Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ81ኛው የአርበኞች የድል በዓል በሰላም | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ81ኛው የአርበኞች የድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

በአሉ የኢትዮጵያ አርበኞች ለሀገር ነፃነት አንድነትና ክብር የኢጣልያን ፋሽሽት ወራሪ ኃይልን በመመከት ከሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫዎች በመትመም /በመዝመት/ ጠላትን ያስጨነቁበት እና ድል ያደረጉበት አልበገር ባይነትን ያስመሰከሩበት "የኢትዮጵያ ጥንታዊ ጀግኖች አርበኞች የድል ቀን መታሰቢያ" በዓል ሚያዚያ 27 ለ81ኛ ጊዜ በመላው ሀገራችን እየተከበረ ይገኛል።

ጥንታዊ ጀግና አርበኞች የጣልያንን ጦር ለአምስት አመት ተዋግተው የሀገር ነፃነትን ማስከበር ችለዋል። ሁላችንም ይህን አኩሪ የድል ታሪክ ህያው አድርጎ ለማቆየት የአሁኑ ትውልድ ከጀግኖች አርበኞቻችን ገድልና ታሪክ በመማር የበኩላችን ድርሻ በመወጣት እንደ ጀግኖች አርበኞቻችን ህያው ሁኖ የሚያልፍ ስራ መስራት ይጠበቅብናል።
ሚያዚያ 27 ቀን /2014 ዓ.ም
"ክብር ለጀግኖች አርበኞቻችን!"

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