Get Mystery Box with random crypto!

የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
टेलीग्राम चैनल का लोगो amharaattorney — የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU
चैनल का पता: @amharaattorney
श्रेणियाँ: राजनीति
भाषा: हिंदी
ग्राहकों: 2.34K

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


नवीनतम संदेश 61

2022-06-05 18:03:50
ጠበቆችን ላይ የሚታዮ የሥነ-ምግባር ጉድለቶች በማስተካከል ኀብረተሰቡን የፍትሕ ተጠቃሚ ለማድረግና የፍትሕ ስርዓቱ ከብልሹ አሰራር የፀዳ ለማድረግ እንደሚሰራ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ።ዝርዝሩን ከአሚኮ የቴሌቪዥን ዜና ይከታተሉ።
280 viewsAlemshet, edited  15:03
ओपन / कमेंट
2022-06-04 14:49:34 "የፍትሕ ሥርዐቱ የሚዘምንበትን መንገድ አልሞ መሥራት አስፈላጊ ነው" የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ አቶ ገረመው ገብረጻድቅ

ባሕር ዳር: ግንቦት 27/2014 ዓ.ም የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ከጠበቆች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በፍትሕ ሥርዐቱ ዙሪያ ምክክር አካሂዷል።

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገረመው ገብረጻድቅ
የፍትሕ ሥርዐቱ የሚዘምንበትን መንገድ አልሞ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል።

የጥብቅና ሥራ ለፍትሕ ሥርዐቱ መጎልበት አንድ ክንፍ ነው ያሉት አቶ ገረመው ጠበቆች ያለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት አስተዋጽኦ ማበርከት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የአማራ ክልል ጠበቆች ማኀበር ፕሬዚዳንት ኃይለየሱስ ደምሴ ሁሉም አካል ለፍትሕ ሥርዐቱ መሻሻል ኃላፊነት መውሰድ አለበት ብለዋል።

ጠበቆች ሥራቸውን በሚያከናውበት ወቅት ክፍተት እንዳይፈጠር በመተዳደሪያ ደንባቸው መመራት እና የሕግ የበላይነትን ማስጠበቅ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

አቶ ኃይለየሱስ ባልተገባ ግንኙነት ችግር በፈጠሩ ጠበቆች ላይ ከማስጠንቀቂያ እስከ ፈቃድ መንጠቅ የሚደርስ ውሳኔ መተላለፉን አመልክተዋል፡፡ በቀጣይ ችግሩን ለማስወገድ እንደሚሠሩም ተናግረዋል።

በባሕር ዳር ከተማ ፣ በአማራ ክልል እና በፌዴራል ፍርድ ቤቶች ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ እንዲሁም የማህበሩ አባል ጠበቃ ገበያው ይታየው በፍትሕ ሥርዐቱ የሚያልፉ የክርክር ሂደቶች፣ ክርክሮች የሚዳኙበት ሁኔታ፣ የሚወስዱት ጊዜ ለፍትሕ መጓደል መንስኤ ናቸውም ብለዋል።

