Get Mystery Box with random crypto!

የሕብረት ሥራ ማኅበራት በኢትዮጵያ መግቢያ አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ ኑሮውን መሰረት ያደረገው በ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የሕብረት ሥራ ማኅበራት በኢትዮጵያ
መግቢያ
አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ ኑሮውን መሰረት ያደረገው በግብርና ነው፡፡ ይህ የኑሮ ዘዴ አጋዥ የሆነ አሰራር እና ስርአት እንዲኖረው ማድረግ ያስፈልገዋል፡፡ ህዝቡ የራሱን የልማት ተግባር ለማከናወን ግንባር ቀደም ተዋናይ የሚሆንበት አደረጃጀት መኖር ያስፈልገዋል፡፡ የሕብረት ሥራ ማኅበራት በዚህ በኩል ዋና አማራጭ በመሆን የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ መድረኮች ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የሕብረት ሥራ ማኅበራትን በዘመናዊ መልኩ ማደራጀት ከተጀመረ 57 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ በመሆኑም የሕብረት ስራ ማኅበራት በአገራችን ፈጣን፣ ቀጣይና ፍትሐዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማትና ዕድገት ከማረጋገጥና የአባላትን ብሎም የህዝብን ተጠቃሚነት ከማሳደግ አንፃር ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ያከናውናሉ፡፡ በዚህም በከተማ እና በገጠር ለሚኖረው የህብረተሰብ ክፍል በርካታ ጠቀሜታዎች ይሰጣሉ።