कमेंट
2022-06-13 17:06:03 https://www.facebook.com/1490190331223441/posts/pfbid0WWwWfxT5CuBX2jA3Ug5DZsmZaSRUpmopqW3W5uMdWVmqg3xpUr8asuq7qdAwxUPsl/?sfnsn=mo
294 viewsAlemshet, 14:06
ओपन / कमेंट
2022-06-13 14:14:23
የመንዝ ጌራ ምድር ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ከተዘዋዋሪ ብድር ማስመለስ ጋር ተያይዞ በሁለቱም ወረዳዎች ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ማስመለስ ችሏል።
307 viewsAlemshet, edited  11:14
ओपन / कमेंट
2022-06-12 21:25:53
በምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ 25 ወረዳዎች የሚገኙ የወሳኝ ኩነቶች ባለሙያዎች፣ የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የፍትሕ ጽ/ቤት ኃላፊዎች፣ የጤና ኃላፊዎች በተገኙበት በወሳኝ ኩነቶች ስራዎቻችንና በሕግ የበላይነት ማስከበር ላይ የአንድ ቀን ስልጠና መስጠት ተችሏል።የስልጠና ወጪዎችን ጤና መምሪያ እንዲሸፍን በማድረግ የተሻለ ግንዛቤ ማስጨበጥ ተችሏል።
97 viewsAlemshet, edited  18:25
ओपन / कमेंट
2022-06-12 21:10:22 ዮ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባበር በ"ፍትሕ" የቴሌቪዥን ኘሮግራማችን የውክልና ሕግን በተመለከተ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የክልል ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ ዘላለም ከፋለ እና ወ/ሮ ናርዶስ ጥላሁን በአሚኮ ቴሌቪዥን ቀርበው የሰጡት ማብራሪያ መሉውን ኘሮግራም ያዳምጡ።

112 viewsAlemshet, edited  18:10
ओपन / कमेंट
2022-06-12 16:42:51 ዮ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባበር በ"ፍትሕ" የሬዲዮ ኘሮግራማችን የኢንቨስትመንት አዋጁ ለባለሃብቶች የሚሰጠው ጥበቃና ከለላ ምን ይመስላል? የባለሃብቶች መብትና ግዴታዎች ምን ምን ናቸው? በሚል ጉዳይ ሕጉ ምን ይላል በሚል የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የክልል ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ ዳኝነት ይግዛው በአማራ ሬዲዮ እና በኤፍኤም ጣቢያዎች ቀርበው የሰጡት ማብራሪያ ሙሉውን ይከታተሉ?

208 viewsAlemshet, 13:42
ओपन / कमेंट
2022-06-12 05:51:45
በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በደዋ ጨፋ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት የወንጀል ተጠቂ(ተጋላጭ) በሆኑ ሴቶች እና ህፃናት መብቶች ዙሪያ ለአጋር አካላት የተሰጠ ስልጠና
147 viewsAlemshet, edited  02:51
ओपन / कमेंट
2022-06-12 05:30:11
በሰሜን ሸዋ ዞን ሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽ/ቤት በ "UNDP" በጀት በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚፈፀመው የኃይል ጥቃት ወንጀሎችን ለመከላከልና እና ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሰጥቷል።
152 viewsAlemshet, edited  02:30
ओपन / कमेंट
2022-06-12 05:22:07
በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ሰኔ 03/2014 ዓ.ም ከUNDP በተገኘ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ለሰሜን ሸዋ ዞን አጎራባች ከሆኑ 9 (ዘጠኝ) የወረዳው ቀበሌዎች ውስጥ ለሚገኙና ከዚህ ቀደም በብሔረሰብ ግጭቱ ብሎም በወራሪው ምክንያት ለማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ሥነ ልቦናዊና አካላዊ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ከእያንዳንዱ ቀበሌ ለተወጣጡ 7 ግለሰቦች (5 ሴት እና 2 ወንድ) በድምሩ 63 ሰዎች በፆታዊ ጥቃት፣በቤተሰብ ሕግ እንዲሁም በገጠር መሬት ሕጎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና መብቶቻቸውን ስለሚያስከብሩባቸው፣ የሁልጊዜም አገልጋያቸው ስለሆነው የፍትሕ ጽ/ቤት ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በመድረኩም አዎንታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፤ የታዳሚውንም አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ይመልሳሉ ተብለው የተጋበዙ የወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተው ተሳታፊውን ሁልጊዜም ከጎናችሁ እንሆናለን ብለው አበረታተዋል።

በመድረኩም ከግንዛቤ ማስጨበጥ በመቀጠል ተሳታፊዎች ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣የፆታዊ ጥቃት ጥቆማዎችን እንዲሰጡ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ ለጥቆማዎቻቸው አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ ለአርጡማ ፉርሲ ፍትሕ ጽ/ቤት የቤት ስራ ሰጥተዋል።
131 viewsAlemshet, edited  02:22
ओपन / कमेंट