Get Mystery Box with random crypto!

የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ የዋስትና ይፈቀድልኝ ጥያቄ እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ የዋስትና ይፈቀድልኝ ጥያቄ እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ
(ሰኔ 03/2014 ዓ/ም)ብርጋዴር ጀኔራል ተፈራ ማሞ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋሉ ጊዜ ጀምሮ ክስ ሳይቀርብባቸው በጊዜ ቀጠሮ ቆይተው ሰኔ 02/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት መርማሪ ፖሊስ ምርመራውን አጠናቅቄ የተጣራውን የምርመራ መዝገብ ለዐቃቤ ሕግ ለመላክ በዝግጅት ላይ ነኝ ያለ ሲሆን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ዐቃቤ ሕግ ምርመራው ተጠናቋል፤የክስ መመስረቻ ጊዜ 15 ቀን ይሰጠኝ ሲል ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡
የተጠርጣሪው ጠበቆች በበኩላቸው ምርመራው ከተጠናቀቀ ደንበኛችን የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ዋስትና የሚያስከለክል ባለመሆኑና ሊጠፉ የማይችሉ ታዋቂ ሰው በመሆናቸው ዋስትናቸው ሊከበርላቸው ይገባል ሲሉ ተከራክረዋል፡፡
ፍርድ ቤቱም ምርመራው የተጠናቀቀ በመሆኑ የጊዜ ቀጠሮውን ጉዳይ ዘግቶ የተጠርጣሪ ጠበቆች ባቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ላይ ዐቃቤ ሕግ አስተያየት እንዲሰጥበት አድርጓል፡፡
ዐቃቤ ሕግም ተጠርጣሪው የተጠረጠሩት በሽብር ወንጀል ስለሆነ እና በሌሎች ተጨማሪ የወንጀል አይነቶች ስለሆነ ሊቀርቡ ስለማይችሉ ዋስትና ሊፈቀድላቸው አይገባም ሲል ተከራክሯል፡፡
ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ በዋስትና ጥያቄው ላይ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 3/2014 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ቀጠሮ መስጠቱ ይታወቃል።
ፍርድ ቤቱም በያዘው ቀጠሮ መሰረት መዝገቡን መርምሮ ዐቃቤ ሕግ ዋስትናው እንዲከለክል ያቀረባችውን ምክንያቶች ባለመቀበል ለተጠርጣሪው በ30,000 /ሰላሳ ሺህ/ ብር ዋስትናውን ፈቅዷል፡፡