Get Mystery Box with random crypto!

ዮ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዩጵያ ድጋፍ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ያለበትን ሁኔታ የሚያ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

ዮ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዩጵያ ድጋፍ የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ያለበትን ሁኔታ የሚያሳይ ጥናት እና ስትራቴጅክ ዕቅድ ዝግጅት ስራ ማስጀመሪያ 'በጎግል ሚት' የመወያያ ማስተግበሪያ ዮ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ አማካሪዎች፣ የፍትሕ ቢሮ ኃላፊዎችና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ውይይት ተካሄደ። (ግንቦት 29 ቀን 2014ዓ.ም) በጥናቱ የቢሮው ስትራቴጂክ ዕቅድ ዝግጅት መነሻ ጥናት የሚካሄድ ሲሆን የሁኔታ ትንተና በማካሄድ ችግሮችን በመለየት ወደ ስራ ይገባል። ፍትሕ ቢሮ ካለው ኃላፊነት አኳያ ትንታኔ ይሰራል፣ኃላፊነቱን በማስፈፀም ያለበት ሁኔታ፣የውጪን የአጋር አካላት ሁኔታ፣ተቋሙ ያለበትን ደረጃ ሁኔታ ይመለከታል።ጥናቱ እና ስትራቴጂክ ዕቅዱ ሲዘጋጅ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት እና የዞን ፍትሕ መምሪያዎች በሚያሳትፍ መንገድ እንደሚከናወን በውይይቱ ተነስቷል። አማካሪዎች የተለያዮ መረጃዎችን ለስራቸው መጠቀም ሲፈልጉ በክልል ፍትሕ ቢሮ ሆነ በተዋረድ በሚገኙ የፍትሕ መምሪያዎች በፍጥነት መረጃዎችን በመስጠት ስራው በተቀመጠለት ጊዜ እንዲከናወን ሊያደርጉ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል። ለጥናቱ እና ለስትራቴጂክ ዕቅዱ ስራ አራት አማካሪዎች በሙያቸው በትምህርት ዝግጅታቸው በተግባር አፈፃፀማቸው የተሻለ አፈፃፀም ያላቸው ተመርጠው ወደ ስራ የገቡ ሲሆን በጥናት የሚለዮ ጉዳዮችን መለየት፣የአምስት አመት ስትራቴጂክ ዕቅድ ፣የ2015 በጀት ዓመት ዕቅድ ሳይንሳዊ በሆነ አሳታፊ መንገድ በተቀመጠው ጊዜ ገደብ በእንግሊዘኛና በአማርኛ ቋንቋ አዘጋጅተው ያቀርባሉ።