Get Mystery Box with random crypto!

የሰሜን ሸዋ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ጉዳዮች የስራ ሂደት ዐ/ህግ በተከሳሾች 1ኛ) ወር | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የሰሜን ሸዋ ዞን ፍትህ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ጉዳዮች የስራ ሂደት ዐ/ህግ በተከሳሾች 1ኛ) ወርቅአፈራሁ አሻግሬ ድንበሩ 2ኛ) አለምሸት አሻግሬ ድንበሩ በተባሉት ተከሳሾች ላይ በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ክርክር ያደረገ ሲሆን በአንደኛ ተከሳሽ ላይ በአንደኛ ክስ የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23 (3) እና 23 (2) (ሀ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሽ የማይገባውን ጥቅም ለራሱ ለማስገኘት በማሰብ በደ/ብርሀን ከተማ ቀበሌ 06 ቀጠና 2 ልዩ ቦታው ሰፈረ ሰላም (የታችኛው ሰፈረ ሰላም) እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ አዋሳኙ በሰሜን መንገድ፣ በደቡብ ባዶ ቦታ፣ በምስራቅ ሙሉ ተክሉ እና በምዕራብ መንገድ በሚያዋስኑት ስፋቱ 205.32 (ሁለት መቶ አምስት ከ ሰላሳ ሁለት) ካ.ሜ. የሆነን እና በ2012 ዓ.ም. በሊዝ መሸጫ የዋጋ ግምቱ ብር 3490706.92 (ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሺህ ሰባት መቶ ስድስት ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም) የሆነውን፤ ከሽንሻኖ የተረፈ ባዶ የከተማ ይዞታ ቦታ ቀኑና ወሩ በውል ባልታወቀ በ2011 ዓ.ም. በህገ ወጥ መንገድ በመያዝ ግንባታ የፈፀመ ሲሆን ይህን በህጋዊ መንገድ ያልተገኘን ይዞታ እና ግንባታ በህጋዊ መንገድ የተገኘ በማስመሰል በሀሰት የተዘጋጁ መንግስታዊ ሰነዶችን እንደ የይዞታ ማረጋጋጫ የምስክር ወረቀት የመሰሉትን በማያያዝ በቀን 17/11/2011 ዓ.ም በተፃፈ ክስ ለደ/ብርሀን ወረዳ ፍ/ቤት በማቅረብ የመ.ቁ. 0121127 በሆነው መዝገብ ተከፍቶ የፍታብሄር ክርክር ለማድረግ የተገለገለ በመሆኑ እንዲሁም ከአቶ ሰይፈ ዘውዴ ከተባለ ግለሰብ ጋር ለፈፀመው የብር 60000 (ስልሳ ሺህ ብር) የብድር ውል በመያዣነት እነዚህን በሀሰት የተዘጋጁ የሰነድ ማስረጃዋች ከውሉ ጋር በማያያዝ የተገለገለባቸው በመሆኑ በፈፀመው በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል በአንደኛ ክስ የቀረበት ሲሀን፡፡ በሁለተኛ ክስ የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 5(1) እና አንቀፅ 35 (ለ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ 1ኛ ተከሳሽ የከተማ ይዞታ ቦታ ከሊዝ ስሪት ወጪ ሊገኝ እንደማይችል እየታወቀ በደ/ብርሀን ከተማ ቀበሌ 06 ቀጠና 2 ልዩ ቦታው ሰፈረ ሰላም (የታችኛው ሰፈረ ሰላም) እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ አዋሳኙ በሰሜን-- መንገድ፣ በደቡብ-- ባዶ ቦታ፣ በምስራቅ-- ሙሉ ተክሉ እና በምዕራብ መንገድ በሚያዋስኑት ስፋቱ 205.32 (ሁለት መቶ አምስት ከ ሰላሳ ሁለት) ካ.ሜ. የሆነን እና በ2012 ዓ.ም. በሊዝ መሸጫ የዋጋ ግምቱ ብር 3490706.92 (ሶስት ሚሊዮን አራት መቶ ዘጠና ሺህ ሰባት መቶ ስድስት ብር ከዘጠና ሁለት ሳንቲም) የሆነውን፤ ከሽንሻኖ የተረፈ ባዶ የከተማ ይዞታ ቦታ ቀኑና ወሩ በውል ባልታወቀ ጊዜ በ2011 ዓ.ም. በህገ ወጥ መንገድ በመያዝ. ግንባታ የገነባ በመሆኑ በፈፀመው የከተማ ቦታን በህገ-ወጥ መንገድ መያዝ እና ግንባታ ማካሄድ ወንጀል በሁለተኛ ክስ የቀረበበት ሲሆን ሶስተኛ ክስ በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ በጋራ በ1997 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሬ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 (1) (ሀ) እና የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 23 (3) እና 23 (2) (ሀ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች የማይገባቸውን ጥቅም ለራሳቸው ለማስገኘት በማሰብ በደ/ብርሀን ከተማ ቀበሌ 06 ቀጠና 2 ልዩ ቦታው ሰፈረ ሰላም (የታችኛው ሰፈረ ሰላም) እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ አዋሳኙ በሰሜን መአዛ ታፈረ፣ በደቡብ መንገድ፣ በምስራቅ መሬም መሀመድ እና በምዕራብ ምንዳዬ ሀ/ጊዮርጊስ የሚያዋስኑት ስፋቱ 230 (ሁለት መቶ ሰላሳ) ካ.