ፍትሕ ሲጓደል ሊመጣ የሚችለውን ማኀበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የሥነ-ልቦና ውድቀት ለመቅረፍ ጠበቆች ሕግ ማስፈጸም ብቻ ሳይሆን በሕግ ማርቀቅ ሂደቱ ተሳታፊ መሆን እንደሚገባቸውም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ከ800 በላይ ጠበቆች ፍቃድ ወስደው አገልግሎት እየሠጡ ቢሆንም የሥነ-ምግባር ችግር ያለባቸው ጥቂት ጠበቆች ከተቀመጠላቸው የአሠራር ሥርዐት ውጭ ሲሰሩ በመገኘታቸው ለልዩ ልዩ ቅጣቶች መዳረጋቸውን ከቢሮው የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
(አሚኮ)
225 viewsAlemshet, 11:49
ओपन / कमेंट
2022-06-04 14:49:07
216 viewsAlemshet, 11:49
ओपन / कमेंट
2022-06-03 12:53:26
ዮ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባበር እሁድ ግንቦት 28 ቀን 2014ዓ.ም ከምሽቱ 2:30 ሰዓት ጀምሮ በ"ፍትሕ" የቴሌቭዥን ኘሮግራማችን "የልማት ተነሽዎች የካሣ አከፋፈል ሕጉ ምን ይላል?" በሚል ርዕስ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የክልል ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ መሉጌታ አሻግሬ በአሚኮ ቴሌቪዥን ማብራሪያ ይሰጣሉ።አዳምጠው ተመልክተው አስተያየት ይስጡን?
360 viewsAlemshet, edited  09:53
ओपन / कमेंट
2022-06-02 10:12:51
በአዊ ብሔረሰብ ዞን የተያዙ ፎርጅድ ማህተሞች
229 viewsAlemshet, edited  07:12
ओपन / कमेंट
2022-06-02 04:33:58
381 viewsAlemshet, 01:33
ओपन / कमेंट
2022-06-02 04:33:53 ሕገ-ወጥ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኀንን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ምንም ዓይነት የብሮድካስት ፍቃድ ሳይኖራቸው የህዝቡን ሰላምና ደህንነት የሚያናጉ በብሄር እና በሀይማኖት ጉዳዮች ላይ ግጭት ቀስቃሽ መረጃ የሚያሰራጩ እንዲሁም በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ መንግስትና ህዝብን ለመለያየት ሌት ተቀን የሚሰሩ 111 (አንድ መቶ አስራ አንድ) ሕገ-ወጥ የበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውን ባሰባሰበው መረጃ አረጋግጧል።

ከዚህ ውስጥ በጣም ወጣ ያሉ ብሄርን ከብሄር ሃይማኖትን ከሃይማኖት በማጋጨት የሀገርን ሰላምና ደህንነት ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱትን ለይቶ 10 (አስር) ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው ይገኛል።

እነዚህ ግለሰቦች የተለያዩ ግጭት ቀስቃሽ አጀንዳዎችን በመቅረጽ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት እንዳይረጋጋ የጥላቻ ንግግር በማሰራጨት በብሄር እና በሀይማኖት መካከል ጥርጣሬ እንዲፈጠር ሲያደርጉ የቆዩ መሆናቸው ይታወቃል።

ተቋሙ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገው ክትትል ግለሰቦቹ ምንም አይነት ህጋዊ ፍቃድ የሌላቸውና በመገናኛ ብዙሃን አዋጅ ቁጥር 1238/2013 መሰረት ያልተመዘገቡ መሆናቸውን ከኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ባሰባሰበው መረጃ ማረጋገጥ ችሏል። ግለሰቦቹ የሚዲያ ተከታዮቻቸውን በመጠቀም ሐሰተኛና ግጭት ቀስቃሽ መረጃዎችን የሚያሰራጩት በክፍያ እንደሆነም በምርመራ ደርሶበታል።

በየትኛውም ሚዲያ ተጠቅመው መረጃን ለህዝብ ተደራሽ የሚያደርጉ ግለሰቦች የሀገሪቱን ህግና ሥርዓት አክብረው መንቀሳቀስ እና ህጋዊ መስመር በመከተል በተጠያቂነት መንፈስ መስራት ይኖርባቸዋል። ፖሊስም ህግን አክብረው በማይሰሩት ላይ የጀመረውን ምርመራ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማሳሰብ ይወዳል፡፡

በመጨረሻም ህብረተሰቡ ያገኘውን መረጃ ሁሉ ከመጠቀም በመቆጠብ በጥንቃቄ መርምሮ ማየትና ማገናዘብ እንዳለበት እያሳሰበ በህገ ወጥ መንገድ በበይነመረብ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት አጀንዳ ቀርፀው በሀይማኖት፣ በብሄር ህብረተሰቡን ለማጋጨት የሚሰሩ አከላትን በማጋለጥና ለህግ አሳልፎ በመስጠት ሀገራዊ ግዴታውን መወጣት ይኖርበታል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ለህዝብ ሲገለጽ እንደነበረው ከሌሎች የጸጥታና የፍትህ አካላት ጋር በመቀናጀት የጀመረውን የህግ ማስከበር ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያስታውቃል።

