Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሕግ ኦዲ | የአብክመ ፍትሕ ቢሮ ANRS JUSTICE BUREAU

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ከዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዙሪያ በተዘጋጀ ማኑዋል ላይ ከክልልና ከዞን የተውጣጡ ዐቃብያነ ሕግ በጎንደር ከተማ እየመከሩ ይገኛሉ። ዩ ኤስ ኤ አይ ዲ ፍትሕ ተግባራት በኢትዮጵያ ሪጅናል ሌጅስሌቲቭ ስፔሻሊስት አቶ ዘመኑ ታረቀኝ ዩ ኤስ አይ ዲ ፍትህ ተግባራት በኢትዮጵያ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ጋር በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ፤ይህ የምክክር መድረክም አንዱ መሆኑን ጠቅሰው የእንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋል።
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አያሌው አባተ (ዶ/ር) የሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ማኑዋል በፌዴራል ደረጃ መውጣቱን አስታውሰው፤ ይህን ማኑዋል ወደ ክልላችን በማምጣት የክልሉን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በማዘጋጀት እንድንመክርበት ቀርቧል ብለዋል። በሕግ ኦዲትና ኢንስፔክሽን በተዘጋጀው ማኑዋል ላይ የተለያዮ የማዳበሪያ ጥያቄና አስተያየቶች ከቀረበ በኋላ ጥልቅ ውይይት ተደርጎበት
በተነሱ ጥያቄዎች ላይ ምላሽ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።