Get Mystery Box with random crypto!

በሀሰተኛ ሰነድ/መታወቂያ/መገልገል ወንጀል የተከሰሰው በ2 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በብር | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በሀሰተኛ ሰነድ/መታወቂያ/መገልገል ወንጀል የተከሰሰው በ2 አመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት እና በብር 40,000 እንዲቀጣ ተወሰነ
ተከሳሽ ዋሲሁን እረብሶ ወዳጆ ለራሱ ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በጎንደር ከተማ አስተዳደር  በሽሮ ሜዳ ቀበሌ በመታወቂያ ቁጥር 03/መ. ቁ 27400 በቀን 30.4.2013 ዓ.ም እንደተሰጠው  በማስመሰል በሀሰት የተዘጋጀ ሀሰተኛ የነዋሪነት የቀበሌ መታወቂያ በመያዝ ታህሳስ 7.04.2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8:30 ሰአት ሲሆን በጎንደር ከተማ አስተዳደር ሽሮ ሜዳ ቀበሌ በሐሰት የተዘጋጀውን መታወቂያ ለማሳደስ ሲል በቀጥታ የተያዘ በመሆኑ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምርያ 3ኛ ፓሊስ ጣቢያ በሰው እና በሰነድ ማስረጃ ምርመራ አጣርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሒደት በመላክ የዞን ዐቃቤ ሕግ የተላከለትን መዝገብ መርምሮ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23/3/የተመለከተውን በመጥቀስ ክስ መስርቶ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ቆይቶ በ28.8.2014 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት  ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ2 አመት ከ6 ወር እስራት እና በብር 40,000 እንዲቀጣ ተወስኗል በማለት መረጃውን ያደረሰን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ነው።