ሜ. የሆነን እና በ2012 ዓ.ም. በሊዝ መሸጫ የዋጋ ግምቱ ብር 3910299 (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር) የሆነውን፤ ቀደም ሲል በ2005 ዓ.ም. ለቤት መስርያ ቦታ ተሸንሽኖ የነበረና ግንባታ ባለመፈፀሙ ወደ መሬት ባንክ ገቢ እንዲሆን የተወሰነበትን የከተማ ቦታ በየካቲት ወር 2011 ዓ.ም. በህገ ወጥ መንገድ በመያዝ ግንባታውን የገነቡ መሆኑን ተከትሎ የከተማ አስተዳደሩ ግብረ-ሀይል ህገ-ወጥ ግንባታ ነው በሚል እንዲፈርስ ቢደረግም 1ኛ ተከሳሽ ለ2ኛ ተከሳሽ ወኪል በመሆን ይህን በህገ-ወጥ መንገድ የተያዘን የከተማ ቦታ በህጋዊ መንገድ የተገኘ በማስመሰል በሀሰት የተዘጋጁ መንግስታዊ ሰነዶችን በማያያዝ በቀን 1/12/2011 ዓ.ም የተፃፈ ክስ ለደ/ብርሀን ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት በማቅረብ የመ.ቁ. 0121182 በሆነው መዝገብ ተከፍቶ የፍታብሄር ክርክር ለማድረግ የተገለገሉበት ሲሆን በዚህም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል ክስ ቀርቦባቸዋል ፡፡አራተኛ ክስ በ1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች ላይ በጋራ በ1997 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሬ የወንጀል ህግ አንቀፅ 32 (1) (ሀ)ን እና የከተማ ቦታን በሊዝ ለመያዝ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 5 (1) እና አንቀፅ 35 (ለ) ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ተከሳሾች የከተማ ይዞታ ቦታ ከሊዝ ስሪት ወጪ ሊገኝ እንደማይችል እየታወቀ በደ/ብርሀን ከተማ ቀበሌ 06 ቀጠና 2 ልዩ ቦታው ሰፈረ ሰላም (የታችኛው ሰፈረ ሰላም) እየተባለ ከሚጠራው ስፍራ አዋሳኙ በሰሜን መአዛ ታፈረ፣ በደቡብ መንገድ፣ በምስራቅ መሬም መሀመድ እና በምዕራብ ምንዳዬ ሀ/ጊዮርጊስ የሚያዋስኑት ስፋቱ 230 (ሁለት መቶ ሰላሳ) ካ.ሜ. የሆነን እና በ2012 ዓ.ም. በሊዝ መሸጫ የዋጋ ግምቱ ብር 3910299 (ሶስት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አስር ሺህ ሁለት መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር) የሆነውን፤ቀደም ሲል በ2005 ዓ.ም. ለቤት መስርያ ቦታ ተሸንሽኖ የነበረና ግንባታ ባለመፈፀሙ ወደ መሬት ባንክ ገቢ እንዲሆን የተወሰነበትን የከተማ ቦታ በየካቲት ወር 2011 ዓ.ም. በህገ ወጥ መንገድ አጥረው በመያዝ ሰርቪስ ቤት የገነቡ ሲሆን የህም ግንባታ በደ/ብርሀን ከተማ አሰተዳደር ግብረ-ሀይል እንዲፈርስ ቢደረግም ተከሳሾች ይህን የከተማ ቦታ አሁንም ወካይ እና ተወካይ በመሆን በፍ/ቤት ክርክር እያደረጉበት በመሆኑ በፈፀሙት የከተማ ቦታን በህገ-ወጥ መንገድ መያዝ እና ግንባታ ማካሄድ ወንጀል ክስ ተከሰዋል፡፡ በተከሳሾች ላይ ያቀረብናቸውን ተደራራቢ ክሶችን በሰውና በሰነድ ማስረጃ አሟልተን በማቅረብ እንዲሁም በችሎት በጥሩ ሁኔታ ክርክር ከተደረገ በኋላ ተከሳሶች በዐ/ህግ በቀረበባቸው አራት ክሶ ሁሉ እንዲከላከሉ ብይን የሰጠና በመሆንኑ ተከሳሾችም አለን የሚሉትን የሰውና የሰነድ ማስረጃ አቅርበው ካሰሙ በኃላ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በቀን 24/08/2015 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጥፋተኛነት ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በዐ/ህግ በኩል ሁለት የቅጣት ማክበጃ ምክንቶች እንደያዙልን አሳስበን ሁለቱን የቅጣት ማክበጃ የተቀበላቸው ሲሆን በከሳሾች በኩል የቀረቡ 10 የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን በመቀበል ሁለቱም ተከሳሾች እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እና በብር 5000/ አምስት ሺህ ብር/ የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ እና ተከሳሾች ለ2 ዓመታት ከማንኛውም ህዝባዊ መብታቸው እንዲሻሩ ሲል ፍ/ቤቱ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