Get Mystery Box with random crypto!

አሸናፊ ሞሱ የተባለ ግለሰብ በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ ወጀል ከተማ ላይ መደበኛ የመኖሪያ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

አሸናፊ ሞሱ የተባለ ግለሰብ በምስራቅ ጎጃም ዞን አዋበል ወረዳ ወጀል ከተማ ላይ መደበኛ የመኖሪያ ቦታውን በማድረግ ከተቀመጠ በኋላ ለተለያዩ ግለሰቦች የትምህርት ማስረጃ፣ፓስፖርት፣የህክምና ማስረጃ እና መንጃ ፈቃድ በሀሰት እየሰራ ይሸጣል በሚል ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ መሰረት የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል ወደ ግለሰቡ የመኖሪያ ቤት በመሄድ በቁጥጥር ስር አውሎ ብርበራ ሲያደርግ ተሰርተው የተቀመጡ የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶች፤ለዚሁ ተግባር የሚያገለግሉ አንድ ላፕቶፕና አንድ ዴስክቶፕ እንዲሁም ቀለሞችንና ወረቀቶችን ያገኘ በመሆኑ ምርመራ አጣርቶ መዝገቡን ለምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ልኮታል፡፡የምርመራ መዝገቡ የደረሰው የዞኑ ፍትህ መምሪያ የስራ ሂደትም በተጠርጣሪው ላይ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 23/1 ን በመጥቀስ ክስ መስርቶበታል፡፡የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በቀረበው ክስ ላይ ሲያከራክር እና በምርመራ መዝገቡ የተያያዙ የሰነድ ማስረጃዎችን ሲመረምር ከቆየ በኋላ የተከሰሰበትን የወንጀል ድርጊት ስለመፈጸሙ ያረጋገጠ በመሆኑ ጥፋተኛ በማለት በ8 ዓመት ጽኑ እስራት እና በ5000 /አምስት ሽህ/ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጣ፤በኤግዚቪትነት የተያዙትን ላፕቶፕና ዴስክቶፕ ለመንግስት ገቢ እንዲሆኑ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡በመጨረሻም የምስራቅ ጎጃም ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት መሪ አቶ ያለለት ሙኔ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሲባል የሚዘጋጁ የሀሰተኛ ማስረጃዎች በሕዝብና በሀገር ላይ የሚያደርሱት ኪሳራ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑም በላይ ለህይወት መጥፋትም ዋነኛ ምክንያቶች በመሆናቸው የፍትህ ተቋማት በቅንጅትና በትብብር ትኩረት ሰጥተው በመስራት፤ህብረተሰቡም ጥቆማ በመስጠት በወንጀል ድርጊቱ የተሰማሩ ግለሰቦችን ወደ ህግ ማቅረብ ይገባል ብለዋል፡፡