Get Mystery Box with random crypto!

የሽግግር ፍትህ ጠቅላላ ጽንሰ ሃሳብ መግቢያ፡ በሀገረ መንግስት ግንባታ እና ለውጥ ዉ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የሽግግር ፍትህ ጠቅላላ ጽንሰ ሃሳብ
መግቢያ፡
በሀገረ መንግስት ግንባታ እና ለውጥ ዉስጥ በርካታ ኩነቶች ይከሰታሉ፡፡ የሰላም ጊዜ፤ የጦርነት ጊዜ፤ የድህነትና የብልጽግና ዘመን፤ ሁሉን ዓቀፍ እድገት፤ ሁሉን አቀፍ ውድቀት፤ የህግ የበላይነት የሰፈነበት በአንጻሩ የሰዎች የበላይነት የነገሰበት፤ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት፤ ሰላምና መረጋጋት፤ በዜጎች መካከል መፈቃቀር እንዲሁም አለመግባበቶች ሊከሰቱ የሚችሉ የገሃዱ ዓለም እውነታዎች ናቸው፡፡
በዚህ ሁሉ ሂደት ውስጥ የትኛውም የሀገር መንግስት ተቀዳሚ ተግባሩ የመንግስትን እና የዜጎችን ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ፤ እውነተኛ ፍትህን ማስፈን ነው፡፡ በሰላምና ጸጥታ የማስከበር ሂደት ውስጥ አንድ በኩል አጥፊዎች ተገቢውን ቅጣት ሲያገኙ በአንጻሩ ሰላማዊ የሆኑ ዜጎች የጥፋት ሰላባ ሆነው ፍትህ ሲጠይቁ ይስተዋላል፡፡
በሰላም ይሁን በጦርነት ጊዜ አላግባብ ሰብዓዊ መብታቸውን የተገፈፉ፤ ፍትሕ ያጡ፤ የአካል እና የሞራል ውድቀት የደረሳባቸው ዜጎች የሽግግር ፍትህ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታታ በርካታ ሀገራት የሽግግር ፍትህ ፖሊሲን በመቅረጽ ተግበራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵያ ሀገራችን የሽግግር ፍትህ ሥርዓትን ለመዘረጋት እና ተግባረዊ ለማድረገ ያለሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡
ስለሆነም በዚህ ጽሁፍ ስጠቅላላ የሽግግር ፍትህ ጽንሰ ሃሳብ ግንዛቤ ለማስጨበጥ እንሞክራለን፡፡