Get Mystery Box with random crypto!

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮዎች ጋር ወጥ የሆነና የተደራጀ ሪ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮዎች ጋር ወጥ የሆነና የተደራጀ ሪፓርት ለማቅረብ በአዲሱ የሪፓርት ማቀረቢያ ቅፅ ዙሪያ የዙም ውይይት አካሄደ። ሚያዚያ 26 ቀን 2014.

የተጠቃለለ፣ወጥ የሆነ እና በተደራጀ መንገድ የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር እና የክልል እና የከተማ ፍትሕ ቢሮዎች ዐቃቤ ሕግ የተሰጠውን ተልዕኮ፣ ተግባርና ኃላፊነት ውጤታማ በሆነ መልኩ መፈፀም እንዲቻል በስራ ክፍሎች የሚከናወኑ ተግባራት ሪፓርት አቀራረብ ወጥነት ያላቸው ተነባቢ፣ ግልፅና ተጠያቂነት በተሞላበት መልኩ ለማቅረብ ዓላማ ይዞ የሚከናውን መሆኑ በውይይቱ ተገልዷል።

በቀጣይ የክልል እና የከተማ አስተዳደር ፍትሕ ቢሮዎች አዲሱን የሪፓርት ፎርማት ጠንቅቀው በመረዳት ውጥነት ባለው መንገድ ሪፓርት ሊያደርጉ እንደሚገባ በውይይቱ ተነስቷል።

በቀጣይ ከዙም ውይይቱ በመነሣት በሪፓርት አላላኩ ላይ ተጨማሪ የግንዛቤ እና የመወያያ መድረክ በመፍጠር የዳይሬከተሮች እና የባለሙያዎችን ግንዛቤ በማሳደግ ወጥ እና አዳጊ የሪፓርት አቀራረብ እንዲኖር ማድረግ ይገባል ተብሏል።