Get Mystery Box with random crypto!

በከባድ የዉንብድና ወንጀል የተከሰሱት ግለሰቦች ተቀጡ፡፡ ተከሳሽ ኮ/ል በልእስቲ ብርሃኑ ደረሰህ እ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በከባድ የዉንብድና ወንጀል የተከሰሱት ግለሰቦች ተቀጡ፡፡
ተከሳሽ ኮ/ል በልእስቲ ብርሃኑ ደረሰህ እና ኮ/ል ዉባረግ ላቀ ጎሹ የአማራ ልዩ ኃይል ሚኒሊክ ክፍለ ጦር አባላት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32/1/ሀ/ እና 671(1)(ለ) በመተላለፍ የማይገባቸዉን ብልፅግና ለራሳቸዉ ወይም ለሌላ አካል ለማስገኘት በማሰብ ታህሳስ 19/ 2015 ዓ/ም በግምት ከቀኑ 9፡00 ስዓት በሚሆንበት ጊዜ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ፍየል ዉሃ ንዑስ ወረዳ አዘነባ መዉጫ አሸዋዉ ከተባለዉ ቦታ ተከሳሾች በታጠቁት የመንግስት መሳሪያ በማስፈራራት የግል ተበዳይ አቶ ጥጋቡ ብርሃኔ የያዘዉን 100,000/ አንድ መቶ ሽህ/ ብር እና አቶ ክብረት ብርሃኔ ከአንገቱ ተጠቅሞ የነበረዉን 37 ግራም የብር ሃብል በጥሶ በመዉሰድ በፈፀሙት ከባድ የዉንብድና ወንጀል ተከሰዋል፡፡
ስለሆነም የጠለምት ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት የመደበኛ ወንጀል ምርመራ ክፍል አጣርቶ የላከውን መዝገብ የሰሜን ጎንደር ዞን ፍትህ መምሪያ የመደበኛ ወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት ክስ መስርቶበት የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲያከራከር ከቆየ በኋላ ተከሳሾች ተከላከሉ ተብለዉ ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸዉ ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 2/2015 ዓ/ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሾችን ያስተምራል፤ሌሎችንም ያስጠነቅቃል ያለዉን ለእያንዳንዳቸዉ በ16 ዓመት ከ6 ወር ፅኑ እስራት ቅጣት ወስኖባቸዋል፡፡