Get Mystery Box with random crypto!

በህጻናት ጋብቻና በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ የፍትሕ፣የፀጥታ እ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በህጻናት ጋብቻና በሴት ልጅ ግርዛት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል ረገድ የፍትሕ፣የፀጥታ እንዲሁም የባለድርሻ አካላት ሚና በሚል በእንጅባራ ከተማ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

ውይይቱ የክልል የሚመለከታቸውን ዐቃብያነ ሕግ እና በምስራቅ አማራ በዩኒሴፍ ለታቀፉ ወረዳዎች የተውጣጡ ዐቃብያነ ሕግንና የፖሊስ አባላትን ያሳተፈ ነው።

የአማራ ክልል ፍትሐ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዝጋለ ገበየሁ ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ንግግር አድርገው የመወያያ ፅሁፎች በዳይሬክተሮች ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ነው።