Get Mystery Box with random crypto!

በ ጉግል ፎቶስ (Google Photos) - የእድሜ ልክ፣ ገደብ የለሽ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ | 𝐁𝐢𝐥𝐚𝐥 𝐓𝐞𝐜𝐡

በ ጉግል ፎቶስ (Google Photos) - የእድሜ ልክ፣ ገደብ
የለሽ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ!
----------------------------------
በካሜራዎ ላይ አንዳንድ ወሳኝ የሆኑ አፍታዎችን ለመያዝ ሞክረዉ
ዝቅተኛ ማከማቻ ስላልዎት ማንሳት አይችሉም የሚል ችግር
አልገጠምዎትም?
ጉግል ፎቶስ፣ ለዚህ ችግር ሁነኛ መፍትሄ
የሚሆን ያልተገደበ፣ የእድሜ ልክ፣ የፎቶ እና የቪዲዮ ማከማቻ
አገልግሎት ይዞ ብቅ ብሏል፡፡
ጉግል ለፎቶ(እስከ 16 ሜጋፒክስል) እና ቪድዮ(እስከ 1080ፒ
ባለ Full HD ድረስ) ያለገደብ ለእድሜ ልክ መጫን እና
ማስቀመጥ እንደሚቻል አስታዉቋል።
የ ጉግል ፎቶስ መተግበሪያ
በ Android, iOS, Mac እና Windows ጨምሮ በሌሎቸም
ፕላትፎርሞች ይገኛል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክዎ ላይ ይህን መተግበሪያ በሚከፍቱበት
ጊዜ, ለመጠባበቂያዎቹ (backup) የሚጠቀሙበትን የጉግል
መለያዎን (account/email) ይጠይቅዎታል።
አንዴ ከተዋቀረ
እና ከተስተካከለ በኋላ ስልክዎ ከ WiFi ጋር ሲገናኝ ሁሉንም
ፎቶዎች እና ቪድዮዎች መጠባበቂያ ላይ ያስቀምጣል።

መጠባበቂያዉ ላይ አስቀምጦ ከጨረሰ በኋላ ከስልክዎት ላይ
ማጥፋት እና የስልክዎን ማከማቻ መጠን ማሳደግ ይችላሉ።

በተጨማሪም፦
ሁሉንም ፎቶዎችዎን እና ቪድዮዎችዎን ለመጠባበቂያ
በሰጣችሁት መለያዎ ሲገቡ ከማንኛውም ኮምፒተር፣ ተንቀሳቃሽ
ስልክ ላይ ወይም ብሮውሰር ( photos.google.com
በመክፈት) ማግኘት እና ማየት ይችላሉ።

ፎቶዎትን መከርከም (cut)፣ ማሽከርከር (rotate) ወይም
ቀለሙን (color setting) ማስተካከል ካስፈለገዎት መሰረታዊ
የፎቶ አርትዖት በመተግበሪያው ውስጥ ራሱ ቀርቧል።
በኮምፒተርዎ ላይ የ Mac ወይም Windows መተግበሪያን
ማውረድ እና በጉግል ፎቶስ ላይ በጠቅላላ አለኝ የሚሏቸውን
ፎቶዎች ማስቀመጥ ይችላሉ፡፡ በሚፈልጓቸው ጊዜም ከጉግል
ፎቶስ ድህረ ገጽ ( photos.google.com ) ላይ በቀላሉ
ሊያገኟቸው ይችላሉ።

ይህን ከማድረግዎ አስቀድመዉ ግን ለመለያዎ በቀላሉ ሊገመት
የማይችል አስተማማኝ የይለፍ ቃል መስጠት እንዳለብዎት
እንመክራለን፡፡
እናም ይሄንን መንገድ በመጠቀም ስለስልክዎ
ማከማቻ መጠን እና ስልክዎ ሲጠፋ አብረዉ ስለሚጠፉት
ማስታወሻ ፎቶዎች መጨነቅ ያቁሙ ይለናል።