Get Mystery Box with random crypto!

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ሰኔ 03/2014 ዓ.ም ከUNDP በተገኘ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ሰኔ 03/2014 ዓ.ም ከUNDP በተገኘ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ ለሰሜን ሸዋ ዞን አጎራባች ከሆኑ 9 (ዘጠኝ) የወረዳው ቀበሌዎች ውስጥ ለሚገኙና ከዚህ ቀደም በብሔረሰብ ግጭቱ ብሎም በወራሪው ምክንያት ለማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ሥነ ልቦናዊና አካላዊ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ከእያንዳንዱ ቀበሌ ለተወጣጡ 7 ግለሰቦች (5 ሴት እና 2 ወንድ) በድምሩ 63 ሰዎች በፆታዊ ጥቃት፣በቤተሰብ ሕግ እንዲሁም በገጠር መሬት ሕጎች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና መብቶቻቸውን ስለሚያስከብሩባቸው፣ የሁልጊዜም አገልጋያቸው ስለሆነው የፍትሕ ጽ/ቤት ግንዛቤ ተፈጥሯል።

በመድረኩም አዎንታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ፤ የታዳሚውንም አስተዳደራዊ ጥያቄዎች ይመልሳሉ ተብለው የተጋበዙ የወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ እና የአስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተው ተሳታፊውን ሁልጊዜም ከጎናችሁ እንሆናለን ብለው አበረታተዋል።

በመድረኩም ከግንዛቤ ማስጨበጥ በመቀጠል ተሳታፊዎች ጥያቄዎችን እንዲጠይቁ፣የፆታዊ ጥቃት ጥቆማዎችን እንዲሰጡ ተደርጓል። በዚህም መሰረት ለጥያቄዎቻቸው ምላሽ ለጥቆማዎቻቸው አስፈላጊው ክትትል እንዲደረግ ለአርጡማ ፉርሲ ፍትሕ ጽ/ቤት የቤት ስራ ሰጥተዋል።