Get Mystery Box with random crypto!

በስራ ተግባር የሚፈፀም የመዉሰድና የመሰወር የሙስና ወንጀል የተከሰሱት ግለሰቦች ተቀጡ፡፡ 1ኛ. ተ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በስራ ተግባር የሚፈፀም የመዉሰድና የመሰወር የሙስና ወንጀል የተከሰሱት ግለሰቦች ተቀጡ፡፡
1ኛ. ተከሳሽ ሳጅን መላኩ ምህረት የ5ኛ ሻለቃ የ3ኛ ሻንበል አዛዥ፣2ኛ ተከሳሽ የ5ኛ ሻለቃ የ3ኛ ሻንበል አስተዳደር 3ኛ. ተከሳሽ የ5ኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ በአብክመ ልዩ ኃይል ፖሊስ ተከዜ ክፍለ ጦር ሁነዉ ሲሰሩ የነበሩ ግለሰቦች በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/፣የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 15(1)(ለ) እና (3)ን በመተላለፍ የማይገባቸዉን ቁሳዊ ጥቅም ለራሳቸዉ ለማግኘት ወይም ለሌላ ሰዉ ለማስገኘት በማሰብ ሚያዚያ 28 ቀን 2014 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 8፡00 ስዓት በሚሆንበት ጊዜ በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ አይጥ ጀሮ ከሚባል ስፍራ የተከዜ ክፍለ ጦር የ5ኛ ሻለቃ የ3ኛ ሻንበል የልዩ ሃይል ፖሊስ አባላት በህግ ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ 2,304,000/ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ አራት ሽህ / ብር ከእነ ተጠርጣሪዎቹ ይዘዉ ለተከሳሾች አስረክበዋቸዉ ተከሳሾች ገንዘቡን ከተረከቡ በኋላ ገንዘቡን ሲያዘዋዉሩ የነበሩትን ግለሰቦች በአካባቢዉ በነበረዉ የልዩ ሃይል ካምፕ ለ2 ቀን አስረዉ ከቆዩ በኋለ ከተያዘዉ ገንዘብ ዉስጥ ለዐቃቤ ህግ ምስክር ለሆነዉ ግለሰብ 350,000/ሶስት መቶ ሃምሳ ሽህ /ብር በመመለስ ግለሰቦችን ፈትተዉ ከለቀቁ በኋላ ቀሪዉ ገንዘብ 3ኛ ተከሳሽ ወደ አለበት ካምፕ በመዉሰድ ገንዘቡ በህጋዊ መንገድ ወደ ሚመለከተዉ አካል ቀርቦ መቀመጥ እያለበት ተከሳሾች በመመሳጠር በአደራ የተረከቡትን ጥሬ ገንዘብ ከፊሉን የሰወሩት ከፊሉን ደግሞ የተከፋፈሉት በመሆኑ በፈፀመት በስራ ተግባር የሚፈፀም የመዉሰድና የመሰወር የሙስና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ስለሆነም የጃናሞራ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የሙስና ወንጀል ምርመራ ክፍል አጣርቶ የላከውን መዝገብ የሰሜን ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ክስ መስርቶበት የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲያከራከር ከቆየ በኋላ ተከሳሾች በመከላከያ ምስክሮች ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸዉ ፍርድ ቤቱ መጋቢት 28/2015 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሾችን ያስተምራል፤ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ያለዉን ለእያንዳንዳቸዉ የ9 ዓመት ፅኑ እስራት እና 3,000/ሶስት ሽህ ብር ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