Get Mystery Box with random crypto!

በሰሜን ሸዋ ዞን ፍትሕ መምሪያ የወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት አስተባባሪ ፣ የንዑስ ጉባኤ ጽ/ቤት | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

በሰሜን ሸዋ ዞን ፍትሕ መምሪያ የወንጀል ጉዳዮች የስራ ሂደት አስተባባሪ ፣ የንዑስ ጉባኤ ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ ህይወታቸው እስካለፈበት ጊዜ በወንጀል የተገኘ ሀብት ማስመለስ ቡድን መሪ በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ተክሌ ንጉሴ በደረሠባቸዉ ድንገተኛ ጉዳት ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው በ10/7/2015ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብር ሥነ ስርዓታቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ቤተሰብ፣የሥራ ባልደረባዎቻቸው በተገኙበት ዛሬ በ11/7/2015 በጠባሴ እግዚአብሔራብ ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

በባልደረባችን ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሠቦቻቸው፣ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ለስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናቱን እንዲሰጥልን እንመኛለን።