ግንቦት 24 ቀን 2014 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ
372 viewsAlemshet, 01:33
ओपन / कमेंट
2022-06-01 21:04:47 https://www.facebook.com/100066914805321/posts/341255858114905/?sfnsn=mo
131 viewsAlemshet, 18:04
ओपन / कमेंट
2022-06-01 16:45:35
የሐሰተኛ ሰነድ ቁጥጥርን ለማጠናከር የባለድርሻ አካላት ድጋፍ ያስፈልጋል ተባለ

የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ በሰነድ ማረጋገጥና መመዝገብ ስራ ላይ የሐሰተኛ ሰነዶች መበራከት አዳጋች ተግዳሮት ቢሆንበትም በከፍተኛ ትኩረት እየሰራበት እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

የህግ ጉዳዮችና ሰነዶች ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ አሰፋ እንደገለጹት ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ሲሉ ሐሰተኛ ሰነዶችን በመያዝ ወደ ተቋማችን የሚመጡ ግለሰቦች በርካታ ቢሆኑም እየተወሰደ ባለው ጠንካራ ክትትል አበረታች ውጤት እየታየ መምጣቱን አስረድተዋል፡፡

ዳይሬክተሩ እንደተናገሩት በሐሰተኛ ሰነድ ለመገልገል ከሚመጡና እጅ ከፍንጅ ተይዘው ፍርድ ቤት ቀርበው ጉዳያቸው የታየና እየታየ ያለ ሲሆን በአገልግሎት ወቅት መረጃቸው ሲጣራ ለማምለጥ የሚሞክሩትን ለመያዝ የፖሊስ በቦታው አለመኖር ቁጥጥሩን ፈታኝ አድርጎታል ብለዋል::ሐሰተኛ ሰነድን በማቅረብ ተይዘው በሚመሰከርባቸው ወንጀለኞች ላይ ምስክር የሚሆኑ ግለሰቦች በራሳቸው ወጪ ለምስክርነት መቅረብ፣ የሚያቀርቡት ሰነድ ከጅምሩም ሐሰተኛ በመሆኑ ለፖሊስ ክትትል አስቸጋሪ መሆኑን አንስተዋል፡፡በ9 ወራት ውስጥ 303 መታወቂያ፣ 12 የጋብቻ ማስረጃ ፣ 111 ያላገባ ማስረጃ.፣ 8 የውክልና ሰነድ፣ እና ሌሎች ሰነዶችን ጨምሮ በአጠቃላይ በተቋሙ 444 ሐሰተኛ ማስረጃዎች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ በማድረግ ሊደርስ የነበረ ጉዳት ለማስቀረት ተችሏል ሲሉ አቶ ተስፋዬ ገልጸዋል፡፡ በመሆኑም በሐሰተኛ ሰነዶች ምክንያት የግለሰቦች ንብረት የማፍራት መብት እየተጣሰ በመሆኑ የሚመለከታቸው የፍትህ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩበት ይገባል ሲሉ አክለው ተናግረዋል፡፡

መስሪያ ቤቱ ሐሰተኛ ሰነዶችን ለመከላከል በህግ አግባብና በቴክኖሎጂ መጠነሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡
226 viewsAlemshet, 13:45
ओपन / कमेंट
2022-05-31 14:34:23 ዮ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ የገንዘብ ድጋፍ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ጋር በመተባበር በ"ፍትሕ" የሬዲዮ ኘሮግራማችን የገጠር መሬት ባለቤት ማነው መብትና ግዴታዎችን በተመለከተ ሕጉ ምን ይላል? የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የክልል ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ አንቲገኝ መርሻ በአማራ ሬዲዮ እና በኤፍኤም ጣቢያዎች ማብራሪያ

362 viewsAlemshet, 11:34
ओपन / कमेंट