Get Mystery Box with random crypto!

የማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የ2015 ዓ/ም    የ9 ወር እቅድ ክንውን የስራ አፈፃፀም | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የማእከላዊ ጎንደር ዞን ፍትህ መምርያ የ2015 ዓ/ም    የ9 ወር እቅድ ክንውን የስራ አፈፃፀም ገመገመ
     ፍትህ መምርያው በስሩ የሚገኙትን 24 የወረዳ እና ንኡስ ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የዞን የስራ ሒደት አስተባባሪዎች እና ባለመያዎች እንዲሁም የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምርያ እናየጣቢያ የምርመራ ክፍል ኃላፊ የተከሳሽ እና ምስክር አቀራረብ በተጨማሪ የማእከላዊ ጎንደር ዞን የምርመራ ክፍል ኃላፊ ፣ ተከሳሽ እና ምስክር አቀራረብ በተገኙበት በ27/7/2015ዓ/ም የአንድ ቀን ግምገማ ያካሔደ ሲሆን ከሰአት በፊት የመምርያውን እና የወረዳዎችን የ9 ወር አፈፃፀም ገምግሟል ከሰአት በኋላ ደግሞ የተከሳሽ እና ምስክር አቀራረብ ፣ የምርመራ ጥራት፣የ38/ሐ/ አተገባበረ ፣ ውስብስብ እና ከባድ ወንጀሎቾ የፓሊስ እና ዐቃቤ ሕግ የትብብር ፣ስራን መሰረት ያደረገ ጤናማ ግንኙነት ዙርያ መነሻ ያደረገ ግምገማ ተካሔዷል በግምገማው በጥንካሬ ከታዩት በወረዳ ደረጃ በፍታብሔር እና በወንጀል ብልሹ አሰራርን በመታገል የላቀ እንቅስቃሴ መኖሩን፣ ከፓሊስ ጋር በመተባበር በተከሳሽ እና ምስክር አቀራረብ ዙርያ የተዘጉ መዛግብት ማንቀሳቀስ፣ በሙስና ወንጀል ጉዳይ ለረጅም ጊዜ ለተጨማሪ ምርመራ የተላኩ መዛግብትን ተሟልተው እንዲመለሱ የተሰሩ ስራ ዎች በጥንካራ ከተገመገሙት ጥቂቶቹ ሲሆኑ በድክመት ደግሞ በተከሳሽ እና ምስክር አቀራረብ ዙርያ ተቆራርጦ አለመስራት ከዚህ ጋር በተያያዘ ከፓሊስም ሆነ ከዐቃቤ ሕግ የሚታይ የስነምግባር ችግር መኖሩ፣ የምርመራ ስራ የጥራት መጓል፣የሙስና መዛግብትን በሚመለከት በአንዳንድ ወረዳዎች ተቆራረጦ አለመስራት ፣ በጠለፋ እና በሕገወጥ የሰዎች ዝውውር እንዲሁም የጦር መሳርያ ዝውውር ላይ ሕገወጦችን በቀላሉ በዋስ መልቀቅ እና በአጠቃላይ የስነምግባር ችግር መታየት ዐቃቢያነ ሕግ በዞን ደረጃ በተለይ የልዩልዩ ወንጀል ጉዳይ የስራ ሒደት ወደችሎት ሲገባ በቂ ዝግጅት አድርጎ ጠንካራ ክርክር አለማደረግ ላይ ችግር ያለባቸው ባለሙያዎች መኖር በድክመት ከተገመገሙት ለአብነት የሚወሰዱ ናቸው በመጨረሻ በግምገማው የታዩትን ድክመቶች በማረም እና በጥንካሬ የተገመገሙትን ይበልጥ በማጠናከር ከፓሊስ ተቋማት ጋር ተባብሮ በመስራት የቀሪ 3 ወራት አፈፃፀምን ወጤታማ ለማደረግ የጋራ መግባባት ተደርሶ የለቱ ግምገማ ተጠናቋል።