Get Mystery Box with random crypto!

በሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት እድሜያቸዉ ከ12 ዓመት በላይ ለሆ ኑ ከ6 | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከያ ክትባት እድሜያቸዉ ከ12 ዓመት በላይ ለሆ ኑ ከ6 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመከተብ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

የአብክመ ጤና ቢሮ የክትባት ክፍል አስተባባሪ አቶ ወርቅነህ ማሞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደተናገሩት የመጀመሪያ ዙር የኮቪድ-19 ክትባት በፀጥታ ችግር ምክንያት የተፈለገዉን ያክል መከተብ አለመቻሉን ገልፀዉ በሁለተኛ ዙር በተሻለ መልኩ የክትባት ዘመቻ እንደ ክልል በርካታ ጠንካራ ጎኖች የታዩበት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ሶስተኛው ዙር የኮቪድ-19 ክትባት ደግሞ ከሰኔ 02/2014 ዓ.ም ጀምሮ እድሜያቸዉ ከ12 ዓመት በላይ ለሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች በክልላችን በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳዎች እና ጤና ተቋማት ክትባቱ ይሰጣል፡፡

ክትባቱ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስቃይና ሞት የሚከላከል በመሆኑ አብዛኛዉን የህብረተሰብ ክፍል ለመከተብ መታቀዱን ገልፀዉ ክትባቱን በተባለዉ ቀን ለመጀመር ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አቶ ወርቅነህ አክለዉም የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በሚሰጠዉ መደበኛ ክትባት የጤና ባለሙያዎች በቡድን በመሆን ህዝብ በብዛት በሚገኝባዉ አካባዎች በትምህርት ቤቶች፣ ማረሚያዎች እና መጠለያ ካንፖች ተዘዋዉረዉ ክትባቱን ይሰጣሉ፡፡

የኮቮድ-19 ስራ የሁሉም ማበረሰብ እና ሴክተር መስሪያቤቶች ስራ በመሆኑ ለክትባቱ ስኬታማነት ርብርብ ያሰፈልጋል ብለዋል፡፡

ጤና ቢሮ