Get Mystery Box with random crypto!

ከሳሽ .......የጠ/ዐ/ህግ ተከሳሽ .....ደስታው ጥላሁን አባይ አድራሻ ...ዳባት ወረዳ አጅ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

ከሳሽ .......የጠ/ዐ/ህግ
ተከሳሽ .....ደስታው ጥላሁን አባይ አድራሻ ...ዳባት ወረዳ አጅሬ ቀበሌ
ተከሳሹ ካልተያዘ ግብረ አበሩ ጋር በመሆን ጥቅምት 2 ቀን 2014 ዓ/ም በጠገዴ ወረዳ ሸኒ ቀበሌ ልዩ ስሙ ፈንጥሮ በርሃ ላይ የግል ተበዳይ የሆኑትን 1ኛ ፈረንጁ አየነው 2ኛ አዲሱ ገብሬ አዝመራና ከብት እየጠበቁ እያለ ካልተያዘው ግብረ አበሩ ጋር በመሆን በያዘው ሰደፍ ክላሽ በማንገራገር እንዲሁም ከቤተሠብ ብር አስመጣ እያለ በመደብደብ ከፍተኛ እንግልት ሲያደርስባቸው ቆይቶ ጥቅምት 16 ቀን 2014 ዓ/ም ከምሽቱ 3:00 ሲሆን ሸኒ ቀበሌ አናሴ የተባለች ጎጥ ላይ 250000(ሁለት መቶ አምሳ ሽ) ብር ተቀብሎ ከ13 የእንግልት ቀናት በኋላ የግል ተበዳይን የለቀቃቸው ሲሆን የጸጥታ ሀይሉ ጠላፊውን ወደ ህግ ያቀረበ በመሆኑ የጠ/ወ/ ፍ/ጽ/ ቤት የወንጀል የስራ ሂደት ተጠርጣሪው ላይ የወንጀል ህግ አንቀጽ ቁጥር 290/1/(ሀ) እና /2/ (ሐ) ጠቅሶ ክስ ያቀረበ ሲሆን ተጠርጣሪው ክዶ የተከራከረ በመሆኑ አቃቤ ህግ ምስክሮችን አሰምቶ ፍርድ ቤት የተከላከል ብይን ሰጥቷል ተጠርጣሪው 6 የመከላከያ ምስክር አቅርቦ ያሰማ ቢሆንም መከላከል ባለመቻሉ የጠገዴ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀን 18/07/2015 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን ያርማል ሌሎችንም ያስተምራል ያለውን 13 ዓመት ፅኑ እስራት ወስኖበታል
   የጠገዴ ወረዳ ፍ/ጽ/ቤት