Get Mystery Box with random crypto!

የሀዘን መግለጫ በምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ የመተማ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት የፍትሐብሄር የ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የሀዘን መግለጫ

በምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ የመተማ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት የፍትሐብሄር የስራ ሒደት አስተባባሪ እና ዐቃቤ ሕግ የሆኑት አቶ ኢዮኤል መንገሻ ባደረባቸው ድንገተኛ ህመም ጎንደር ዩኒቨርስቲ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና ድጋፍ ሲደረግላቸው ቆይቶ ዛሬ ግንቦት 08 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።

አቶ ኢዮኤል መንገሻ በዐቃቤ ሕግ ሙያቸው በቋራ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን ህብረት ስራ ማህበር የሕግ ባለሙያነት እና አሁን በህይወት አሰከተለዩበት ድረስ የመተማ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት የፍትሐብሄር የስራ ሒደት አስተባባሪ ሆነው ሲያገለግሉ ነበር።

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ፣ምዕራብ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ፣የመተማ ወረዳ ፍትሕ ጽ/ቤት ዐቃቤያነ ሕግና የአስተዳደር ሰራተኞች በሙሉ ለቤተሰቦቹ ፣ ለጓደኞቹ ፣ ለስራ ባልደረቦቹ ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹ መፅናናትን ይመኛሉ።