Get Mystery Box with random crypto!

የዲጂታል መታወቂያ ምንነት እና የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ዋና ዋና ገጽታዎች | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የዲጂታል መታወቂያ ምንነት እና የዲጂታል መታወቂያ አዋጅ ቁጥር 1284/2015 ዋና ዋና ገጽታዎች
ዘመናዊ የመታወቂያ ስርዓት በአንድ ሀገር ውስጥ ተግባራዊ ሲደረግ መሰረታዊ የሚባሉ ጠቀሜታዎች ያሉት ሲሆን፣ ከነዚህ ጠቀሜታዎች መካከልም ሃገራዊ ልማትን በአግባቡ ለማቀድ፣ ምጣኔ ሃብታዊ ሽግግር ለመፍጠር፣ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ የሀብት ብክነትን ለመቀነስ፣ ወንጀልን ለመከላከል፣ ፖሊሲዎች ሲቀረጹ እና የልማት ሥራዎች ሲከናወኑ ድግግሞሽን ለመቅረፍ እና አካታችነትን ለማጎልበት የሚረዳ መሆኑ የተረጋገጠ ነው፡፡